>

የዐማራ ልዩ ኃይል መጨረሻ - በሴራ እየተረሸኑ በጅምላ መቀበር...!(መምህር ዘመድኩን በቀለ)

የዐማራ ልዩ ኃይል መጨረሻ – በሴራ እየተረሸኑ በጅምላ መቀበር…!

መምህር ዘመድኩን በቀለ

“…አሁን ይሄ እዚሁ ሰሜን ሸዋ ውስጥ የተረሸነ የዐማራ ልዩ ኃይል ነው ቢባል ማን ያምናል?ከወራት በፊት የዐማራ ሕዝብ ነበር እንዲህ በጅምላ የሚቀበረው። አሁን ከሕዝቡ ወደ ዐማራ ልዩ ኃይል ተሸጋግሯል። ከወልቃይት፣ ከራያ፣ እዚሁ ሰሜን ሸዋና ደቡብ ወሎ የሚገኘውን የዐማራ ልዩ ኃይል በአርቴፊሻል ጦርነት በኦነግ ሸኔ ስም ከፍተው በተኙበት፣ ባልተዘጋጁበት መረሸን ተጀምሯል። 

“…በዘር ኦሮሞና ቅማንት ነን የሚሉ የዐማራ ልዩ ኃይልን እንዲመሩና እንዲያዙ አድርገው፣ በየትኛውም የጦር ግንባር የማይማረክ፣ እጅ የማይሰጠውን በምንም ተአምር በዚህ መልኩ በጅምላ የማይረሸነውን የዐማራን ልዩኃይል በዚህ መልኩ እያስጨፈጨፉ ልክ እንደ ሕዝቡ በዶዘር ቆፍረው በጅምላ ይቀብሩት ጀምረዋል። 

“…ጎንደሮች ስለ ወልቃይት ብቻ ስለሚዘምሩ፣ ጎጃሞች ንግድ ላይ ስለሆኑ፣ ወሎዎች በራብና በጦርነት አጣብቂኝ ውስጥ እንዲገቡ ስለተደረጉ፣ የዐማራ እንዳይናበብ በብአዴን ስለከፋፈሉት የዐማራ ልዩ ኃይልን አጣዬና ከሚሴ በማምጣት በዚህ መልክ እየቀነሱት ይገኛሉ።

“…አሁን አሁን በእኔ በኩል ከነአካቴው ተስፋ ባልቆርጥም በጀግኖች ዐማሮች የምኮራውን ያህል በቸልተኛውና በማይነቃው፣ በወሬ ብቻ፣ በጉራ፣ በቀረርቶ እየፎከረ በሚኖረው ዐማራ እየበገንኩኝ ለዐማራው ማዘኑ እየደከመኝ መጥቷል። ይሄን ስል አዝናለሁ። 30 ዓመት ሙሉ ሥልጣን ላይ ለተጎለቱ በድን ብአዴኖች በብላሽና በፈቃደኝነት የሚሞት ሕዝብ ከዐማራ በቀር በየትኛውም ዓለም ላይ አላየሁም። ወዶ እና ፈቅዶ ለሚሞት ሰው ደግሞ ምን ብለህ ትጮህለታለህ? ያስቃል፣ ያስለቅሳል፣ ያሳቅቃልም።

“…እነዚህ እንዴት ተረሸኑ? ማን አስረሸናቸው? በቀጣይስ ምን ድነው የታቀደው?

ቀጥሎ ያለውን የመምህር ዘመድኩን በቀለን ገጽ በመክፈት ያንብ ቡ ። መረጃ ሙሉ ሰው ያደርጋል።

https://t.me/ZemedkunBekeleZ

• የተረሸኑትን ነፍስ ይማር…!

Filed in: Amharic