>

ጉራጌ አዲስ ታሪክ ፅፏል! (ጥላሁን ጽጌ)

ጉራጌ አዲስ ታሪክ ፅፏል! 

ጥላሁን ጽጌ

ታስታውሱ እንደሆነ ከዛሬ ሶስት ዓመታት ገደማ በፊት አቢይ አህመድ ወደ ጉራጌ ሄዶ ከህዝብ ጋር ውይይት አድርጎ ነበር። ያኔ የጉራጌ ክልልነት ጥያቄ መቀንቀን የጀመረበት እንጅ እንደዛሬው መሬት የያዘ የፖለቲካ ትግል ይደረግበት የነበረ ወቅት አልነበረም። ለኦህዴዶች ግን ገና ከጅምሩ እንደ ስጋት ይታይ የነበረ እንቅስቃሴ ነው። 

ከሶስት አመታት በፊት አቢይ አህመድ ባደረገው ንግግር የኢትዮጵያዊነትን ካርድ ጉራጌን ለመሸወድ ተጠቅሞት ነበር። አቢይ “ጉራጌን በዘር የታጠረ ፖለቲካ አይመጥነውም። የጉራጌ ክልሉ ኢትዮጵያ ናት። ጉራጌ የሚያምርበት እየነገደ ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሲያደርግ እንጅ ከኢትዮጵያዊነት ወርዶ የክልልነት ጥያቄ ሲያነሳ አይደለም” የሚል በመርዝ የተለወሰች ፖለቲካዊ ንግግርን ሲያደርግ አስታውሳለሁ። መፅሀፉ ይህ ህዝብ በእጁ እያጨበጨልኝ ልቡ ግን ከእኔ አይደለም እንደሚለው የአዳራሹ ህዝብ ጭብጨባ ለሚወደው ጠሚ ሞቅ አድርጎ አጨበጨበለትና ሸኘው። ልቡ ግን ሌላ ነበር! 

ለወትሮው የጉራጌ ህዝብ Politically less relevant ተደርጎ ይሳል ነበር። ህዝቡ ከንግዱ ዓለም ውጭ ሌላ ፍላጎትና ጥቅም እንደሌለው ተደርጎ ይፃፍ ይነገር ነበር። የአቢይ አህመድ ንግግርም ጉራጌ የኢኮኖሚ እንጅ የፖለቲካ ኢንተረስት የለውም ከሚለው የተለመደ እሳቤ የሚመነጭ ሆኖ በዚህ እሳቤ ውስጥ በጉራጌ expense ለማሳካት የሚፈልጉትን ጥቅም ያሰላ ማደንዘዣ ንግግር ነበር። ይህ በብዙዎች ይነሳ የነበረው እሳቤ የጉራጌን ህዝብ በብዙ መልኩ ሲጎዳ ነበር። 

እየጋለ የመጣውን የጉራጌ ህዝብ የክልልነት ጥያቄ የኦህዴድ መራሹ መንግሥት በሀይል ለማፈን ያላደረገው ጥረት የለም። ነገር ግን የጉራጌ ህዝብ ጥይቄ ይባሱን ተጠናከረ። የጉራጌ የክልልነት ጥያቄ Oromization of the entire south ለሚለው የኦሮሙማ ፕሮጀክት ትልቅ ደንቃራ ሆኖባቸዋል። በህገመንግሥቱ የተፈቀደውን ጥያቄ በሀይል ለማፈን የፈለጉትም ለዚህ ነው። 

ዛሬ የወልቂጤ ህዝብ ለጠቅላይ ሚንስትሩ ያሳየው ግልፅ ምላሽ በጉራጌ የቅርብ ጊዜ ታሪክ አዲስ የፖለቲካ ምዕራፍ ተደርጎ የሚወሰድ ነው። ንግድ እንጅ ፖለቲካ ለጉራጌ ምን ያደርግለታል የሚለውን አደንዛዥ እሳቤ የሰባበረ ክስተት ነው። የዛሬው የጉራጌ ህዝብ የተናበበ እና ስኬታማ የፖለቲካ ምላሽ ለሌሎች አጎራባች የደቡብ አካባቢዎች ሳይቀር ትልቅ መልዕክት ይሰድዳል። 

እኔ ለጉራጌ ህዝብ የፖለቲካ ጥያቄዎች ግልፅ ድጋፌን እሰጣለሁ። አንደኛ ከState ተቃራኒ የሆነ የፖለቲካ ጥያቄ ስለሌለው። ሁለተኛ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ እቅፍ ድግፍ አድርጎ በመያዝ ትልቅ ድርሻ ያለው ህዝብ ፖለቲካዊ ጥቅሙ ሊከበርለት ይገባል ብዬ ስለማምን። ሶስተኛ ሌሎችን በመዋጥ የጠቅላይ እና ጨፍላቂ ተስፋፊዎችን ፕሮጀክት በግልፅ ስለሚገታ።

Filed in: Amharic