ከአዲስ አበባ ወደጎጃም የሚወሴደው መስመር በኦነግ ሠራዊት ተዘጋ….!
ፅናት ሚዲያ -Tsinat media
መንግስት ካለ የህዝብን ደህንነት ያስጠብቅ ለመንግስትም አድርሱልን መንገዶኞች
ከአዲስ አበባ ወደ ጎጃም ይጓዝ የነበሩ መኪኖች ቆመዋል ተሳፋሪዎችና ሹፌሮች ያስተላለፉት መልክት!!
እንደሚከተለዉ እናቀርባለን
ከትላንት ጀምሮ እንዲሁም አሁን በዚህ ስአት ከአዲስ አበባ ተነስተው የህዝብ ማመላለሻ አውቶብሶች፣የጭነት መኪኖች፣ሬሳ የጫኑ መኪኖች፣የግለሰብ መኪኖች እንዲሁም አገር አቋራጭ ባሶች ነዳጅም ሸቀጣሸቀጥም የጫኑ መኪኖች በሙሉ ወደ ጎጃምና አልፈውም ወደ ጎንደርና የሚሔዱ መኪኖች በሙሉ አሊ ዶሮ አካባቢ ኦነግ ሸኔ በከፈተው ከፍተኛ ጦርነት አማካኝነት ሁሉም መኪኖች ተሳፋሪዎቻቸውን እንደያዙ ከትላንት ጀምሮ መንገድ ላይ ለማደር ተገደዋል።
በኦነግ ሰራዊት ከበባ ማንኛውም መኪና ወደ ጎጃም ማለፍ አይችልም።
እጅግ አስከፊ ጦርነት ነው እየተካሄደ ያለው ሲሉ ከተጓዦች መካከል ስማቸውን መጥቀስ ያልፈለጉ ግለሰቦች መረጃውን ነግረውናል።
እጅግ ብዛት ያለው መከላከያ እኛን እያለፈ ከወደ አዲስ አበባ ወደ አሊ ዶሮ ወይም ጦርነቱን ወደ አለበት ቢጓዝም አሁንም ሰላም ነው እለፉ የሚለን አካል እስካሁን አልመጣም። የመንግስት ጥበቃ በሌለበት መንገድ ላይ ህፃናት ሳይቀሩ አዛውንቶችም በሽተኞችም ሬሳ የጫኑ ሀዘንተኞችም ጫካ ውስጥ ለማደር ተገደናል።
የሚደርስልን መንግስት ባይኖርም እንኳ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያውቅልን መረጃውን አድርሱልን ሲሉ ተማፅኗቸውን አሰምተዋል።
በአሁኑ ሰዓት #ጉዞ ከአዲስ አበባ ወደ ጎጃም መንገድ በኦነግ ሠራዊት ዝግ ነው።