>

ደመቀ መኮንን፣ ደመላሽ ፍኖ እና ዳያስፖራ ፋኖ (መስፍን አረጋ)

ደመቀ መኮንን፣ ደመላሽ ፍኖ እና ዳያስፖራ ፋኖ  

ሸማ በየፈርጁ፣ ትግል በየደጁ ነው፡፡  ድል ደግሞ የትግሎች ሁሉ ድምር ውጤት ነው፡፡

ደመቀ መኮንን ለስሙ ያማራ ብልጽግና መሪ ነው፡፡  ያማራ ሕዝብ በታሪኩ አይቶት የማያውቀው መከራና ውርደት ሲደርስበት ግን፣ ይህ ያማራ መሪ ነኝ የሚል ግለሰብ ምን ተዳየ ብሎ እንዳይናገር፣ እንዳይጋገር አፉን ለጉሟል፡፡  የመሪነት ቦታውን ላማራ የሚቆረቆሩ ዶክተር አምባቸውን የመሰሉ ሰወች እንዳይዙት ደግሞ ግደሉኝ እንጅ አልለቅም በማለት ሙጥኝ ብሏል፡፡  የሱ በታቾች የሆኑት ያማራ ክልል ፕሬዚዳንቶች ደግሞ ከሕዝባቸው ጋር በቂ ትውውቅና መናበብ እንዳይኖራቸው ከጭራቅ አሕመድ ጋር እየተመሳጠረ በየ ስድስት ወሩ ይቀያይራቸዋል፡፡  ይህ አልበቃው ብሎት ደግሞ የክልሉ ፕሬዚዳንት እንዲሆኑ የሚያደርጋቸው እንደ ተመስግን ጡሩንህ ጃንደረባ፣ እንደ አግኘሁ ተሻገር ሰካራም፣ ወይም እንደ ይልቃል ከፋለ ሙትቻ የሆኑትን ሥራየ ብሎ እየመረጠ ነው፡፡  ስለዚህም ትልቁ ጥያቄ ደመቀ መኮንን እመራዋልሁ በሚለው ባማራ ሕዝብ ላይ ይሄን ሁሉ ደባ የሚፈጽመው ለምንድን ነው የሚለው ነው፡፡   

ደመቀ መኮንን በትምህርቱ ብዙም ያልገፋ ከመሆኑም በላይ ራሱን በራሱ የሚያስተምር ዓይነት ሰው አይደለም፡፡  ወያኔ የትምህርት ሚኒስቴር አድርጎት የነበረውም ያልተማረ በመሆኑ ነበር፡፡  በዚያ ላይ ደግሞ የሚያውቃትን በደንብ መግለጽ የማይችል አንደበተ ግድር (challenged) ከመሆኑም በላይ በራስ መተማመን የሚባል ነገር ምናምኒትም እንደሌለው በግልጽ ያስታውቅበታል፡፡  ይባስ ብሎ ደግሞ ኃላፊነት መውሰድን እንደ ጦር የሚፈራ የዣግሬነት ሰብዕና (follower mentality) በጽኑ የተጠናወተው፣ ለጀሌነት እንጅ ለመሪነት ያልተፈጠረ ግለሰብ ነው፡፡  

ይህን በእውቀትና በመንፈስ ደካማ የሆነ የምድረገነት (ከሚሴ) ግለሰብ፣ ላኮመልዛ (ወሎ) የኦሮሞ ነው በሚለው የኦነጋውያን የፈጠራ ትርክት አጭበርብሮ ወደ ቀንደኛ ኦነጋዊነት ለመቀየር፣ ላጭበርባሪው ለጭራቅ አሕመድ እጅግ በጣም ቀላል ነው፡፡  የደመቀ መኮንን ተግባር በግልጽ የሚያመለክተው ደግሞ ግለሰቡ በጭራቅ አሕመድ ኦነጋዊ ስብከት ታውሮ፣ ከወያኔነት ወደ ኦነጋዊነት ተቀይሮ፣ ከመምህሩ ደቀመዝሙሩ እንዲሉ ከራሱ ከጭራቅ አሕመድ በላይ ጽንፈኛ ኦነጋዊ ሁኖ፣ የኦነጋውያንን ፀራማራ አጀንዳ ከጭራቅ አሕመድ በላይ እያራመደ መሆኑን ነው፡፡  የአማራ ሕዝብ መሪ ነኝ እያለ፣ አማራ ሕዝብ በኦነግ ሲጨፈጨፍ ዝንብ የሞተ ሳይመስለው ድመጹን አጥፍቶ የተቀመጠው፣ የአማራን ለምድ የለበሰ ኦነጋዊ ተኩላ በመሆኑ ብቻና ብቻ ነው፡፡   

የሰኔ አስራምስቱ የባሕርዳር ጭፍጨፋ ሚስጥር ቁልፉ ያለው ደመቀ መኮንን የአማራን ለምድ የለበሰ ኦነጋዊ ተኩላ መሆኑን በመረዳትና በጭፍጨፋው ወቅት ቦሌ አየር ወደብ ውስጥ ጃኖች መንፈላሰሻ  (vip lounge) ተቀምጦ ምን ሲያደርግ እንደነበር አጥብቆ በመጠየቅ ነው የሚባለውም በዚሁ ምክኒያት ነው፡፡  

ደመቀ መኮንን በራስ መተማመን  እጥረት የሚሰቃይ ሰው ስለሆነ፣ እነከሌ በማንነትህና በምንነትህ ይንቁሃል ብሎ በመስበክ ለበቀል እንዲነሳሳ ማድረግ ለሐሳዊ ተዋኙ (con artist) ለጭራቅ አሕመድ የሕጻን ጨዋታ ያህል ቀላል ነው፡፡  የፈሪ ብትር ሆድ ይቀትር እንዲሉ፣ እንደ ደመቀ ዓይነት ቱርቂ ለበቀል ከተነሳሳ ደግሞ ብትሩ በጣም አሰቃቂ ነው፡፡  ጭራቅ አሕመድ ደመቀ መኮንንን በበቀል ስሜት አነሳስቶ ባሕርዳር ላይ ለፈጸመው አሰቃቂ ወንጀል ግብራበሩ ካደረገው ደግሞ፣ ወንጀለኛነቱን እንደ ማስፈራርያ በመጠቀም ሲጠራው ወዴት፣ ሲልከው አቤት፣ ዝቀጥ ሲለው እስከየት የሚል፣ አፋሽ አጎንባሽ ሎሌው ያደርገዋል፣ አድርጎታልም፡፡  

ባጭሩ ለመናገር ደመቀ መኮንን ማለት በወያኔ ዘመን ከወያኔ በላይ ወያኔ፣ በኦነግ ዘመን ደግሞ ከኦነግ በላይ ኦነግ እየሆነ፣ ለመጣ ለሄደው አማራበል ጭራቅ በሎሌነት በማደር አማራን የሚያስበላ ሎሌጭራቅ ነው፡፡  ስለዚህም የአማራ ሕዝብ ሕልውናውን በጭራቅ አሕመድ ላለማስበላት በሚያደርገው መራራ ትግል ላይ የመጀመርያው ርምጃ መሆን ያለበት ይህን ሎሌጭራቅ ባስፈላጊው መንገድ ጨርቅ ማድረግ ነው፡፡  

ደመቀ መኮንን ልክ እንደ ጌታው እንደ ጭራቅ አሕመድ እጅግ ሲበዛ ፈሪ ነው፣ እጅግ ሲበዛ ጨካኝ የሆነውም እጅግ ሲበዛ ፈሪ ስለሆነ ነው፡፡  ስለዚህም፣ ደመቀ መኮንን ባማራ እጅ ወድቆ የጁን እስኪያግኝ ድረስ በሚከተሉት ሁለት መንገዶች በማስፈራራት ባማራ ሕዝብ ላይ የሚፈጽመውን ደባ በተወሰነ ደረጃ መቀነስ ይቻላል፡፡

አንደኛው መንገድ እዚያው ጦቢያ ውስጥ ነው፡፡  ደመቀ መኮንን አማራን ደም እያስበላ በሚከፈለው የደም ገንዘብ እሱ፣ የሱ ቤተሰቦችና ዘመድ አዝማዶች ማኛ እየበሉ ጦቢያ ውስጥ በሰላም መኖር የለባቸውም፡፡  ይህን መፈጸም ያለበት ደግሞ ሌላ ማንም ሳይሆን ደመላሽ ፋኖ ነው፡፡  ለሚደረግብህ ሁሉ አፀፋውን መመለስ አልሞት ባይ ተጋዳይነት የሚባል የተፈጥሮ ሕግ ስለሆነ፣ በፍትሓብሔርም አያስወነጅልም፣ በወንጌልም አያስኮንንም፡፡     

ሁለተኛው መንገድ አሜሪቃ ውስጥ ነው፡፡  ደመቀ መኮንን አማራን እየጨፈጨፈና እያስጨፈጨፈ በሚከፈለው የደም ገንዘብ እሱና ቤተሰቦቹ አሜሪቃ ውስጥ ተንቀባረው መኖር የለባቸውም፡፡  ይህን ማድረግ ያለበት ደግሞ ሌላ ማንም ሳይሆን ዲያስፖራ ፋኖ ነው፡፡   ዲያስፖራ ፋኖ ደመቀን ለማሸማቀቅ ሊያደርጋቸው ከሚችላቸው ድርጊቶች ውስጥ አንዱ ማንነቱን የሚያጋልጡ ጽሑፎችን ይዞ በደመቀ ያሜሪቃ ቤት አቅራቢያ በፈረቃ እየተለዋወጠ በየዕለቱ መቆም ነው፡፡  ይህ ደግሞ ያገር ውስጥ ደመላሽ ፋኖ ከሚከፍለው መስዋዕትነት አንጻር ኢምነት ነው፡፡  አወ፣ ሸማ በየፈርጁ፣ ትግል በየደጁ ነው፡፡  ድል ደግሞ የትግሎች ሁሉ ድምር ውጤት ነው፡፡

መስፍን አረጋ

mesfin.arega@gmail.com

Filed in: Amharic