>

የባህርዳሩ ስብሰባ...!  (ዘመድኩን በቀለ)

የባህርዳሩ ስብሰባ…!

ዘመድኩን በቀለ


*…. “…አንተ አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ በክልልህ ይሄ ሁላ ግፍ እየተፈጸመ፣ ሰው እየታረደ፣ በእሳት እየተቃጠለ፣ ሚሊዮኖች እየተፈናቀሉ ለምንድነው እስከአሁን ሥልጣን ላይ የተቀመጥከው? ለምን አንተም ካቢኔህም ሥልጣን አትለቁም። እናንተ ሃገር መምራት አትችሉም። ልክ እንደ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ መልቀቂያ አስገባ። ህዝባችንን አታስጨርስ…!

“…በዐማራ ክልል ከሁሉም ወረዳዎችና ዞኖች የተውጣጡ ኮር አመራሮች የሚባሉት 3 ሰዎች ማለትም ዋና ሓላፊው፣ ምክትሉና ዋና ጸሐፊው፣ የዞን አመራር፣ የወረዳ እና የክልሉ አመራር በሙሉ፣ የፓርላማ አባላቱም በክልሉ ምክርቤት አዳራሽ ተሰብስበዋል።

 

“…ስብሰባው የተጠራው ቀደም ሲል በአዲስ አበባ በኦሮሚያ ብልጽግና እና በዐማራ ብልፅግና መካከል የተፈጠረውን ክፍተት ለመድፈንና ቅሬታ የገባውን የዐማራ ብልፅግና አመራሮች (ኮንቪንስና ኮንፍዩዝ) ለማድረግ ነበር። ስብሰባው በቲቲ ይቅርታ፣ በቦቢ፣ ኦፋ ምንድነው በፖፖ ኧረ ምን መሆኔ ነው? በፒፒ ምክትል ፕሬዘዳንት በኦሮሞ ሱማሌው አቶ አደም ፋራህ ነበር የተከፈተው። ከአደም ቀጥሎ ዶር ይልቃል የመግቢያ ንግግር አደረጉና አደም፣ ይልቃልና የአደምም፣ የይልቃልም ስውር አለቃ ሽመልስ አብዲሳ ወደ መድረኩ ወጡ። በዐማራ ሞት ጮቤ ረጋጩ ጴንጤው ታገሰ ጫፎና አረቄያሙ የፓርቲ ብር ሌባው አገኘው ተሻገርም በታዛቢነት በስብሰባው ተገኝተዋል።

“…የስብሰባው አጀንዳ የነበረው በሃገሪቱ ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ ነው። ለዛሬ ከመድረክ የምናቀርበው ነገር የለም። መስማት የምንፈልገው ከእናንተ ከአመራሮቹ ነው በማለት አመራሩ ጥያቄ እንዲያነሳ እድል በመስጠት ነበር የተጀመረው። አመራሩም በታሪክ በብአዴንም፣ አሁንም በፒፒ ጊዜም ታይቶ በማያውቅ ሁኔታ ዝም፣ ጭጭ፣ ነበር ያሉት። የዐማራ ዝምታ ደግሞ ያስፈራል። ብአዴን ቢሆኑም ሰዎች ናቸው። ዘራቸው እየጠፋ ያሉ ሰዎች። ቤተሰብ ዘመዱ እየታረደ ያሉ ሰዎች እናም ዝምታው በረታ። ዝምታ ደግሞ አደገኛ ነገር ነው።

“…ከብዙ ዝምታ በኋላ በአደራሹ ዝምታው ይሰበር ጀመር። በተለይ ከሙሉ ወሎ ከዋግ ኽምራ፣ ከላስታ፣ ከራያ፣ ከሰሜን ወሎ፣ ከደቡብ ወሎ፣ ከኮምቦልቻና ደሴ፣ ከሙሉ ሸዋ…ከጎንደርም በከፊል፣ ከጎጃም በጥቂቱ ጥያቄ ይጎርፍ ጀመር። ይኽን የምላችሁ ለመከፋፈል አይደለም። የሆነውን እውነታ ነው።

በወያኔ በደንብ የተወቀጡት ቀውጠዋል። ወሎ፣ ሸዋ፣ ጎንደር በየደረጃቸው እሪሪ ነው ያሉት። ጎጃሞች የወያኔ ዱላ ስላላረፈባቸው እንደ ወሎና ሸዋ እሪሪ ባይሉም በጥያቄ ወቅት ግን ከቤቱ የተለየ ነገር አላንፀባረቁም። ባገኙት ዕድል ተጠቅመው ዐማራ አንድ መሆኑን አሳይተዋል። በመተከል እና በወለጋ የሚታረደው፣ አዲስ አበባ ለመግባት በሰው 1ሚልዮን ብር የሚከፍለው እኮ የጎጃም ዐማራው ነው። በጦርነቱ ወሎ ላይና ጎንደር ያለቀውም የጎጃም ሚኒሻም ነው። ጎጃም ቀጥተኛ የወያኔ ዱላ እንደሌሎቹ ባያርፍበትም ያው ቀምሷል። ከተሰብሳቢዎቹ በዋነኝነት በጠንካራ ሁኔታ የቀረቡት ጥያቄዎች በአዲስ አበባና በሂዊ ኦህዴድ መካከል ስለተፈጸሙት  ስምምነትቶች ነበር።

“…አንተ አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ በክልልህ ይሄ ሁላ ግፍ እየተፈጸመ፣ ሰው እየታረደ፣ በእሳት እየተቃጠለ፣ ሚሊዮኖች እየተፈናቀሉ ለምንድነው እስከአሁን ሥልጣን ላይ የተቀመጥከው? ለምን አንተም ካቢኔህም ሥልጣን አትለቁም። እናንተ ሃገር መምራት አትችሉም። ልክ እንደ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ መልቀቂያ አስገባ። ህዝባችንን አታስጨርስ። ደግሞስ የጎጃም አዲስ አበባ መንገድ እና የወሎ ሸዋ አዲስ አበባ መንገድ የምትዘጋው ለምንድነው? የኦሮሞ ሪፐብሊክ አጀንዳን ለማስፈጸም እንደምትደክም እናውቃለን። ነገር ግን እሱ ህልም ነው አይሳካም። በአስቸኳይ አቁሙ። ሽሜ አንገቱን ደፍቶ ዝም።

“…በአዲስ አበባ የኦሮሚያን ባንዲራ መስቀል፣ መዝሙር…

“…በአዲስ አበባ የኦሮሚያን ባንዲራ መስቀል፣ መዝሙር ዘምሩ ማለት ምን ማለት ነው? አዲስ አበባ የኦሮሞ ናት የሚለውን ትርክት ለማጽናት ነው የተፈለገው? አሁን የአዲስ አበባ አመራር የእናንተን ጉዳይ አስፈፃሚ አመራር በዐማራ ታርጋ ብቻ እንደምትሾሙ እናውቃለን። ይሄ ነውር ነው። በአስቸኳይ ይስተካከል።

“… ጫን ያለው አሁን ነው የመጣው። ከወሎ እና ከሸዋ የመጡት ቀወጡት። ስሙ ስምምነት፣ ስምምነት ትላላችሁ? የምን ስምምነት ነው? ስትጣሉ ሰብስባችሁ ተዋጉ እንዳላችሁት ስትታረቁ እኛ ማወቅ የለብንም? በትግሬ የደረሰብን በደልስ? የተደፈረችው እናቴ፣ የታረዱት ቤተሰቦቼስ? ትግሬ ከዐማራ ዘርፎ የወሰደውን ንብረት ሳናስመልስ የምን ስምምነት ነው? እናንተ አፋርና ዐማራን የወደመ ንብረት ባላየ እያለፋችሁ ደንታ ሳይሰጣችሁ አሁን እየቧቸራችሁ ያላችሁት ትግራይን መልሶ ለማቋቋም ነው።  ይሄ ነውር፣ ወንጀልም ነው።

“…የጎንደር ዐማራ ጠያቂ አመራር እሳት ለብሶ እሳት ጎርሶ ተነሣ። አረቄ ጠግቦ አድሮ ጋንጋን ወደ ሚሸተው፣ ከንፈሩን በምላሱ አስር ጊዜ በሚልሰው በአቶ አገሁ ተሻገር ላይ ያወርደው ጀመር። አንተ አቶ አገኘሁ በጦርነቱ ጊዜ የወልቃይት ጉዳይ የተዘጋ ነው፣ ስለ ወልቃይት የሚነሣ ከሆነ ሽጉጤን እጠጣለሁ ስትል ከርመህ አሁን ወደ ፌደራል ተዛውረህ ፌደሬሽን ምክርቤት ሰብሳቢ ስትሆን ምንነው ካድክ? (አረቄና ሽጉጥ ተማታቶበት እኮ ነው)

“…መልሱልን በወለጋ ለሚታረደው ዐማራ ተጠያቂው ማነው? እንደግመዋለን አቶ ሽመልስ አብዲሰ ክልልህን መምራት አልቻልክም እና በአስቸኳይ ልቀቅ። ስምምነት የምትሉትንም ቢሆን እንደ ዐማራ አልተወከልንበትም። አናውቀውምም። እኛ እየተራብን፣ እየተገደልን ስለ ሌላው የምናስብበት የምንጨነቅበትም ምክንያትም ጊዜም የለንም።…

የምንመራው ህዝብ ተርቧል። ደህይቷል። በትግሬ ጥጋብ ወድመናል። ዐማራ ይሻገረዋል እንጂ ለከፋ ችግር ነው የተጋለጠው። አፋርና ዐማራን ዘላችሁ አሁን ከትግሬ ጋር የምትፈጽሙትን እያየን ነው። ሰው ይታዘበናል፣ ሃገርስ ምን ይለናል አትሉም እንዴ? ያለ ፍትህ እንዴት ያለ ሰላም ለማምጣት ነው እየጣራችሁ ያላችሁት? ዝም ስንል፣ ስንታገስ አንደኛውኑ ደንቆሮ፣ መሃይም አድርጋችሁ ነው እንዴ የምታዩን?

“…አዲስ አበባም የብሔር ብሔረሰቦች ሁሉ ማዕከል፣ ሃብትም ናት። ባለቤቷም የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ሁሉ ናቸው። አዲስ አበባን የአንድ የኦሮሞ ብቻ ለማድረግ የምትሰሩትን ተግባር በአስቸኳይ አቁሙ። ከዚያ በፊት ግን ሃገር ወደ ከፋ ውድቀት ከማምራቷ በፊት እናንተ አመራሮች ሃገሪቷን መምራት አልቻላችሁም እና በአስቸኳይ እንደ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ሥልጣን ልቀቁ። ኢትዮጵያን ለማትረፍ ግማሽ ርቀት የሚወስደን ይሄን ያደረጋችሁ እንደሆነ ነው በማለት በርካታ ጥያቄዎችን ተሰብሳቢው ዐማራ በጋለ ዐማራዊ ወኔ በመጠየቅ የአቶ ሽመልስን ፊት ጉልበቱ ላይ እስኪዘፈዘፍ ድረስ አስታጥቀውት ስብሰባው ለትናንት በዚህ መልኩ ተጠናቋል።

“…ከመድረክ ምንም ዓይነት ምላሽ ያልተሰጠ ሲሆን ዛሬ ከ8 ሰዓት ጀምሮ ትናንት ከመድረኩ ለተነሡ ጥያቄዎች በሙሉ ምላሽ ሊሠጥ ይችላል ተብሎ ይጠበቃል። የዛሬውንም ምላሽ ወፌ እዚያው ስለሆነች  መረጃውን እንዳደረሰችኝ ለእናንተ አቀርብላችኋለሁ።

…ሲጠቃለል፦ የትናንቱ የባህርዳር ስብሰባ ዐማራ አንድ ሁኖ የታየበት ስብሰባ መሆኑን ነው ታማኟ ወፌ የነገረችኝ። ዐማራ ክርስቲያን እስላም ሳይል፣ ጎንደር ጎጃም፣ ወሎ ሸዋ ብሎ በጎጥ ሳይከፋፈል። እንደ አንድ ልብ መካሪ፣ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ሆነው በዐማራዊ ወኔና ጀግንነት፣ ለሽመልስ ሳያጎበድዱ በድፍረት፣ በኃይልና በሥልጣን ሲሞግቱ ነው የዋሉት። ደግሞም ግዴታቸውም ነው። ከዚህ ውጪም ሌላ አማራጭ የላቸውም። ዐማራን ውሽልሽል ካቢኔ አያድነውም። ዐማራን የሚያድነው ዐማራነቱና እንዲህ ነቅቶ የፖለቲካ እና ኅልውናውን ለይቶ አንድነቱ ላይ አተኩሮ ከነፍጡ ጋር የተነሣ እንደሆን ብቻ ነው። ያኔ አይደለም ለራሱ ለምሥራቅ አፍሪካም ይተርፋል።

“…ምንአልባት በዛሬው ከሰዓት ስብሰባ መዝጊያ ዐቢይ አሕመድ እንደ እርጎ ዝንብ ዘው ብሎ ሊመጣ ይችላል ብለው የሚሰጉ አሉ። እጅእጅ ባለው ቅርሻት ስብከቱ ዐማራን ዳግም ሊሸውድ፣ ኮንቪንስና ኮንፊዩዝድም ሊያደርግ የሚችል ግን አይመስለኝም። እንደኔ እንደኔ ዐማራ አሁን አመራሮቹን ቀርቦ ማገዝ ያለበት ጊዜ ነው ባይ ነኝ። ብአዴንን በመስደብና በመግደል ነፃነቱን አታገኙምም ባይ ነኝ። በንስሀ አባት፣ በኡስታዝ በሼክ፣ በቤተዘመድ፣ በጓደኛ በዕድር፣ በእቁብ፣ በማኅበር ካቢኔዎቹን ቀርባችሁ ስለህልውናችሁ ብትወያዩ መልካም ነው።

“…ብአዴን ቢሆንም እኮ ግን ያው አብዛኛው ዐማራ ነው። ሰው ሁሌ ሞኝ ከሃዲም ሆኖ አይቀርም። እንደ ይሁዳ በክህደቱ ፀንቶ ታንቆ የሚሞት እንዳለ ሁሉ እንደ ቅዱስ ጴጥሮስም በድሎ በፍጹም ንስሐ የሚመለስም ይኖራልና ድከሙባቸው። የሚታረድ ቤተሰብ ያለው የዐማራ ካቢኔም እኮ የትየለሌ ነው። መክራችሁ፣ ዘክራችሁ እምቢ ብሎ ለጠላት የሚሠራ ከሆነ ግን ለራሱና ለቤተሰቡም ንገሩ። አስጠንቅቁ። አቃጣሪ ካቢኔ ግን ከዐማራም ከኢትዮጵያ ህልውና አይበልጥም። ኢትዮጵያን ያለ ሁሉ ከዐማራ ጎን የመቆሚያ ጊዜውም አሁን ነው። የበረኸኞቹ ትንቢትም ይፈጸም ዘንድ ዐቢይ የሚጠራቸው ነጮችም ኢትዮጵያ ሊገቡ ይመስላል።

አበቃሁ…!

Filed in: Amharic