የኦሮምያ ባንዲራ አይሰቀልብንም መዝሙሩንም አንዘምርም ያሉ ተማሪዎች ቁጣቸውን ገለጹ….!
ስንታየሁ ቸኮል
በአዲስ አበባ ከተማ ሽሮሜዳ በቀድሞ ስሙ አምሀ ደስታ በአሁኑ (እንጦጦ አምባ ) ት/ቤት ተማሪዎች አመፅ አነሱ።
የአመፁ ምክንያትም ኦህዴድ በግዳጅ የጣለባቸውን የኦሮሚያን መዝሙር ካልዘመራችሁ፣የኦሮሚያን ባንዲራ ካልሰቀላችሁ በሚል እኛ ይህንን ለማድረግ ወደ ግቢ አልመጣንም በሚል አለመግባባት መሆኑ ታውቋል።
በሁኔታውም የአካባቢው ማህበረሰብም ጭምር ተሳትፎ እንዳደረገ ከቦታው መረጃ አድረሰውናል።
ፖሊስ በቦታው በመድረስ በ2ት ፒካፕ ተማሪዎችን ጭነው መሄዳቸውን እና ሁለት ህፃናት ላይ ጉዳት መድረሱን ከቦታው የነበሩ ግለሰቦች ለፅናት ሚዲያ ተናግረዋል።በዚህም ምክንያት የዛሬ ትምህርታቸው ተቋርጦ ውሏል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ኦህዴድ በሌሎች ትምህርት ቤቶችም ይህንኑ አይነት የተማሪዎች አመፅ ይነሳል በሚል ስጋት በተለያዩ ትምህርት ቤቶች በር ላይ በርካታ ፖሊስ አስማርቶ እንደዋለ ተስተውሏል።
ምንጭ፦የአካባቢው ነዋሪዎች