>

በአዲስ አበባ የፖለቲካ ድርጅት አመራሮች ጨምሮ ጋዜጠኞችና የተለያዩ ግለሰቦች እንዲታሰሩ ከከንቲባ አዳነች አበቤ ቀጥተኛ ትእዛዝ ወጣ...! (ፅናት ሚዲያ) -

በአዲስ አበባ የፖለቲካ ድርጅት አመራሮች ጨምሮ ጋዜጠኞችና የተለያዩ ግለሰቦች እንዲታሰሩ ከከንቲባ አዳነች አበቤ ቀጥተኛ ትእዛዝ ወጣ…!

ፅናት ሚዲያ 


የመምህር መስከረም አበራ እስር የከንቲባ አዳነች አቤቤ ቀጥተኛ ትዕዛዝ እስር መሆኑ ተረጋግጧል…!

  በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የገጠመው ሕዝባዊ ተቃውሞ ለማስተንፈስ የተጠናከረ እስርና ወከባ በተለዩ ጋዜጠኞች የማህበረሰብ አንቂዎች ፖለቲከኞች ላይ እስር እንዲጀመር ለአዲስ አበባ ፖሊስና ለአዲስ አበባ ሰላምና ደህንነት ቢሮ  ከንቲባ አዳነች አበቤ ቀጥተኛ ትህዛዝ በወጣ መመሪያ ማስተላለፋቸዉ ታውቋል።

የፌደራል ፖሊስ የብሔራዊ ደህንነት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ባደረጉት የሁለት ቀን ስብሰባ በከተማዋ የሚታወቁ ፖለቲከኞች እና ጋዜጠኞች  ጨምሮ ዋና ዋና ተብለዉ የተለዩ ግለሰቦች በኦህዴድ /ብልፅግና አመራሮች በእጅጉ ጥርስ ተነክሶባቸዋል የሚሉት የመረጃ ምንጮች በሰሞኑ በርካታ ሰዎች የመታሰር የመታፈን እድል እንዳላቸው ለፅናት ሚዲያ  ገልፀዋል። እንደ መረጃ ምንጮች በዚህ ሳምንት በአዲስ አበባ ታዋቂ ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች ላይ አዳዲስ እስሮች እና ወከባወች አሉ ብለዋል።

Filed in: Amharic