>

የከሸፉት የብልጽግና መንግስት ስብሰባዎች ..! (ግርማ ካሳ)

የከሸፉት የብልጽግና መንግስት ስብሰባዎች ..!

ግርማ ካሳ

የብልጽግና መንግስት ስብሰባ በስብሰባ ላይ ነው፡፡ ነገር ደግሞ በአማራ ክልል ከዞን፣ ወረዳ የመጡ ከ3500 በላይ የብልጽግ ና መንግስት ታችኛውና ላይኛው አመራሮች በባህር ድር ይሰበሰባሉ እየተባለ ነው፡፡

እስከአሁን የተደረጉት ስብሰባዎች በዋናነት የከሸፉ ነበሩ፡፡ ይሄም የከሸፈ ስብሰባ ነው የሚሆነው፡፡ ስብሰባው እንደሌሎቹ ስብሰባ ዝግ ቢሆን፣ የሌሎች ስብሰባዎች መረጃዎች እንደወጡት የዚህም ስብሰባ መረጃ ይወጣል፡፡

ስብሰባው የሚከሽፍበት ዋና ምክንያቶቹ ሁለት ናቸው፡፡

አንደኛው ስብሰባ ፍትህዋኢ፣ ዴሞክራሲይዊ አይደለም፡፡ እነ ዶር አብይ ከላይ የወሰኑት ሌሎች እንዲቀበሉ ለማስገደድ፣ ለምጥመቅ የሚደረግ ስብሰባ እንጂ፣ ታች ካሉ አባላቶቻችን ምን ግባት እንውሰድ ብለው፣ በእርሱ በኩል ህዝብን የሚለውምን ለማዳመጥ የማይፈለግበት ስብሰባ በመሆኑ ነው፡፡

ሁለተኛው፣ በድርጅቱ ያሉ  ስር የሰደዱ ከማንነት፣ ከዘር ጋር የተገናኙ ልዩነቶች ማስታረቅ ስለማይቻል ነው፡፡ በድርጅቱ ውስጥ ዘይትና ውሃ የሆኑ አብረው ሊሰሩ የማይችሉ አካላት በመካተታቸው ነው፡፡ ሕወሃት ላይ ያላቸው አቋም አንድ አደረጋቸው እንጂ ብ አዴኖችና ኦህዴዶች አንድ አይደሉም፡፡ እንደው በአስተሳሰብ ኦህዴድ የሚቀርበው ከህወሃት ጋር ነው ስንል ነበር፡፡ ለዚህም ነው ይኸው አሁን የሰሜኑ ጦርነት ለትንሽ ጊዜ ጋብ ሲል። ኦህዴዶች ከህወሃት ጋር ታርቀው ሽር ጉድ እያሉ ያሉት፡፡

የዶር አብይ አህመ ድከፍተኛ የብልጽግና አመራር፣ ዘይትና ውሃ ሆኖ መቀጠል አይችልም፡፡ስምምነትን ማምጣት አይችልም፡፡ ወይ ዉሃ ፣ አሊያም ዘይት ሲሆን ነው በድርጅቱ ውስጥ አንድነትን መፍጥር የሚቻለው፡፡ የብልጽግና መንግስት ወይም አንደኝዐው የፌዴራሊስት ኃይሎች ነን ከሚሉ ከነ ኦፌኮ፣ ህወሃት ጋር ጥምረት ይፍጠርና ይለይለት፡፡ አሊያም የዘር ፖለቲካ ቡትቶዉን ጥሎ በይፋ በድፍረት የዜግነት  ፖለቲካ በማራመድ፣ አገርን ከዘር ፖለቲካ ለማውጣት፣ ድፍረቱ ይኑረው፡፡

በነገው ስብሰባ ፣ ምንአልባት የተወሰኑ ክፍተቶች ከታዩ ፣ አባላት ድፍረት አግኘተው ከፍተኛ አመራሩን ቻሌንጅ ማድረግ መቻል አለባቸው፡፡ ባመረረ መልኩ የህዝቡ ብሶት ለከፍተኛ አመራሩ ማሳወቅ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ባመረረ መልኩ፡፡ የነርሱ ዝምታ ነው፣ ከፍተኛ አመራሮ በህዝቡ ላይ እንዲቀልድ ያደረገው፡፡

ስብሰባዎች እየደጋገሙ ማድረግ ፋይዳ የለውም፡፡ ስብሰባዎች መሰረታዊ ለውጥ እንዲመጣ ካላደረጉ፡፡

Filed in: Amharic