>
5:13 pm - Saturday April 19, 0656

የፊደል ቅኝ ግዛት.....! (ታደለ ጥበቡ)

የፊደል ቅኝ ግዛት…..!

 

ታደለ ጥበቡ


*… ሦስት አራት ቋንቋ ማወቁ ክፋት የለውም።ክፋቱ በባእዳን ቋንቋ ጻፉ የሚሉት ነገር ነው።የኦነግ ርዝራዦች ከግእዝ ፊደል የላቲን ፊደል በለጠባቸው…!

*ኢትዮጵያ የራሷ ፊደል፣ ቋንቋ፣ ባህል፣ ወግ፣ትውፊት፣ማንነትና ሃይማኖት ያላት የብዙ ሕብረ ብሄር መገኛ ሙዚየም ነች።ኢትዮጵያ ነጻነቷን አስከብራ የኖረች ስንል ማንነቷ፥ባህልና ቋንቋው ያልተከለሰባት በራሷ ታፍራና ተከብራ የምትኖር ማለታችን ነው።

*ኢትዮጵያ የራሷ ፊደል ያላት ሀገር ናት።ነገርግን የራሷ ፊደል እያላት እንደ አፋን ኦሮሞ ያሉ ቋንቋዎች የሚጻፉት በላቲን ፊደል ነው።የግእዝ ፊደል ብቁ አይደለም እንዳይባል፦

1.በጃንሆይ ዘመን  “በሪሳ”የተሰኘ  የኦሮሞ ጋዜጣ በግእዝ ፊደል ይዘጋጅ ነበረ።

2.ከመቶ አመት በፊት አባ አናሲሞስ የተባሉ የወለጋ አባት መጽሐፍ ቅዱስን በግእዝ ፊደል በኦሮሞኛ ቋንቋ ተርጉመውታል።እንግዲህ ኦሮምኛ ቋንቋ በበቂ ሁኔታ በግእዝ ፊደል መጻፍ እንደሚቻል እነዚህ ጥሩ ማስረጃዎች ናቸው።

*በላቲን እና በግእዝ ፊደል መጻፍ ሰፊ ልዮነት አለ።ለምሳሌ በላቲን ፊደል Haacaaluu  Hundeessa= 18 የላቲን ፊደላት ይወጠዋል።

*በግእዝ ፊደል  ሃጫሉ  ሁንዴሳ = 7  የአማርኛ ፊደል ይሆናል።ይኼም ማለት 18-7=11 የላቲን ፊደል ጭማሪ አለው ማለት ነው።ልዮነቱ ይኼን ያህል ይሰፋል።በተጨማሪ “አመሰግናለሁ” በላቲን “galatoomaa” ነው።በግእዝ ፊደል ደግሞ “ገለቶማ” ነው።በላቲን 10 ፊደላት ሲፈጅ በግእዝ 4 ብቻ ነው የሚፈጀው።

*”በጣም አመሰግንዎታለሁ” ወይም “በጣም አመሰግናቹሃለሁ”ማለት ደግሞ በግእዝ ፊደል፣”ባይ ኤን እስን ገለቴፈደ” ነው።13 ፊደላት ያስፈልጋሉ። በላቲን “Baay’een sigalateeffadha”  23 ፊደላት ያስፈልጋሉ።

*እንዲያው ኦሮሞኛ ቋንቋ በሌሎች አካባቢዎች ይሰጥ ከተባለ ቋንቋ ማወቁ፣መማሩ አይከፋም  ነገርግን መጻፍ ያለበት በውጭ ሀገር የላቲን ፊደል ሳይሆን አባቶቻችን ቀርጸው ባስተላለፉልን የግእዝ ፊደል ነው።ለምሳሌ በአማራ ክልል በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ለህጻናት ማስተማር ቢጀመር ሁለት የባእዳን ፊደል ይጫንባቸዋል።አንደኛ የእንግሊዝኛ ፊደል አለ ሁለተኛ የላቲን ፊደል አለ ሦስተኛ አማርኛ ራሱ አለ።ነገርግን በላቲን galatoomaa  ብለው ከሚጽፉት በራሳቸው ፊደል “ገለቶማ” ብለው ቢጽፉ ይቀላል፤የሀገራቸውን ቋንቋ በራሳቸው ፊደል መጻፋቸው በራሱ በማንነታቸው እንዲኮሩ ያደርጋል።

ይኼን ለማድረግ በኦሮሚያ ክልል የግድ ከአንደኛ ክፍል ጀምሮ የግእዝ ፊደል መሰጠት አለበት።በአማርኛ ህጻናት መማር አለባቸው።በተመሳሳይ በሌሎች አካባቢዎች ኦሮሞኛ ቋንቋ በግእዝ ፊደል ቢሰጥ ችግር የለውም።ሦስት አራት ቋንቋ ማወቁ ክፋት የለውም።ክፋቱ በባእዳን ቋንቋ ጻፉ የሚሉት ነገር ነው።የኦነግ ርዝራዦች ከግእዝ ፊደል የላቲን ፊደል በለጠባቸው።እንዲያውም ማድረግ የነበረባቸው የላቲን ፊደል አስወግደው ኦሮሞኛ ቋንቋ በግእዝ ፊደል እንዲተካና ቋንቋው በሁሉም ዘንድ እንዲለመድ መታገል ነበረ።

Filed in: Amharic