>

እነ ጌችም በፊንፊኔያቸው  በሸነና እያሉ ነው፤ ጻድቃንም ንብረቱን አድኗል... የሞተ ተጎዳ…!! (ዘመድኩን በቀለ)

እነ ጌችም በፊንፊኔያቸው  በሸነና እያሉ ነው፤ ጻድቃንም ንብረቱን አድኗል… የሞተ ተጎዳ…!!

ዘመድኩን በቀለ


“…ከሰሜን ዕዝ ጀምሮ በዐማራና በአፋር በትግራይም ያንን ሁሉ ህዝብ አስጨፍጭፎ የራያው ተወላጅ ጀነራል ጻድቃን በመጨረሻ ህንፃዎቹና ቪላዎቹን የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንኩንና የራያ ቢራ ፋብሪካ ፋብሪካውን አድኗል። ማንሞኝ አለ።

“…በሉ እናንተም በረሃ ከርሞ የመጣ ጄነራል ስለሆነ በአንበሳ ባንኩ ገንዘባችሁን አስገቡለት። በጦርነቱ ምክንያት ምርት አቁሞ የነበረው የራያ ቢራም በቅርቡ ሥራ ይጀምራልና ቶሎቶሎ እየጠጣችሁ አቋቁሙት። ዳሽን፣ በደሌ፣ ምናምንን ለጊዜው አቁሙና የራያውን ልጅ ራያ ቢራን ጠጡለት። አፍርአባክ ደም ያስጠጣችሁና ልል ብዬ ከአፌ መለስኩት። ለጥቂት ልሳሳት ነበር።

“…ቦሌ መንድኃኔዓለም 2 ህንፃ፣ ራያ እና ጋምቤላ የእርሻ ባለቤት ነው ጻድቃን። እስከ አሁን ዐቢይ ደብቆ ህይወቱን አቆይቶለታል ሻአቢያ ግን የሚፋታው አይመስለኝም። ለጊዜው እንደተወራው አዲስ አበባ ከሆነ አርፏል ከሚባልበት ከእስካይ ላይት ሆቴል ባይወጣ ጥሩ ነው።

“…ሁለቱ የራያ ልጆች ጌቾና ጻድቃን ህወሓትን ሜዳ ላይ አስጥተው እነሱ አዲስ አበባ ገብተዋል። በሸነና እያሉም ነው። ወዳጄ እደግመዋለሁ። የሞተ ተጎዳ።

“…ያለ ባል የቀሩ ሚስቶች፣ ያለ አባት የቀሩ ልጆች፣ በዱላ ከስናይፐር ጋር ተናንቆ የረገፈው ምስኪን ገበሬ፣ ትምህርት ቤታቸው ወድሞ መማር ያቆሙ ተማሪዎች፣ ማስተማር ያልቻሉ መምህራን፣ ሆስፒታል፣ ጤና ጣቢያው የወደመበት ህዝብ፣ ውኃ ያጣው፣ በጦርነቱ የተደፈሩ እናቶች። የታረዱ ካህናት፣ የተረሸኑ ዲያቆናት፣ ሼኮች፣ የፈረሱ አብያተ ክርስቲያናትና መስጂዶች፣ በበሽታ፣ በረሃብ ያለቀው፣ የተፈናቀለው፣ ቤተሰቡ የተበተነው ምስኪን ህዝብ፣ እሱ ተጎዳ። እንጂማ የጦርነት መጨረሻው የታወቀ ነው። በኢትዮጵያ ደግሞ ሚልዮኑን ትገድላለህ በእርቅ ሰበብ ነፃ ሆነህ ተንፈላሰህ ትኖራለህ።

• ጧ በል እደግመዋለሁ የሞተ ተጎዳ…!!

Filed in: Amharic