>

የማኦ ዜዶንግ መመሪያወች ላማራ ሕዝባዊ ግንባር (መስፍን አረጋ)

የማኦ ዜዶንግ መመሪያወች ላማራ ሕዝባዊ ግንባር

ውሻን በርግጫ መምታት እንካ ሥጋ ማለት ነው

መስፍን አረጋ

ጭራቅ አሕመድ ቆርጦ የተነሳው አማራን በልቶ ለመጨረስ ነው፡፡  አማራን በልቶ ቢጨርስ ደግሞ ምዕራባውያን ጌቶቹ ዝንቡን እሽ እንደማይሉት በግልጽ አሳውቀውታል፡፡  ለነጻነቱ ቀናዒ የሆነው፣ በማንነቱ የሚኮራው፣ ነጭን ከመጤፍ የማይቆጥረው የአማራ ሕዝብ እንደ ሕዝብ ቢጠፋ፣ ያፍሪካ አንድነት ምልክት የሆነችው አዲሳባ ደግሞ አማራና አማራዊነት ሙሉ በሙሉ የተወገደባት፣ አፍርቃዊ አፓርታይድ የነገስባት፣ የአፍሪቃውያን በጎጥ የመከፋፈል ዋና ምልክት የሆነች፣ አፍሪቃውያንን አንገት የምታስደፋ፣ አሳፋሪ ኦነጋዊ ከተማ ብትሆን ምዕራባውያን ደስታውን አይችሉትም፡፡ 

ስለዚህም የምዕራባውያን ሙሉ ድጋፍ ያለውን፣ በጭራቅ አሕመድ የሚመራውን፣ የኦነግንና የወያኔን ፀራማራ ጣምራ ጦር  ፊት ለፊት መግጠም፣ የእሳት ራት ከመሆን ውጭ ፋይዳ የሌለው አጉል ጀብደኝነት ነው፡፡  የጭራቅ አሕመድ ዓላማ ደግሞ ዘመናዊ መሣርያ እስካፍንጫው የታጠቀውን የኦንግንና የወያኔን ጣምራ ጦር ይዞ፣ የነፍስ ወከፍ መሣርያ ካነገበው ከፋኖ ጋር ፊት ለፊት ለመግጠምና፣ ፋኖን በዚያውም መላውን የአማራን ሕዝብ በመድፍ እየመደፈ፣ በንቦቴ (drone) እየነቦተ የዶግ ዐመድ ለማድረግ ነው፡፡ 

በሰው ኃይልና በመሣርያ ብዙ እጥፍ የሚበልጥህን ጠላት አንተ በመረጥከው መቸት (መቸ እና የት) እንጅ እሱ በመረጠው መቸት አትገጥመውም፡፡  ይህ ማለት ደግሞ ሌላ ምንም ማለት ሳይሆን የደፈጣ ውጊያ ማለት ነው፡፡  ስለዚህም ያማራ ሕዝባዊ ግንባር (አሕግ) በጭራቅ አሕመድ ከሚመራው የኦነግና የወያኔ ጣምራ ጦር ጋር መፋለም ያለበት በደፈጣና በደፈጣ ብቻ ነው፡፡  ለዚህ የደፈጣ ውጊያ ግብአት ይሆነው ዘንድ ደግሞ ያያቶቹን ያርበኝነት ትግል ማስታወሱ ብቻ ይበቃዋል፡፡

ያርበኝነት ዘመን ፋኖወች ጣልያንን ያርበደብዱ የነበሩት፣ ያገራቸውን ዱር፣ ተራራና ሸንተርር ተገን በማድርግ መሠረታዊ የደፈጣ ውጊያ ስልቶችን በመጠቀም ነበር፡፡  ምናልባትም ደግሞ እነዚህን የደፈጣ ውጊያ ስልቶች ለመጥቀም የመጀመርያወቹ እነሱ ሳይሆኑ አይቀሩም፣ ያገራችን ታሪክ ከጥንት ከጠዋቱ ጀምሮ የጦርነት ታሪክ ነውና፡፡  ግራም ነፈሰ ቀኝ፣ የቻይናው ማኦ ዜዶንግ በጽሑፍ ስላስቀመጣቸው ብቻ በሱ ስም የሚጠሩት፣ የደፈጣ ውጊያ የሚካሂድባቸው ሦስቱ ስልታዊ ትእዛዞች (The Three Tactical Commandments) የሚከተሉት ናቸው፡፡

  1. ጠላት ሲበረታ አፈግፍግ
  2. ጠላት ሲዳከም አጥቃ
  3. ጠላት ሲያርፍ አውክ

የማኦ ዜዶንግ አሥሩ ስነስርዓታዊ ትዕዛዞች (The Ten Disciplinary Commandments) ደግሞ የሚከተሉ ናቸው።

  1. ያለቃህን ትእዛዝ ቅንጣት ሳትጠራጠርና ላፍታ ሳታንገራግር ፈጽም።
  2. የሕዝብን ንብረት አትንካ፣ መርፌም ብትሆን።
  3. ከሕዝብ ስጦታ አትቀበል፣ ክርም ብትሆን።
  4. ከሕዝብ ምንም ነገር አተዋስ፣ የግድ መዋስ ካለብህ ደግሞ የተዋስከውን ወዲያውኑ ተጠቅመህ በተዋስክበት ሁኔታ መልስ፣ ካበላሸህም ትክክለኛ ዋጋውን ክፈል (አልቀበልም ብትባል እንኳን በትሕትና አሳምነህ ሳትከፍል አትንቀሳቀስ)።
  5. ከገበያም ሆነ ከየትም ቦታ ለምትገዛቸው ወይም ለምትሸምታቸው ነገሮች ሁሉ ተገቢ ዋጋቸውን ክፈል (አልቀበልም ብትባል እንኳን በትሕትና አሳምነህ ሳትከፍል አትንቀሳቀስ)።
  6. በውጊያ ወቅት ላወደምከው ወይም ላጠፋኻው ወይም ለጎዳኻው የሕዝብ ሐብት፣ ንብረትና ሂወት ተገቢውን ካሳ ሙሉ በሙሉ ክፈል (አልቀበልም ብትባል እንኳን በትሕትና አሳምነህ ሳትከፍል አትንቀሳቀስ)።
  7. የውጊያ ግርግር ለዘራፊ ያመቻልና፣ በግርገሩ የተዘረፈን፣ የተበዘበዘን ወይም የተመዘበረን የሕዝብ ሐብትና ንብረት አስመልስ፣ ማስመለስ ካልቻልክ ደግሞ ተገቢውን ካሳ እራስህ ክፈል (አልቀበልም ብትባል እንኳን በትሕትና አሳምነህ ሳትከፍል አትንቀሳቀስ)።
  8. ሴት፣ ወንድ፣ ሕጻን፣ አረጋዊ ሳትል ማናቸውንም ሰው ስታናግር ሁልጊዜም በትሕትና አናግር፣ በተቻለህ መጠን ደግሞ እርዳ።
  9. ልጃገረድ፣ ኮረዳ፣ ባለትዳር፣ ፈት፣ ጋለሞታ፣ ሴታአዳሪ ሳትል ሴትን አክብር እንጅ በጭራሽ እንዳትደፍር።  ግዳጅ ላይ እስካለህ ድረስ ከሩካቤ ሥጋ ፈጽሞ ታቀብ።
  10. ምርኮኛም ሆነ እስረኛ አታጎሳቁል፣ በተቻለህ መጠን ተንከባከብ።

ሦስቱ ስልታዊ ትእዛዞች እና ካሥሩ ስነስርታዊ ትዕዛዞች በተጨማሪ ደግሞ ማኦ ዜዶንግ ያረቀቃቸው የተለያዩ መመሪያወች ነበሩ።  ከነዚህም ውስጥ የሚከተሉት ጥቂቶቹ ናቸው። 

  1. የአካል ብልቶች ብዙ ቢሆኑም፣ የአንድ በአንድ ለአንድ ናቸው።  ዓይን ጆሮን ንቆ አያስፈልገኝም ቢል፣ የደንቆሮ ዓይን ይሆናል።  ጆሮ ዓይንን ንቆ አያስፈልገኝም ቢል፣ የእውር ጆሮ ይሆናል።  እጅ እግርን ንቆ አያስፈልገኝም ቢል፣ የቆማጣ እጅ ይሆናል።  እግር እጅን ንቆ አያስፈልገኝም ቢል፣ የዱሽ እግር ይሆናል።  የጦር መሪ የመጀመርያው ተግባር ሁሉም የሠራዊቱ ክፍሎችና አባሎች ላንድ ዓላማ ባንድነት የቆሙ አንድ መሆናቸውን በማሳመን በመካከላቸው ሠራዊታዊ ፍቅርና መከባበር እንዲያደር በማድረግ አንተ ትብስ አንቺ ትብስን ማስፈን ነው።  መናናቅ አብሮ ለመወደቅ፣ መከባበር አብሮ ለመናር። 
  2. ጠቢብ የጦር አዛዥ ንግግር የማያበዛ ጭምት ነው፣ በቀላሉ የማይበሳጭ ሆደ ሰፊ ነው፣ የሚተማመነው በልቡ ሳይሆን ባይምሮው ነው፣  በእቅድ እንጅ በደመነፍስ አይመራም፣ ደንብና ስርዓትን አክብሮ ያስከብራል፣  ለሂወቱ አይሳሳም፣ ለንብረት አይጓጓም።  ሞት ጅብ ነው፣ የደፈረውን ይፈራል፣ የፈራውን ይደፍራል።  ዘጠኝ ሞት መጣ ሲለሁ አንዱን ግባ ካልከው ዘጠኙም ይመለሳል።  
  3. አንዳንድ ሰወች የራሳቸውን ማንነትና ምንነት አብጠርጥረው ሲያውቁ፣ ስለባላንጣቸው ማንነትና ምንነት ግን ፍንጭ እንኳን የላቸውም።  አንዳንዶቹ ደግሞ የነዚህ ዓይነት ሰወች ተቃራኒወች ናቸው።  ሁለቱም ዓይነት ሰወች ለጦር አመራር ብቁ አይደሉም።  ጠላትህን መርታት የምትችለው ያንተን ብቻ ሳይሆን የጠላትህን ማንነትና ምንነት አብጠርጥረህ ስታውቅ ብቻ ነው።   

ስለዚህም ፋኖ የጠላቱን የጭራቅ አሕመድን ምንነትና ማንነት አብጠርጥሮ ማወቅ አለበት።  የጭራቅ አሕመድ ትልቁ ችሎታው አጭበርባሪነቱ ነው፡፡  ጭራቅ አሕመድ ወተት ነጭ ነው ቢል መታመን የሌለበት ውሸታም፣ የሚፈልገውን ለማግኘት እስካስፈላጊው ለመዝቀጥ ቅንጣት የማያቅማማ ዝቃጭ ነው።  ጭራቅ አሕመድ በከረረ የማንነት ቀውስ (chronic identity crisis) የሚሰቃይ የስነልቦና በሽተኛ፣ በእኩይ ባሕሪ የተጨማለቀ ነውረኛ ነው።  ጭራቅ አሕመድ ቀዝቃዛ ውሃ ውስጥ \የሚያልበው\፣ ጥላው የሚያስበረግገው ፈሪ ነው፣ የፈሪነቱን ያህል ደግሞ ጨካኝ አረመኔ ነው። ስለዚህም ከዚህ ውሽታም፣ ዝቃጭ፣ ነውረኛ ጨካኝ አርመኔ ጋር መደራደር የሚቻለው በነፍጥና በነፍጥ ብቻ ነው።  

ያርበኝነት ዘመን ፋኖወች ከመደበኛ ውጊያ ወደ ደፈጣ ውጊያ የዞሩት ጣልያን አዲሳባን ከተቆጣጠረ በኋላ ነበር፡፡  ባሁኑ ጊዜ ደግሞ አዲሳባን የተቆጣጠረው አማራን ከምድረግፅ ለማጥፋት የተነሳው የጭራቅ አሕመድ ኦነግ ነው፡፡  ይህ ፀራማራ አውሬ ካዲሳባ የሚወጣው ደግሞ ከገጠር ወደ አዲሳባ በሚያመራ፣ በደፈጣ ውጊያ ጀምሮ እያደገ ሂዶ ወደ መደበኛ ውጊያ በሚሸጋገር የነጻነት ጦርነት ነው፡፡  ያማራ ሕዝባዊ ግንባር ዓላማም ይሄውና ይሄው ነው፡፡         

በደፈጣ ውጊያ ላይ ያማራ ሕዝባዊ ግንባር (አሕግ) የመጀመርያ ግብ መሆን ያለበት ደግሞ፣ ገጠሩን ያማራ ክልል መሠርት አድርጎባስፈላጊው መቸት አስፈላጊውን ጥቃት እያደረሰ፣ በጭራቅ አሕመድ የሚመራው የወያኔና የኦነግ ጥምር ጦር ያለ አጃቢ (ኮንቮይ) እንዳይጓዝ በማስገደድ፣ የሰው ኃይል፣ የስንቅና የትጥቅ አቅርቦቱን በከፍተኛ ደረጃ ማስተጓጎል ነው፡፡

በኮንቮይ በሚጓዝበት ጊዜ ደግሞ ኮንቮዩ መዟዟሪያ ከሌለው ጠባባ የተራራ መንገድ ላይ እስኪደርስ ጠበቆ፣ የኮንቮዩን የመጀመርያና የመጨርሻ መኪኖች በማጋየት ኮንቮዩ ወደፊትም ወደኋላም መንቀሳቀስ እንዳይችል ካደረጉ በኋላ ግራ የተጋቡትን ወታደሮች ይበልጥ ግራ እያጋቡ በመትረየስ መልቀም ነው፡፡ 

መስፍን አረጋ

mesfin.arega@gmail.com

Filed in: Amharic