ከአማራ ሕዝባዊ ግንባር የተሰጠ አስቸኳይ መግለጫ
ዘመነ ካሴንና የአማራን የቁርጥ ቀን ልጆች ለማፈን መሞከር በእሳት መጫወት ነው!
(07/14/2023)/የአብይ አህመድ እና የብአዴን ተላላኪዎች በቅርቡ በፍርድ ቤት ትእዛዝ ከ9 ወር እሥራት በኋላ የተፈታውን አርበኛ ዘመነ ካሴን መልሶ ለማሠር የሚያደርጉት ጥረት የአማራን የህልውና ትግል ለመቀልበስ እንደሆነ ግልጽ ነው።
የአማራውን የቁርጥ ቀን ልጆች የሚያሳድዱ፣ የሚያሥሩ፣ የሚያሳሥሩ ወይም ግርግር እየፈጠሩ ሕይወታቸውን አደጋ ላይ ለመጣል የሚሞክሩ፣ የሚተባበሩ፣ የሚያስተባብሩ፣ መረጃ ለጠላት የሚያቀብሉ፣ የሚመሩ ሁሉ የአማራን ህዝብ እየወጉ መሆናቸውን ሊያውቁት ይገባል።
ስለሆነም፣ አሳልፎ በመሥጠት ሥራ የተሰማራችሁ ከድርጊታችሁ እንድትቆጠቡበጥብቅ እናሳስባለን። የአማራን ሕዝብ የቁርጥ ቀን ልጆች ለማፈን ወይም ለማሳፈን መሞከር በእሳት መጫወት ነው!
ጀግናው የአማራ ሕዝብ ሆይ!
የአርበኛ ዘመነ ካሴም ሆነ የሌሎች የሕልውና ትግልህ መሪዎች በጠላት እጅ መውደቅ ማለት አማራን እያስጨፈጨፉ ለሚገኙት አብይ አህመድና ለብአዴን ድልን ማጎናፀፍ ማለት ነው። ስለሆነም፣ በረዥም ጊዜ ትግል የተፈተኑትን፣ ላንተ ሲሉ በመደጋገም የታሠሩልህን፣ በበረሃ የተንከራተቱልህን የቁርጥ ቀን ልጆችህን ከውስጥም ሆነ ከውጭ የህልውናህ ጠላቶች በያሉበት ቀንም ሆነ ማታ እንድትጠብቃቸው ጥሪያችንን እናቀርብልሃለን።
የአማራ ሕዝባዊ ግንባር!
መነሻችን አማራ፣ መዳረሻችን ኢትዮጰያ!