>

ቤተ ክርስቲን "በእምነትና ሥርዓት ላይ እየተፈጸመ ያለው ሁከት ይወገድልኝ " ስትል ክስ መሰረተች   ...

ቤተ ክርስቲን “በእምነትና ሥርዓት ላይ እየተፈጸመ ያለው ሁከት ይወገድልኝ ” ስትል ክስ መሰረተች   …

ለጠቅላይ አቃቤ ሕግ ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ

አዲስ አበባ

ጉዳዩ፡- በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲን እምነትና ሥርዓት ላይ እየተፈጸመ ያለው ሁከት ቀስቃሽ ድርጊት በሕግና በሥርዓት እልባት እንዲያገኝ የቀረበ አቤቱታ ነው ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አንዲት ኩላዊት ሉዓላዊት፣ ብሔራዊት እና ዓለምአቀፋዊ ሆና የይሦስት ሺህ ዘመናት በላይ የታሪክ ባለቤት ከመሆን አልፋ ለሀገራችን ኢትዮጵያ ቀለም በጥብ ብራና ዳምጣ፣ ብዕር ቀርና ፊደል ጽፋ ለሀገራች የሥነ ጽሑፍ ታሪክ መሠረት በማስቀመጥ ትምህርትን ለትውልድ በማስተላለፍ የራሷ የሆነ ፊደልና የመን አቆጣጠር እንዲኖራት በማድረግ ኢያቡ የሆነ፤ ለዘመናት የሚወሳ ልዩ ልዩ ታሪክን በማስቀመጥ የሀገር ባለውለታ በመሆን ብዙ ዋጋ ከፍላለች፣ እሁንም እየከፈለች ትገኛለች።

ይህ ሆኖ ሳለ አንዳንድ የቤተ እምነት አስተማሪዎች የቤተ ክርስቲያናችንን የዘመናት ውለታ በንግተው ያለ ስሟ ስም በመስጠት ማብጠልጠል፣ ማንኳሰስ እና ማጠልሸት እንዲሁም ሁከት ቀስቃሽ የሆነ ድርጊቶችን መፈጸምን ሥራዬ ብለው ማከናወን ከጀመሩ ውሎ አድሯል፡

ይሁን እንጅ ቤተ ክርስቲያናችን ይህንን ድርጊት ለሀገራዊ ሰላምና ደህንነት ለህዝቦቿ አንድነት እና ክብር ስትል እይታ እንዳላየች፣ ሰምታ እንዳልሰማች ማለፏን አምኖ እንደመቀበል ቆጥረውታል፡፡

በመሆኑም እነዚህ አካላት ሰላም እና መከባበርን በሚንድ ዓላማ ላይ በመመስረት በቤተ እምነቶች እና በሃይማኖት ተቋማት መካከል የሥም ማጥፋት ጥላቻን በመዝራት ባለመቻቻል ሁከት እና ብጥብጥ እንዲንሰራፋ ሆን ብለው እየሠሩ የስትን ተግባር ተቋቁማ በዝምታ ማለፍ የማትችልበት ደረጃ ላይ ደርሳለች።

ስለዚህ የኢፌዴሪ ፍትሕ ሚኒስቴር ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የድርጊቱን የወንጀል ይዘት በአግባቡ በማጤንና በመመርመር የወንጀል ክስ በመመሥረት አስተማሪ የእርምት እርምጃ እንዲወስድ እና ውጤቱን እንዲያሳውቀን እያሳሰብን ሚኒስቴር መ/ቤቱ ችግሩ ወደ ከፍተኛ ደረጃ ከመድረሱ በፊት የጉዳዩን አሳሳቢነት በማጤን አስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጥልን ስንል በአጽንኦት እንጠይቃለን።

Filed in: Amharic