>

ችሎት ሳይገባ ችሎት በመድፈር የተፈረደበት ጠበቃ ወንድሙ ኢብሳ...!" (ብዙአየሁ ወንድሙ ፈይሳ)

ችሎት ሳይገባ ችሎት በመድፈር የተፈረደበት ጠበቃ ወንድሙ ኢብሳ…!”

    ብዙአየሁ ወንድሙ ፈይሳ

ዘንድሮም አብዮት ልጇን  በላች…!


ከአቶ ወንድሙ አፍ የሰማነው እንዲህ የሚል ነው።ወደ ፍ/ቤቱ ግቢ ስገባ አንድ ሰላምተኛዬ የነበረ ዳኛ ጋር ተገናኘን። እስከዛሬ ለኦሮሞ እታገላለሁ ስትል ቆይተህ እንዴት ለአማራ ትጮሃለህ።ያሳዝናል ብሎ ከእኔ ምንም መልስ ሳይጠብቅ በንዴት እየተወራጨ ጥሎኝ ሄደ።ምንም መልስ አልሰጠሁትም ። ሁለት ቀጠሮ ነበረኝ።የመጀመሪያውን ቀጠሮ ተራ ደርሶኝ ተጠራን ጨርሼ ወጣሁ።ሁለተኛው መዝገብ እስኪጠራ ከችሎት ወጥቼ ራቅ ብዬ መጽሐፍ እያነበብኩ ነበር።

የፍ/ቤቱ ፕሬዝደንት መጥቶ ለምን አትቀመጥም አለኝ ። ስለቆምኩ አዝኖልኝ ነበር የመሰለኝ።መቀመጫው ተይዟል ።እስክጠራ እዚሁ ቆሜ ባነብ ይሻለኛል አልኩት። ዝም ብሎኝ ሄደ።ከዚህ ወጭ ክፉም ደግም አልተነጋገርንም ። ከአምስት ደቂቃ በኃላ ፖሊስ መጥቶ ከአሁን ጊዜ ጀምሮ እስረኛ ነህ አለኝ።ምን አጠፋሁ ?አልኩት።ምንም መልስ ሳይሰጠኝ ወደ እስረኛ ማቆያ ቦታ እንድሄድ ነገረኝ።

ዝም ብዬ ሄድኩኝ።ምንም ሳልናገር በትግስት ቁጭ አልኩ።ከሁለት ሰዓት ቆይታ በኋላ ፖሊሱ ችሎት ትጠራለህ አለኝ።ችሎት ገብቼ ቆምኩ።ችሎት በድፈር አራት ወር ተፈርዶብሃል።ጨርሰናል አስወጡ ብለው አዘዙ።ፖሊስ ገፍቶ አስወጣኝ።

የትኛውን ችሎት ምን አድርጌ እንደደፈርኩ ሳይገለጽ ወስነናል አሉኝ። ሂደቱ እጅግ የሚገርምም የሚያስቅም ነው።ብለዋል ።

እንድታሰር ዋናው ምክንያት አ.አ ት/ቤቶች የሚሰቀለው የኦሮሚያ ባንዲራ እና በግዳጅ እንዲዘመር ስለታዘዘው የኦሮሚያ መዝሙር ተቃውም በማቅረቤ እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል ስለተፈጸመው ህገወጥ እስር በማውገዜ ይመስለኛል ብሏል።

Filed in: Amharic