>

የአማራ ህዝብ ትግል ከፍ ወዳለ ደረጃ መሸጋገርን አስመልከቶ የተሰጠ አስቸኳይ መግለጫ

የአማራ ህዝባዊ ግንባር  አስቸኳይ መግለጫ

የአማራ ህዝብ ትግል ከፍ ወዳለ ደረጃ መሸጋገርን አስመልከቶ የተሰጠ አስቸኳይ መግለጫ

የአማራ ህዝብ በደምና አጥንቱ ባፀናት አገሩ ላለፉት 50 ዓመታት ስርዓት ወለድ በሆነ ችግር በማንነቱ ሲጨፈጨፍ፣ሲፈናቀል፣ሲሰደድና በሴራ ከአገሪቱ ፖለቲካ እንዲገለል በማደረገ ከምጣኔ ሀብታዊና ማህበራዊ ጥቅሞች ውጭ ሆኖ ቆይቷል።ይባስ ብሎ ላለፉት አመታት በለውጥ ስም የኢትዮጵያን መንበረ ዙፋን የተቆጣጠረውና በጥላቻ ያደገው የዘረኛው ህዎሓት የብኩር ልጅ ኦህዴድ/ኦነግ በስልጠና፣በትጥቅና በስንቅ ባደራጃቸው ገዳይ ኃይሎቹ አማራውን ያለርህራሄ በጥይትና በገጀራ በመጨፍጨፍ የዘር ማጥፋት ፈፅመዋል።ሀብት ንብረቱን ዘርፈውና አውድመው ከሚኖርበት አካባቢ በማፈናቀል የዘር ማፅዳት ፈፅመዋል፤ቅድመ አያቶቹ ባቀኗት ከተማ አዲስ አበባ እንዳይገባ ከልክለዋል፣በኢትዮጵያ ሰማይ ስር ተዘዋውሮ እንዳይሰራ መንገድ ላይ እያገቱ ዘርፈዋል፣ገድለዋል።
አሁን አሁን ደግሞ ከመዝረፉና መግደሉ ባሻገር ህፃናትን ሁሉ ሳይቀር እያገቱ “ማስለቀቂያ” በሚል ዘዴ ከድሃ የአማራ እናቶች መቀነት በሚሊዬንስ ገንዘብ ይቀበላሉ፤የአማራ ባለሃብቶች የባንክ አካውንቶችን አግደዋል።አርሶ አደሩ በጉልበቱ ዘርቶ እንዳይቅም በተጠና መንገድ የአፈር ማዳበሪያ በመከልከል ማሳው ጦም እንዲያድር አድርገዋል።
ይህ ሀሉ አልበቃ ያለው ፈሽስቱ የኦህዴድ/ኦነግ ስርዓት ላለፋት አራት ወራት “ህግ ማስከበር” በሚል ሽፋን በአማራ ክፍለሀገር በመከላከያ ስም የተደራጀ የአንድ ዘር ታጣቂ ሰራዊት በማዝመት የዕምነት ተቋማትን አውድሟል፣ሴቶችን ደፍሯል፣ንፁሃንን ገድሏል፣አሁንም ስፍር ቁጥር የሌለው ሰራዊት ወደ አካባቢው እያስገባ ይገኛል።
የዚህ ሁሉ በደል ባለቤት የሆነው የአማራ ህዝብ የጀመረውን የህልውና ትግል ከፍ ወዳለ ደረጃ በማደረስ ከሐምሌ 24/2015 ዓ.ም ጀምሮ ከተሞችን ከፋሽስቱ ኦህዴድ/ኦነግ ብልፅግና መዋቅር በክንዱ ነፃ እያዎጣ ከተሞችን እየተቆጣጠረ ይገኛል።
በተለይም በጎጃም፣በጎንደር፣በወሎና በሸዋ አብዛኛውን ከተሞች ፋኖ ከህዝቡ ጋር በመቀናጀት የአሽከሩን ብአዴን ብልፅግና መዋቅር በመበጣጠስ በአስገራሚ ፍጥነት እና ብቃት እየተቆጣጠራቸው ይገኛል።
በመሆኑም የአማራ ህዝባዊ ግንባር የሚከተለውን ጥሪ ያስተላልፋል:-
1ኛ) የአማራ ህዝብ በጀግኖች ልጆቹ የጀመረውን የገዥውን ስርዓት መዋቅር እየበጣጠሰ ከተሞችን የመቆጣጠር ጎዞውን አጠናክሮ እንዲቀጥል፤
2ኛ) የአማራ ህዝብ የጀመረውን በክንዱ ነፃ የመውጣት ጉዞ ለማደናቀፍ በኩሊው ብአዴን በኩል ሐምሌ 27/2015 ዓ.ም ከምሽቱ 1 ሰዓት ጀምሮ ክልሉ ከቁጥጥራቸው ስር እንደወጣ በይፋ በመግለፅ ተጨማሪ የስርዓቱ ገዳይ ኃይል እንዲገባና ንፁሃንን እንዲጨፈጭፍ  ፈቅደዋል።ክልሉም በወታደራዊ አገዛዝ ስር እንዲዎድቅ አዝዘዋል።ስለሆነም:- በአማራ ክልልም ይሁን ከክልሉ ውጭ የሚገኝ ማንኛውም ታጣቂ ፋኖ፣የአማራ ልዮ ኃይል፣የአማራ ፖሊስ፣አድማ ብተና፣ምልስ የሰራዊቱ አባላት፣የሚሊሻ አባላትና ሌሎችም በሙሉ ከዛሬ ጀምሮ በክልሉ ያለው የስርዓቱ መዋቅር መፍረሱን በመረዳት ከአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ጎን እንድትሰለፉና ታሪካዊ ኃላፊነታችሁን ትዎጡ ዘንድ ግንባሩ ጥብቅ ጥሪ ያደርጋል።
3ኛ) የመከላከያ ሰራዊት አባላት በሙሉ የኦህዴድ/ኦነግ ፋሽስቱ ስርዓት ለግል ጥቅሙና ስልጣኑ ሲል ትናንት በእር በርስ ጦርነት በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ጓዶቻችሁን አስጨፍጭፏል፤የተጨፈጨፉ ጓዶቻቸሁ አስክሬን በወግ ተሰብስቦ ለአፈር ሳይበቃ ከገዳዮቻችሁ ጋር “በሰላም ስምምነት ስም” ክህደት ፍፅሞባችኋል።ዛሬ ደግሞ ይባስ ብሎ በክፉ ቀን ያበላ፣ ያጠጣችሁንና የሸሸጋችሁትን ህዝብ እንድትዎጉ ተገዳችኋል።ትዕዛዙን ባለመቀበል እየከዳችሁ ከአማራ ኃይሎች ጎን እንድትሰለፉ ጥሪ እናቀርባለን።
4ኛ) በአገዛዙ ስቃይና መከራ ውስጥ የምትገኝው ሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ ከአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ጎን እንድትቆም ጥሪ ቀርቧል።
5ኛ) በስተመጨረሻም የአማራና የኢትዮጵያ ህዝብ ዘብ የሆንከው ጀግናው የአማራ ፋኖ ከህዝብህ ጋር የጀመርከውን የነፃነት ጉዞ አጠናክረህ እንድትቀጥል ጥሪ እያቀረብን የአማራ ህዝባዊ ግንባር በቀጣይ ሁለት ቀናት ውስጥ ላልተወሰነ ጊዜ የማቆይ ኮማንድ ፖስት የሚያቋቁም መሆኑን ይገልፅል።
ኮማንድ ፖስቱ በመላው የአማራ ከተሞች የሚተገበር ሆኖ የአማራን የህልውና የነፃነት ትግሉን ማቀጣጠልና ነፃ የወጡትን የአማራ የቀበሌ፣የወረዳ፣የዞን አውራጃዎችንና ከተሞችን በሚቋቋመው ኮማንድ ፖስት በተመደቡ የአማራ የትግል አካላት እንዲተዳደሩና ህዝቡም አካባቢውን እንዲጠብቅ ደንብ ተዘጋጅቷል።በተጨማሪም ስለንብረትና እስረኛ አጠባበቅን በተመለከተ በኮማንድ ፖስቱ ተካቶ ደንቡ ይፋ ይሆናል።
ድል ለአማራ ህዝብ
ሐምሌ/28/2015 ዓ.ም
የአማራ ህዝባዊ ግንባር
Filed in: Amharic