>

የትኛውን ዕድሜ ለመኖር ነው ይኼ ሁሉ ጉብ-ቂጥ!? (ጋዜጠኛ ወሰንሰገድ ገብረኪዳን)

የትኛውን ዕድሜ ለመኖር ነው ይኼ ሁሉ ጉብ-ቂጥ!?

ጋዜጠኛ ወሰንሰገድ ገብረኪዳን

እኚህ ሰው “ምሁር” ነበሩ። እኚህን ሰው ስናውቃቸው “ታጋይ” ነበሩ። በዚህ ላይ ዕድሜአቸው ገስግሷል። ዛሬ አብርሆት ቤተመፅሐፍት ተገኝተው እንዲህ አሉ፤ አሉ፦መደመር የተበታተነን ጉልበት ወደ ጠንካራ ሀይል የሚቀይርና ከመነጋገር ለውጥ እንደሚመጣ የሚያረጋግጥ መንገድ ነው

ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም መቼም እዚህ ሀገር “ዘይገርም” የማያሰኝ ነገር የለም። እኛ አምስት ዓመት ሙሉ ያየነው እኚህ “ምሁር” ከሚሉት ነገር የተለየ ነው። መደመር የሚባል ቅዠት ከመጣ ወዲህ አብሮ የኖረው ሕዝብ አንዱ ተሳዳጅ፣ ሌላው አሳዳጅ ሲሆን ነው ያየነው። አንዱ አፈናቃይ ሌላው ተፈናቃይ ሲሆን ነው ያየነው። ጦርነት እና ስቃይ ነው ያየነው። ስደት እና መከራ ሰፍቶ ተንሰራፍቶ ነው ያየነው። ሕግ ያስከብሩ የተባሉ ወገኖች ከሕግ በላይ ሆነው ሥርዓት አልበኝነትን ሲያነግሱ ነው ያየነው። በሕግ ስም ሕጋዊ ማጅራት መቺዎቾ መበርከታቸውን ነው የምናውቀው። የኑሮ ውድነት በሚያናጥርበት ሕዝብ ትከሻ ላይ የተፈናጠጡ የለየላቸው አምባገነን ገዢዎች መንሰራፋታቸውን ነው የምናውቀው። የሚነጋገር ሳይሆን ዳፍንታም አመራር መምጣቱን ነው የምናውቀው። ወዘተእኚህ “ምሁር”፣ እኚህ “የቀድሞ ታጋይ”፤ እኚህ ትን የሚያሰኙ “ተንታኝ” ከአሜሪካ ድረስ ተንደርድረው መጥተው ለእኛ መደመር የተሰኘውን የሰውዬውን ቅዠት ሊተነትኑልን መሞከራቸው ነው የሚገርመው። የኖርንበትን የምናውቅ እኛ፣ የሚተነትኑልን እነኛ ማለት ይኼ ነው። ድንቅ ሎጂክ ነው ያልኖሩበትን መተንተን። ግን ግን የትኛውን ዕድሜ ለመኖር ነው ይኼ ሁሉ ጉብ-ቂጥ!ወይ አለማፈር….

Filed in: Amharic