>

ጋዜጠኝ ተመስገን ደሳለኝ ዛሬ በ 30,000 ብር ዋስ ከእስር ቤት እንዲወጣ ፍርድ ቤት ወስኗል...! (ታሪኩ ደሳለኝ)

ጋዜጠኝ ተመስገን ደሳለኝ ዛሬ በ 30,000 ብር ዋስ ከእስር ቤት እንዲወጣ ፍርድ ቤት ወስኗል…!

ታሪኩ ደሳለኝ


የቂሊጦ እስር ቤት በበኩሉ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን አልፈታም ብሏል…!

የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እውነታዎች ወደ ክብራቸው ተመልሰዋል። የዘገየም ቢሆን እውነት ማደሪያዋን አግንታለች።

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እንዲከላከል የተወሰነው በእስር በማያስቀጣ አንቀጽ መሆኑ  በግልፅ ተቀምጦ፣ በቀላል አማርኛ፦ የሀገር መከላከያን በተመለከተ ምንም አይነት ምስጢር አለማውጣቱንም ሆነ ተቋሙን የሚጎዳ ነገር አለመጻፉን ፍርድ ቤቱ በማረጋገጡ የዐቃቢ ሕግ ክስ ውድቅ ሆኖ የልደታው ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ ፀረ ሽብርና የሕገ-መንግሥት ጉዳዮች ችሎት ዛሬ ሕዳር 6/2015 ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በሰላሳ ሺ ብር ዋስ ከእስር እንዲወጣ ወስኗል።

በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ 175 ቀናትን በእስር ቤት ባሰለፈበት ጊዜ ድምፅ ለሆናችሁት የሰብዓዊ መብትና የሚዲያ ተቋማት፣ የፍትሕ መፅሔት ቤተሰሶች፣ በዘር ገመድ ያልታጠራችሁ በአገር ውስጥና በውጭ ሀገራት ለምትገኙ የማህበረሰብ አንቂዎችና የጋዜጠኛ ተመስገን አድናቂዎች በሙሉ የከበረ ምስጋናችንን እናቀርባለን።

የቂሊንጦ እስር ቤት ተመስገን ይፈታ የተባለበት ሙሉ ፎርማሊቲውን ያሟላ መፈቻ ከችሎቱ ቢደርሰውም  ተመስገንን ለመፍታት ፍቃደኛ አለመሆኑን ገልፆልናል፡፡

Filed in: Amharic