>

ብልፅግና የተከበረውን የኦሮሞ ማንነት ወደ አፀያፊ ማንነት አውርዶታል ! (ድምፃዊ ጃንቦ ጆቴ)

ብልፅግና የተከበረውን የኦሮሞ ማንነት ወደ አፀያፊ ማንነት አውርዶታል !

ድምፃዊ ጃንቦ ጆቴ

 


ብልፅግና ኦሮሞነትን ወደ አፀያፊ ማንነት ባይቀይረዉ ኖሮ ኦሮምኛ አምጡ ተብላችሁ የምታስተምሩት ቋንቋ ይሆን ነበር።

በዚህ ዘመን ሰዉ ከፍሎ እንግሊዘኛ ይማራል፣ ፈረንሳይኛን ለመማስተማር ለልጁ አሰጠኝ የሚቀጥር ወላጅ አለ፣ ጀርመንኛንና አረብኛን አቀላጥፎ ለመናገር የሚፈልገዉ ወጣት በርካታ ነዉ።

ቻይንኛን መናገር ትልቅ የአስተርጓሚነት የስራ እድል የሆነባት መዲና ናት ሰዉ ግን ኦሮሚኛን ማወቅ ይፀየፋል። ባህሉንም ላለመዉረስ ያምፃል።  ምክንያቱ  ግልፅ ነዉ! ብልፅግናዎች ኦሮሞነትን ወደ አፀያፊ ማንነት ቀይራችሁታል።

በናንተ ዘመን ኦሮሞነትን ሁሉን ልብላ ባይ ስግብግብነት አርጋችሁታል።   አለም አቀፍ ከተማን ኬኛ ብላችኋል

ሚዲያችሁን ጥላቻ መትፊያ ተቋም አርጋችሁታል።

ፍቅር ሰባኪ ኦሮሞን ከሚዲያችሁ ነቅላችኋል

ሰዉ ከኦሮሞ ጋር እንዳይደሰት ለኢሬቻ ተሳደባችሁ፣

ሰዉ ከኦሮሞ ጋር እንዳያዝን በሀጫሉ ሞት ንፁሀንን አሳረዳችሁ።

ዛሬ ሰዉ ኦሮሞነትን ጠላ፣ ቋንቋዉን ተፀየፈ፣ ባህሉን ሸሸ።

ሰዉን የኔን ቋንቋና ባህል ዉሰድ ብሎ ከማስገደድ በፊት እኔ ኦሮሞነትን ምን አርጌ ፃፍኩት ብሎ መጠየቅ ተገቢ ነዉ።

በቋንቋዉ ፍቅርን ስበኩበት፣ በባህሉ መተቃቀፍን አስተምሩበት፣በስልጣናችሁ ሰዉ ማረድ ትታችሁ አራጅን ቅጡበት፣ በሚዲያችሁ ኬኛ እያሉ ማላዘንን ተዉና! የሁላችን ብላችሁ ፍቅርን ዝሩ።

ወጣቶቻቻችሁን የጥላቻ ሀዉልት ገንቢና የድል ሀዉልት አፍራሽ ደናቁርት አታርጓቸዉ።

  ያንግዜ ኦሮሞነት በአጣና የምታስተምሩት ሳይሆን አምጡ ተብላችሁ የምትሰጡት፣ የታለ ተብላችሁ የምታሳዩት ተፈላጊ ማንነት ታረጉታላችሁ።

Filed in: Amharic