>

ሁሌም "ለአዲስ አበቤ ፍትህ ይውረድ" የሚለው ናቲ ፍትህ ተነፍጓል ለእስርም ተዳርጓል...!

ሁሌም “ለአዲስ አበቤ ፍትህ ይውረድ” የሚለው ናቲ ፍትህ ተነፍጓል ለእስርም ተዳርጓል…!

መስከረም አበራ


ናትናኤል ያለም ዘውድ Natnael Ye  ህወሃት መራሹን እና ኦሮሞ ብልፅግና መራሹን አንባገነን መንግስት ያለ አንዳች ፍርሃት በመታገሉ በሁለቱም መንግስታት የወጣትነት ዘመኑን በእስር ቤት እንዲያሳልፍ ሆኗል ። የመጣ እስር አያልፈውም፣እሱም አይበገርም! “እታሰር ይሆን” ብሎ የሚቆጥበው ትግል የለም። የታሰረ ይጠይቃል፣ጠበቃ ላጣ ጠበቃ ያቆማል ለተገፉት ይጮሃል፣ፍትሃዊ ያልመሰለውን ነገር ሁሉ ይሞግታል። በዚህ ላይ ይህችን መከረኛ ባንዲራ የሚወድ የአዲስ አበባ ልጅ ነውና የመጣ የሄጀው ያስረዋል!

የሚታሰር የሚፈታለት ህዝብ ናቲንና ውለታውን ምን ያህል ያውቀዋል?የሚለው የእኔ ጥያቄ ነው። ማን አላላውስ እንዳለው የሚያውቀው አፋኙ መንግስን ግን  እንደ እጁ መዳፍ ያውቀዋልና እስር ቤት ያመላልሰዋል። ናቲ ‘ለአዲስ አበቤ ፍትህ ይውረድ’ እያለ ሞት ሳይፈራ የሚሟገት፣የሚጋፈጥ፣ሰው የረሳውን እስረኛ ሁሉ እየዞረ የሚጠይቅ ፣እስረኛ ቤተሰብ  የሚያፅናና የልጅ አዋቂ ነው።

ዛሬ ጠዋት አውርተን ነበር፣አሁን ታሰረ ስባል ብሽቀት የተቀላቀለበት ሃዘን ተሰምቶኛል። የት እንደታሰረ እንኳን የሚታወቅ ነገር የለም። ስለሚታገሉልን ሰዎች ስቃይ ግድ ሊለን ይገባል።የሚታገለው ለህዝብ ነውና  በህዝብ ድምፅ “ናቲ የት ነው?ለምን ታሰረ” ማለት አለብን! ካልሆነ ከፊት ሆኖ ትግላችንን የሚታገል አይኖርም!!!

Filed in: Amharic