>

ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ውጪ የሚደረግን ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት አንቀበልም...! (የግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን )

ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ውጪ የሚደረግን ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት አንቀበልም…! 

የግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የአቋም መግለጫ 

ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ታዋድሮስ ዳግማዊ የመንበረ ማርቆስ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት፣ 

ጴጥሮስ አሸናፊ ከበደ

የእስክንድርያ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ አቡነ ሳዊሮስ በተባሉ ጳጳስ የተፈጠረውን ቤተ ክርስቲያንን የመክፈልና ራሳቸውን በኢትዮጵያ የኦሮሞ ክልል ፓትርያርክ አድርገው የመሠየም ተግባር ሙሉ ለሙሉ የማይቀበለው ፍጹም ሕግን የጣሰ መሆኑና እና በእሳቸው መሪነት ተሾሙ የተባሉ 26 ጳጳሳት የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ሕግ የጣሱ እንዲሁም መሠረት ያለውን እና ቋሚ የሆነን ከጥንት ጀምሮ በትውልዱ ሁሉ ሲተላለፍ ከመጣውን ከኦርቶዶክስ ቀኖና እና መመሪያ ሕገ ወጥ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የእስክንድርያ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ከሕጋዊው የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ዕውቅና ውጭ የሚደረግን ሢመት ዕውቅና አትሰጥም አትቀበልም።

ከዚህ በተጨማሪ ኮሚቴው (የውጭ ጉዳይ) ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጋር ያለውን ወዳጅነት እና አጋርነት እየገለጽን፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጳጳሳት፤ ሜትሮፖሊታን የሆናቸሁ ሁላችሁ ጥንታዊነት እና በታሪክ የበለጸገች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አንድነት እና ትሥሥር በፍቅርና በሰላም ሁናችሁ እንድትጠብቁ በጥብቅ አደራ እንላለን፡፡

የእስክንድርያ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ

አባ ቶማስ የቂሊያ ሜትፖሊታን እና የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ ዋና ጸሐፊ።

Filed in: Amharic