>

"አብይ አህመድ ከስልጣኑ ውጭ የማይደራደርበት አጀንዳ የለውም...! (መዓዛ መሐመድ)

“አብይ አህመድ ከስልጣኑ ውጭ የማይደራደርበት አጀንዳ የለውም…!

መዓዛ መሐመድ

 


*… በስልጣኑ አይምጡበት እንጂ፣ ሚሊዮኖች በአንድ ቀን ቢያልቁ ለእሱ ጉዳዩ አይደለም።” –

ጦርነቱ የተደረገው ስልጣን ለማስጠበቅ እና ስልጣን ለመቀማት በቋመጡ ሁለት ሀይሎች መካከል ነው። በዚህ መሐል የወደመው አማራ ነው። ህወሃቶችም የትግራይን ወጣት ጭዳ ካደረጉ በሗላ ሞት ወደ እነሱ ሲጠጋ ‘ስልጣንህን አንቃወምም፣ እውቅናም እንሰጣለን’ ብለው ከአብይ አህመድ ጋር እደራደራለሁ ብለዋል። በዚህ መሐል የአማራ ፖለቲከኞች አገጫቸውን ይዘው ከመመልከት ውጭ ሌላ ምንም አላደረጉም። ምክንያቱም የአማራ ህዝብ እንጂ እነሱ ምናቸውም አልተነካም።

አብይ አህመድ ከስልጣኑ ውጭ የማይደራደርበት አጀንዳ የለውም። ብቻ በስልጣኑ አይምጡበት እንጂ፣ ሚሊዮኖች በአንድ ቀን ቢያልቁ ለእሱ ጉዳዩ አይደለም። በአጠቃላይ ሁለቱ የጠገቡ ሀይሎች በንፁሐን ደም ከተራጩ በሗላ፣ ስልጣናቸውን አስጠብቀው ተስማምተዋል።

ኘሪቶሪያ ሄደው የተደራደሩት ስለወደመው አማራ፣ ስለ ወልቃይትና ራያም አይደለም። የኘሪቶሪያው ስምምነት ስለ ስልጣን ክፍፍል የተደረገ ነው። አሁን በስምምነቱ መሰረት ህወሃት ወደ ፌደራል መንግስት ሳያንጋጥጥ ትግራይ ክልልን እንዲያስተዳድር፣ አብይ አህመድም ወንበሩን ማደላደል ነው እቅዱ። አሁን ተስማምተዋል።

Filed in: Amharic