>

ኢትዮ 251 ሚዲያ ተዘረፈ!

ኢትዮ 251 ሚዲያ ተዘረፈ!

ሙሉጌታ አምበርብር

ኢትዮ 251 ሚዲያ ካሜራን ጨምሮ ሙሉ የሚዲያ ንብረቶቹን ተዘረፈ።ዘረፋው የተፈጸመው ትናንት ዕሁድ መጋቢት 10/2015 ዓም “ጠንካራ ጥበቃ” ባለውና መሐል አራት ኪሎ ድንቅ ሥራ ኮምፕሌክስ ላይ በሚገኘው የድርጅቱ ስቱዲዮ ነው። በተፈጸመው ዘረፋም የድርጅቱ መገልገያ የነበሩ አራት ዘመናዊ ካሜራዎች፣ ኔክማይክ፣ ዙመር እና ሌሎችም መገልገያ ቁሳቁሶች ተዘርፈዋል።

ቁሳቁሶቹ ከ”ኢትዮ 251″ በተጨማሪ፤ “አራት ኪሎ ሚዲያ” እና “ነገረ ወልቃይት”ን የመሳሰሉ ሚዲያዎች የሚገለገሉባቸው እንደነበረ ይታወቃል።

የተዘረፉት የሚዲያ ፕሮዳክሽን ቁሳቁሶቹ “ትናንት እሁድ ዕኩለ ቀን ድረስ ሲሰራባቸው ነበር” ያለው የኢትዮ 251 ሚዲያ ባለቤትና ስራ አስኪያጅ ጋዜጠኛ ሙሉጌታ አንበርብር የተዘረፉት ንብረቶች አጠቃላይ ዋጋ ከአንድ ነጥብ ሰባት ሚሊዮን (1,700,000) ብር በላይ እንደሚገመት ተናግሯል።

ኢትዮ 251፣ አራት ኪሎ ሚዲያ እና ነገረ ወልቃይት ሚዲያ ወቅታዊ ሃገራዊ የፖለቲካ ጉዳዮችን በመዘገብና ጥልቅ ትንታኔዎችን በመስጠት ከሚታወቁ ቀዳሚ የዲጂታል ሚዲያ አማራጮች መካከል መሆናቸው ይታወቃል።

በነገራችን ላይ የተከራየንበት ህንጻ “ድንቅ ሥራ ኮምፕሌክስ” ይባላል። በህንጻው ላይ ሁለት ባንኮችን ጨምሮ ሌሎች ታላላቅ ድርጅቶች ለዓመታት እየሠሩ ያለ ቢሆንም አንዳቸውም ሊዘረፋ ቀርቶ ሙከራ እንኳ ተደርጎባቸው እንደማያውቅ ባደረግነው ማጣራት አረጋግጠናል።

ስምንተኛ ፎቅ ድረስ በመውጣት የሚዲያ ተቋምን መዝረፍ የሕዝብ ድምፅ በሆኑ በሚዲያ ላይ የተቃጣ ጥቃት በመሆኑ፣ እንደ ቀላል የሚታይ ጉዳይ አይደለም።

Filed in: Amharic