>

አሊ ቢራ እና ሃጫሉ፤ ኢትዮጵያ እና ኦሮሚያ። (ዘመድኩን በቀለ)

አሊ ቢራ እና ሃጫሉ

ኢትዮጵያ እና ኦሮሚያ

ዘመድኩን በቀለ


“…ሁለቱም በኢትዮጵያ ተወልደው። ኢትዮጵያዊነትን ተጸይፈው በዘር ከረጢት ውስጥ ተወሽቀው የኖሩና ኢትዮጵያ ጠል ጎጠኛ ትውልድ እንደ አሸን አፍርተው ያለፉ የዘር አቀንቃኝ ዘፋኞች ነበሩ። የጥንቱንም ሆነ የዘመኑን የኦሮሞ ወጣት ከኦሮሞነት በቀር ኢትዮጵያዊነቱን እንዳያይ እንዳይመለከት በጭፍን ኦሮሞነትን እንደ ሃይማኖት ተቀብሎ እንዲኖር አበክረው ሲሰብኩ የኖሩ የዘር አቀንቃኝ የነበሩ ግለሰቦች ነበሩ። አንድም ቀን በየትኛውም ስፍራ ተሳስተው ለኢትዮጵያዊነት፣ ለህዝቦች መቀራረብ፣ መቻቻል እና አንድነት ፍቅርም በሙያቸው ሰብከው፣ አስተምረው የማያውቁ፣ በዚህ ዘርፍ ምንም ዓይነት በጎ ሪከርድ የሌላቸው ዘፋኞች ነበሩ። በእነዚህ አቀንቃኞች ስብከት የተነሣ ስንቱ ንፁህ ኢትዮጵያዊ እንደታረደ ቤት ይቁጠረው።

“…አሊ ቢራ ከጋረሙለታው የሐረርጌ ተወላጅ ከእነ ጋሽ ጥላሁን ገሠሠ፣ ከጉራጌው ኢትዮጵያዊ ከእነ ጋሽ መሀሙድ አሕመድ፣ ከእነ ጋሽ ምኒልክ ወስናቸው ጋር በታላቁ የክብር ዘበኛ ውስጥ ተቀጥሮ አብሮ የሠራ፣ አንድም ቀን ግን ኦሮሞ፣ ኦሮሞ ከሚል የዘር ዘፈን በቀር እንደ ጓደኞቹ ለሃገር፣ ለወገን የሚጠቅም ዘፈን ሲዘፍን ዓይቼው ሆነ ሰምቼው አላውቅም። በቁማቸው ኢትዮጵያን እየጠሉ፣ እየተጸየፉም ከሞቱ በኋላ በኢትዮጵያ ስም አስከሬናቸውን ለማክበር መላላጡ ያስተዛዝባል። ሃጫሉና አሊ ቢራ አሁን አንዴ ከሞት ተነሥተው የሚደረግላቸውን ቢያዩ መንግሥትን ፍርድቤት ሁላ ይገትሩት ነበር።

“…ሃጫሉ ሁንዴሳ ኦርቶዶክስ ሆኖ በትክክል እስላሙ አሊ ቢራ አምጦ በአምሳሉ የወለደው ታዋቂ የጥፋት ልጁ ነው። “ቄሮ ጂርቱ” የሚል መፈክር ለአራጁ የኦነግ ገዳይ ቡድን አንደመፈክር እንዲጠቀምበት ከእስላም ኦሮሞ ውጪ ሌላው ዜጋ እንዲታረድበት የሚያደርግ መፈክር ፈጥሮ ለኦሮሞ ተገንጣይና ፅንፈኛ ቡድኖች የበረከተ ግለሰብ ነው። ያለ አቅሙ ከፍ ብሎ አፄ ምኒሊክን ባዋረደ በማግስቱ የተቀሰፈ አሳዛኝ ፍጥረት ነው። እናም ዛሬ ከሞቱ በኋላ ጽንፈኞቹ እሺ እንደፈለጉ ያድርጓቸው የሌላው ማሽቃበጥ ግን አልገባኝም።

“…የኦሮሞ ፅንፋኞች ሐዋርያ የነበሩት አሊ ቢራና ሃጫሉ ሁንዴሳ በምን ሂሳብ ነው “የኢትዮጵያ ጀግና” ተብለው በኢትዮጵያ ስም እንዲወደሱ የሚፈለገው? ሁለቱም በጽንፈኛ ኦሮሞዎች ዘንድ እንጂ በሌላው ኢትዮጵያዊ ዘንድ የሚታወሱበት አንዳችም ታሪክ ያላቸው አይመስለኝም። እስቲ አንድ ሁለት ብላችሁ ቆጥራችሁ አሳዩኝ። አጭቤ ሁላ። እርግጥ ነው የሞተ ሰው አይወቀስም። ደግሞም የሞተ ሰው ባልዋለበት አይደስም። ሰው ለራሱ፣ ለቤተሰቡ፣ ለወዳጅ ዘመዱ፣ ለማኅበረሰቡ፣ ለሃገሩ በሠራው መጠን ነው መወደስ ያለበት።

“…በቅርቡ እኮ ነው የሃጫሉን ግድያ ምክንያት በማድረግ #Prime_media #ዳንዲ_ሀራ በተሰኘ የብልፅግና ልሣን በነበረ ፕሮግራም ላይ ተጋባዥ ሆኖ ቀርቦ ከአንድ ጎምቱ አንጋፋ ዘፋኝ የማይጠበቅ ነውረኛ ቃለመጠይቅ አድርጎ የነበረው። አዝማሪ አሊ ቢራ(ዶር) ከጋዜጠኛው ለቀረበለት ጥያቄ የሰጠውን መልስ ቪድዮውን ከነትርጉሙ አያይዤላችኋለሁ። ስሙት ተመልከቱት።

“…

ጋዜጠኛው የሀጫሉን ሞት ተከትሎ በኦሮሚያ የተፈጠረው ክስተትና አለመረጋጋትን እንዴት ትገልፀዋለህ? ወደፊትስ ምን መደረግ አለበት ብለህ ትመክራለህ? በማለት የአንጋፋነት፣ የአባትነት ሚናውን ወስዶ እንዲያረጋጋ በሚመስል ጥያቄ ነበር ቃለ መጠይቁን የጀመረው።

“…የክቡር ዶ/ሩ አዝማሪ አሊ ቢራ ግን እንዲህ በማለት ነበር ለጋዜጠኛው የመለሰው። “…ጭፈጫፋው ልክ ነው። የሞተው ዐማራና ኦርቶዶክስ እኮ ነው። እና ኦርቶዶክስና ዐማራ ቢሞት ምን ያስደንቃል? አታጯጩሁ፣ ነገር አብርዱ የሚል የሚመስል መልስ ነበር የሰጠው። አንዳችም አይነት በሞቱት፣ በታረዱት ህፃናት፣ ሴቶች፣ እናቶች፣ ወንድሞችና እህቶች፣ ኣዛውንቶች፣ ካህናትና ዲያቆናት ቅንጣት ታህል የማዘን ስሜት ሳይኖረው ነበር ቃለመጠይቁን የጨረሰው።

“…የኦሮሞ ህዝብ ያጣው እኮ ውዱን እና ዕንቁ ልጁን ነው። የኦሮሞ ህዝብ በዚያ ስሜት ውስጥ ሆኖ ያደረገው ነገር፣ በንፁሐን ላይ የፈጸመው አረመኔያዊ ተግባር ሁሉ ልክ ነው። አንድ ሰው ዘሎ ኪስህ ገብቶ ቦርሳህን ቢወስድብህ ዝም ብለህ ቆመህ አታይም። react ታደርጋለህ። ስለዚህ ችግር የሚሆነው ዕንቁህን ሲነጥቁህ ዝም ብለህ ካየህ ነው። ያጣነው እኮ ሀጫሉን ነው። የኦሮሞ ህዝብ ሃጫሉን ተነጥቆ ዝም ቢል ኖሮ በጣም ይገርመኝ ነበር በማለት ነው ለአንድ ሃጫሉ ሺዎች ሃጫሉን የማያውቁም፣ የሃጫሉ ዘመዶች ሳይቀሩ የታረዱት፣ ንብረታቸው የወደመባቸው በሙሉ የተፈጸመባቸው ትክክል ነበር ያለው። ራሱ ነው የሚለው። ቪድዮውን እዩት። አሊ ቢራ ቀጠለና “መንግሥትም ከዚያ በኋላ ህዝቡ እንዲህ አጠፋ እንዲያ አደረገ ብሎ የሚያወራው ነገር ስህተት ነው። ከ50 ሚልዮን ኦሮሞ መካከል አንድ ሺህ ኦሮሞ እንዲህ አደረገ ተብሎ፣ የተወሰኑ ሰዎች ባደረሱት አደጋ ኦሮሞን እንደ አጥፊ መሳሉም ልክ አይደለም ይልና በመቀጠል በዚያው ምነው ሰሞኑን በአሜሪካ በተገደለው ጆርጅ ፍሎይድ ምክንያት የደረሰውን የህዝብ ቁጣ አላየንም እንዴ? በማለት ይጠይቅና የአሜሪካውን የህዝብ ገዳዩ ፖሊስ ለፍርድ ይቅረብልን ብሎ ያመጸውን አመጽ የህዝቡን ተቃውሞ ከኦሮሞ አረመኔያዊ ጭፍጨፋ ጋር ሊያመሳስለው ይላላጣል። አሜሪካውያኑ እኮ ነጭ ጥቁር ሳይሉ የተቃወሙት መንግሥትን ነው። ያወደሙትም የመንግሥትን ንብረት ነው። ጥቁሮች፣ ስፓኒሾች፣ ነጮች፣ አፍሪካውያን፣ ዐረቦች፣ እስያውያን አሜሪካውያን በሙሉ ለፍትህ ነበር ያመፁት። በዘር ሳይለያዩ ፍትህን ነበር የጠየቁት። ያን የሰለጠነ ዐመፅ ከኦሮሞው ጅሃዳዊ ጭፍጨፋ ጋር ሊያቀራርበው አቻ ወንጀል ለመፍጠር ነበር የሚላላጠው። ሃጫሉን የገደለው ራሱ መንግሥት ነው። ኦሮሞ ግን በሃጫሉ ሞት ተናዶ ያረደው ዐማራንና ኦርቶዶክስን ነው። ፅንፈኛው አክራሪ አሊ ቢራ ለእሱ የዜጎች ሞት ሞት አይደለም። ለአንድ ሃጫሉ ሞት ሺ ዐማራ ቢታረድ ደንታው አልነበረም። አሚኮ ሰምተሃል። አሽቃባጭ።

“…አሊ ቢራ ይቀጥልናም እንዲህ ይላል። በሕግ የበላይነት ስም ስንት ወጣት እንደተሰዋብን ዓይተናል። ነገር ግን ሃጫሉን የመሰለ ውድ ልጅ አጥቶ ቆሞ የሚያይ ሰው ለእኔ ጤነኛ አይመስለኝም። ለምሳሌ ህጻን ልጅህን ከእጅህ ላይ ሲነጥቁህ React ካላደረክ አንተ ለእኔ ጤነኛ አይደለህም ማለት ነው። በሃጫሉ ግድያ የኦሮሞ ህዝብ ዝም ቢል ኖሮ ያ ህዝብ ለእኔ የሞተ ነበር በማለት ነበር የመለሰው። በወቅቱ ግን የኦሮሞ ህዝብ በዝዋይ፣ በሻሸመኔ፣ በጅማ፣ በአሩሲ፣ በባሌ፣ በሚኤሶ፣ በአሰበተፈሪ፣ በሐረርና በአጠቃላይ በኦሮሚያ ከፖሊስ ጋር፣ ከወታደር ጋር አልተጋጨም ነበር። ወታደሩና ፖሊሱ እያየ ነበር ሺዎች የታረዱት። የተዘረፉት፣ በአንድ ጀንበር የደሀ ደሀ የሆኑት። ህጻናት ያለ ወላጅ ቀርተው ሴተኛ አዳሪና ለማኝ የኔ ቢጤ የሆኑት። እናም ይሄንን ሰው ነው የኢትዮጵያ ጀግና ብዬ አልቅሼ አሸኛኘት የማደርግለት?

“…አላደርገውም። ገና ፈጣሪ ፊት ሲቀርብ በንፁሐን ሞት ይጠየቃል። ጧ በል ይሄ የእኔ እውነት ነው። ሰውዬዎቹን እንደሰውነታቸው አልጠላቸውም። አስተሳሰባቸውን ንና ክፉ ሥራቸውን ግን አጥብቄ እፀየፈዋለሁ። አሁን በእኔ በዚህ አቋም ጽንፈኛው የኦሮሞ የወሃቢይ እስላም፣ የኦነግ አራጅ ቡድን፣ አክራሪ የኦሮሞ ብሔርተኞች፣ አሽቋላጭ፣ አስመሳይ፣ ገረድ እና አሽከር የዐማራ ካድሬና ፖለተኞች ቅር ሊሰኙብኝ፣ ሊናደዱና ሊሰድቡኝ ይችላሉ። ለደንታችሁ ነው። ከፈለግክም በአናትህ ተተከል። እውነታው ይሄ ነው።

Filed in: Amharic