>

ዜና ምሥራቅ ወለጋ - ኪረሙ ወረዳ (ዘመድኩን በቀለ)

ዜና ምሥራቅ ወለጋ

ኪረሙ ወረዳ

ዘመድኩን በቀለ

“…ከተለያዩ አቅጣጫዎች የተነሣ የኦሮሚያ ልዩኃይል፣ ኦነግ ሸኔ፣ የኦሮሞ ሚሊሻ እና ጋቸና ሲርና ኪረሙ ወረዳ ላይ ሲከማች ሰነበተ። መሸ ነገ በሁለተኛው ቀን ማለትም ዛሬ በተለያየ አቅጣጫ ሃሮ አዲስ ዓለም በርካታ የዐማራ ተፈናቃዮች ያሉበትን ከተማ ከንጋቱ 1:00 ሰዓት ሲሆን ከበቡ።

“…በምሥራቅ በኩል አጋምሳ የምትባል ከተማ አለች። በእሷ በኩል ኦነግሼኔና የኦሮሞ ልዩኃይል አንድ ላይ፣ በሰሜን በኩል ኦነግሸኔ፣ የኦሮሞ ልዩኃይልና ሚሊሻ፣ በደቡብ በኩል ጋቸና ሲርና፣ ኦነግ ሸኔና በዚያ አካባቢ የሚኖር የኦሮሞ ሕዝብ እና ዘራፊው ቄሮ በተመሳሳይ ስዓት የዐማራን ገበሬ ከበው ውጊያ ጀመሩ።

“…የዐማራ ገበሬዎችም ቀደም ብለው በሥነ ሥርዓት በጨዋ ደንብ ነቀምት አካባቢ ላሉ የመከላከያ አመራሮች ህዝባችን ጭፍጨፋ እየተፈጸመበት ነው። ድረሱልን ብለን ይጠይቃሉ። መከላከያም መልሶ ለዐማሮቹ እኛ መድረስ አንችልም። ራሳቹህን አድኑ። እናዝናለን እኛ ምንም ማድረግ አንችልም ይሏቸዋል። ወጉ እንዳይቀር ነው እንጂ፣ አልነገራችሁንም እንዳትሉ ነው እንጂ እኛ ፊትም ቢሆን ከእናንተ ተስፋ የለንም ብለው ራስን በራስ ወደ ማዳን ተፈጥሯዊ መብታቸው ገቡ።

“…4000 ሺ ኃይል ነው የፈሰሰው። ዐማራም ራሱን መከላከል ጀመረ። ውኃ መራጨት ስላልሆነ በመከላከል ላይም ዋጋ እየተከፈለ መመከት ጀመረ። የመጣው ወራሪም እንደጠበቀው አልሆን አለው። ዐማራውም የሚከፈለውን ዋጋ ለአምጪው እንዲከፈል ሕግ ያዛል እና መልሶ ያስከፍለው ጀመር። የተተኮሰ ጥይት መሬት ላይ አይወድቅም።

“…ተከላካዩ ዐማራ የመረረው፣ ከሁለት ዐመት በፊት የተዘረፈ፣ ሞትን በፀጋ ለመቀበል የቆረጠ ነው። ቤታችን፣ ንብረታቺን እንዳይል አስቀድመው ዘርፈውታል። ራሳን ለማደን፣ በሕይወት የመኖር መብትን ለማስጠበቅ ደግሞ አንፈራም። ይምጣ ጥለነው እንወድቃለን አንለቀውም ብሎ የዐማራ ገበሬ መፋለም ጀመረ። ደግሞ ጥሎባቸው ሃሮ አዲስ ዓለም ለጠላት አትመችም። ታቦቱ ተቦተ ቅዱስ ጊዮርጊስ ነው። ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማእታት፣ የዓድዋው ዘማች ተዋጊ ነው።

“…እናም አሁንም ውጊያው እንደቀጠለ ነው። ጠላትም እየረገፈ ነው። እስካሁን ባለው ውጊያ ከጠላት ወገን ከ170  በላይ አስከሬን ቆጥረናል። አዋጊው ወይም አዛዡ ከነመገናኛው ሬዲዮው የዐማራ ገበሬዎቹ እጅ ውስጥ ገብቷል። የሸዋው የተዋነይ ጥበብ ሠርቷል።

አሁንም ከባዲ ውጊያ ላይ ናቸው። በጸሎት አስቡን ብለዋል።

“…እስከአሁን ያለው መረጃ ይሄ ነው። መሣሪያ ከነተተኳሹ ከበቂ በላይ ተገኝቷል። ውጊያው ይቀጥላል። ጥሎ መውደቅ ሳይሆን ጥሎ ማለፍም ይጀመራል። የሚመጣው ዐማራ ተናግሬአለሁ። በደም የሰከረ፣ የቀወሰ፣ በበቀል የተጠመቀ፣ ማንንም የማይምር፣ ዘሩ የተጨፈጨፈበት፣ የመኖር ትርጉሙ የጠፋበት፣ ሕግም፣ መንግሥትም እንደማያድነው ያወቀ፣ የጳጳስ ግዝት፣ የሼክ ቁጣ፣ የሽማግሌ ተግሳጽ፣ የሰባኪ ስብከት አይመልሰውም። ተናገርኩ።

“…የወለጋ ዐማራ ሟች መሆኑን ቁርጡን ዐውቆ ወጥሮ እየተዋደቀ ነው። ለልቅሶ፣ ለኢየዬ ጊዜ የለውም። የቴሌና የብሔራዊ መረጃ አገልግሎት ወፎቼ የአቶ አገኘሁ ተሻገር እና አንድ የወለጋ ዐማራ ያወሩትን የስልክ ምልልስ አድርሰውኝ አድምጬው ነበር። “ከዐማራ ክልል ውጪ ስላላችሁ ዐማሮች አያገባንም ሲሉት ሰምቼ መብረቅ እንደመታው ሰው ነው አናቴ ለሁለት ተከፍሎ የቀረው። የአዲስ አበባ ዐማራም ቁርጥህን ዕወቅ።

• ለወለጋ ዐማራ ያለኝን ክብር ቆሜ በጭጨባ እገልጻለሁ።

Filed in: Amharic