>

ሰዋሰው መልቲሚዲያ ከክብር ዶክተር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን ጋር አብሮ ለመስራት ተፈራረመ...!

ሰዋሰው መልቲሚዲያ ከክብር ዶክተር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን ጋር አብሮ ለመስራት ተፈራረመ…!


ሰዋሰው መልቲሚዲያ  በቅርቡ (መስከረም 29/2015 ዓ.ም) በሸራተን አዲስ ሆቴል በርካታ የሙዚቃ ባለሞያዎች (ግጥምና ዜማ ደራሲያን፤ ድምፃውያን እና አቀናባሪዎች ) በተገኙበት ሰዋሰው የተሰኘ የሙዚቃ ማስተላለፊያ አፕልኬሽን ማስመረቁ ይታወሳል።

በዚሁ መርሃ ግብር ላይ ከበርካታ የሙዚቃ ባለሞያዎች ጋር በጋራ አብሮ ለመስራት እሚያስችለውን የፊርማ ስነ ስዓት ፈፅሟል ። በዕለቱም  የቴሌኮም እና የፋይናንስ ሴክተሩን ከኪነ ጥበብ ማህበረሰቡ ጋር በማስተሳሰር ሙያው ለሃገር ኢኮኖሚያ እና ለሃገር ግንባታ የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ ከግምት ውስጥ በመክተት በጋራ እንዴት መስራት እንደሚቻል ከስምምነት ላይ ተደርሷል።

ከዚህ ቀደም  በሃገራችን የቴክኖሎጂ ዘርፍ በተግባር ተጨባጭ ስራዎችን በሰሩ ስራ ፈጣሪዎች የተቋቋመው ሰዋሰው መልቲሚዲያ ከተወዳጁ ድምፃዊ ክቡር ዶክተር  አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን ጋር በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል።

በቀጣይም የሚያወጣው አልበም ስራዎቹ ሙሉ በሙሉ  ተጠናቀው ሲወጡ ሰዋሰው በተሰኘው መተግበሪያ ላይ እንደሚለቀቁ የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ መሰረት ፍቅሩ ለዘሐበሻ አስታውቀዋል።

ሰዋሰው መልቲሚዲያ በአሁኑ ወቅት  ከ 70 በላይ አንጋፋ እና ወጣት የሙዚቃ ባለሞያዎች ጋር በጋራ እየሰራ ሲሆን ይኸው  ክሬኤቲቨ ኢኮኖሚን (Creative Economy)” የመገንባት ግዙፍ ፕሮጀክት ሙሉ ለሙሉ በእናት ባንክ ፋይናንስ የተደረገ መሆኑ ተገልጿል።

የሰዋሰው ሊንክ http://onelink.to/eytj27

Filed in: Amharic