>

ኦነግ/ሸኔ ዙሪያ ገብ ጦርነት ከፍቷል ! ( ቴዎድሮስ ሀይለማርያም)

ኦነግ/ሸኔ ዙሪያ ገብ ጦርነት ከፍቷል !

    ቴዎድሮስ ሀይለማርያም


   1. በሰሜን ሸዋ ደራ ሙሉ በሙሉ   ለኦነግ/ ሸኔ ከተተወ ቆይቷል። በተለይም ባለፉት ሶስት ቀናት   ይህ ኃይል በርካታ ታጣቂዎቹን አሰማርቶ በህዝብ ላይ  ጦርነት ከፍቷል፡፡ አብዛኛው ነዋሪ አማራ በሆነበት በደራ ፣ በርካታ ንፁሀን ተገድለዋል ፤ ዘረፋ ተፈፅሟል ፥ በቅዳሴ ላይ የነበሩ የቤተ-ክርስቲያን ካህናትን ጨምሮ በርካቶች በቡድኑ ታግተው ተወስደዋል፡፡ ለዜጎች የድረሱልን ጥሪ የመንግሥት አካላት የሰጡት መልስ ” ትእዛዝ አልተሰጠንም!” የሚል ነው፡፡

2. በምዕራብ  ሸዋ ዞን ኖኖ ወረዳ አብዛኛው  ቀበሌ በኦነግ ሸኔ እጅ ይገኛል። በአዋዲ ጉልፋና አርዲ ጉልፋ ቀበሌ የሚኖሩ አማራዎች ላይ በኦነግ ሸኔ ታጣቂ ሃይል ጥቃት እየተፈፀመባቸው ነው።  እነዚህ ቀበሌወች የአማራ ተወላጆች በብዛት ያሉባቸው ሲሆን በወረዳ አመራሮችና የፀጥታ ሃይሎች ችልተኝነት ፣  ካአቅም በላይ ነው ውጡ በማለትና ነዋሪወችን በማሸበር ፣  1ኛ ዲኮ ሽሞ ቀበሌ ፣ 2ኛ ሚጣሪ የበኒ  ቀበሌ ፣ 3ኛ አብዬ የበኒ  ቀበሌ ፣ 4ኛ  ጫንዶ ከተማ  በኦነግ ሸኔ ቁጥጥር ሥር እንዲሆኑ ተደርጓል። ህዝቡ ድጋፍ ይፈልጋል።

   3. የሰሜኑን ጦርነት አስቆማለሁ እያለ ለተራዘመ ጦርነት የሚደግሰው ብልፅግና ፣ እዚህ መኻል ሀገር  ኦነግ/ሸኔ የሚያካሂደውን መጠነ ሰፊ ወረራ የሚፈልገው ይመስላል። ከፊል አማፂ ፣ ከፊል መንግሥታዊ የሆነው ኦነግ/ሸኔ  የኦሮሞ ክልል በርካታ ዞኖችን ተቆጣጥሮ ያለከልካይ እያረደና እየዘረፈ ነው። ከቀናት በፊት በወለጋ ነቀምት ባንኮችንና የመሣሪያ መጋዘኖችን ዘርፎ በሰላም ወደ መጣበት ተመልሷል። ለመዲናችን አዲስአበባ አጎራባች የሆኑትን የምስራቅ ፣ የምዕራብና የሰሜን ሸዋ ዞኖች ማተራመስ ከያዘ ሰነባብቷል !

Filed in: Amharic