>
5:26 pm - Wednesday September 15, 9277

አትሩጡ፤ ፈረሰኛው ይመጣል

አትሩጡ፤ ፈረሰኛው ይመጣል

አማራ ሊገል፣ በሜንጫ ቆርጦ

ሸኔ ተብሎ ስሙን ለውጦ

ዐብይ መጣ ዓይኑን አፍጦ

ወይ መሸሸጊያ ትንሽ ቁጥቋጦ፡፡

ተሸሽገህስ የታባክ ልትደርስ?

እንኳን ቁጥቋጦ መኖርያ የሰስ

ብትገባም እንኳን እግዚአብሔር መቅደስ 

እዚያው ያርድሃል አፍኖ በጭስ፡፡ 

ይልቅ አድርገህ ፊትህን መለስ

ቆርጠህ በሞትህ፣ ጨክነህ በነፍስ

ብትጋፈጠው ዐብዩን እርኩስ፣

ጦሩን እንሰቶ ቀድሞ ከንፋስ

ይደርስልሃል ጎርጊስ በፈረስ፡፡

ፈርተህ ስትፈረጥጥ፣ እየመሰለህ የምታመልጥ

ትገባለህ ብለህ ቀጥ፣ ከእሳት ወጥትህ እረመጥ

ይጠብቅሃል ቀውጥ፣ ይበልጥ የሚሰቀጥጥ፡፡

መስፍን አረጋ 

mesfin.arega@gmail.com

Filed in: Amharic