>

አማራ ድንበር ባስከበረ፤ አማርኛ ባስተማረ፤ እህል ባሳደገ፤ ደበኛ ነው ??!! ( አሥራደው ከካናዳ )

አማራ ድንበር ባስከበረ፤ አማርኛ ባስተማረ፤ እህል ባሳደገ፤ ደበኛ ነው ??!!

 ከካናዳ አሥራደው 

አይሁድ ህዝብ፤ በጀርመን ናዚ ሲጋዝ የአማራ ህዝብ፤ በናዚው አብይ አህመድ ሲጋዝ

ማስታወሻ፤

« ከአማራ ቆዳ በተሠራ ከበሮ: ጭፋሮ !! » በሚል ርዕስ በሁለት ክፍል ባቀረብኩት መጣጥፌ፤ በደቡብ አፍሪካ ህወሃትና (ኦህዴድ/ኦነግ) በዳቦ ስሙ ብልጽግና  ያደረጉት፤ የሠላም ስምምነት ሳይሆን፤ በሌላ ጦርነት አማራውን በጋራ ሆነው ለመዘንጠል ቀጠሮ የያዙበት፤ እንደሆነ አመላክቼ ነበር :: በጥቂቱ ለማስታወስ ያህል:

የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲያውቅ የሚያስፈልገው፤ ሁለቱ አምባ ገነኖች፤ ህወሃትና አሽከሮቹ የብልጽግ ተብዬ (ኦህዴድ/ኦነግ ) ጥርቅሞች፤ ያደረጉት እርቅ ወይም ስምምነት ሳይሆን፤ ለሌላ ጦርነት ቀጠሮ ፤ ይዘውልን ነው የተለያዩት እንጂ፤ እርቀ ሠላም አላወረዱም :: ………..

ባጭሩ፤ የህወሃትና ብልጽግና፤ (ኦህዴድ/ኦነግ/) ጥርቅሞች፤ ላይጣሉ ተጣልተው፤ ላይታረቁ ታረቁ  እንጂ ሠላም አላወረዱም ::  ……………………………..

ህወሃትና ብልጽግና፤ (ኦህዴድ/ኦነግ ) የተጣሉት፤ ለጎሣ የበላይነት፤ ለስልጣን ሽሚያና ለአገር ሃብት ዘረፋ ሲሆን፤ በደቡብ አፍሪካ ያደረጉት አንድ ትልቅ ደባ ደግሞ፤ አማራውን በጋራ ዘንጥለውና፤ ቀረጣጥፈው ለመብላት፤ ጥርሶቻቸውን ለመሞረድ የጊዜ መግዣ ለማግኘት ሲሆን፤ ታረቅን በሚል ቧልት በደቡብ አፍሪካ ጥርሶቻቸውን ጉራይማሌ ተነቅሰው ተመለሱ እንጂ፤ ዘላቂ ሠላም አላወረዱም ::

አንባቢ በነዚህ ማስፈንጠሪያዎች በመጠቀም ሙሉውን መቃኘት ይችላል ::  

ክፍል አንድ፤ https://amharic-zehabesha.com/archives/178164

ክፍል ሁለት፤ https://ethioreference.com/archives/34220

አሁንም እየሆነ ያለው ይኸው ነው ::  

መንደርደሪያ፤

  • « የጨው ተራራ ሲናድ፤ ሞኝ ይስቃል ብልህ ይጨነቃል » አገርኛ ብሂል
  •  « La vie, c’est comme la bicyclette il faut avancer pour ne pas perdre l’équilibre. » Albert Einstein

 « ህይወት ልክ ብስክሌት እንደመንዳት ናት፤ ላለመውደቅ ወደፊት መፍጠን ያሻል » አልበርት አነስታይን

  • « L’ignorant affirme, le savant doute, le sage réfléchit ».  Aristote 

« አላዋቂ ይደነፋል፤  ምሁር ይጠራጠራል፤ ብልህ ያሰላስላል፤ ያስባል፤ ያጤናል »   አሪስቶትል

  •  La vérité est en marche et rien ne l’arrêtera. Emile Zola

« ሃቅ በመጓዝ ላይ ናት ፤ የሚያቆማት: ምንም ሃይል ወይም ተዓምር አይኖርም » ኤሚል ዞላ

መግቢያ፤

አማራ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ወገኖቹ ጋር በመሆን፤ አጥንቱን ከስክሶ ደሙን አፍሶ በተደጋጋሚ በተደረጉ ጦርነቶች፤ የአገሩን ድንበር አስከብሯል:: ያም ሆኖ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ወገኖቹ፤ የተለየ ጥቅምና ድሎት ሳይጠይቅ፤ አብዛኛው የአማራ ነገድ፤ ሰርዶውን ነቅሎ አርሶና ዘርቶ፤ የቻለው ነግዶና ከብት አርብቶ፤ ሲከፋውም ከተወለደበት መንደር፤ ወደ ሌሎች ክፍላተ ሃገራት ተሰዶ፤ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ወገኞቹ ጋር ተጋብቶ፤ ተዋልዶ፤ የራሱን ባህልና ዕሴቶች አካፍሎ፤ የሌሎች ወገኖቹንም በመቀበል፤ ደስታንም ሆነ ሃዘኑን በአብሮነት ተካፍሎ እንደኖረ ታሪኩ ይመሰክራል::

የኢትዮጵያ ህዝብ ከአንዴም ሁለቴ፤ በነጮች ላይ ያረደሰባቸው ሽንፈትና፤ የተጎናጸፈው ድል በእጅጉ ያስቆጫቸው ነጮች፤ የመጽሐፍ ቅዱስ መልክተኞችን (ሚስዮናዊያን) መጽሐፍ ቅዱስ በእጃቸው አስይዘው፤ መስቀል በአንገታቸው አጥልቀው፤ ወደ ኢትዮጵያ በመላክ፤ በአማራው ላይ የነበራቸውን የጥላቻና የዘረኝነት ስብከት፤ ለሌሎች ጎሣዎች ወንድሞቻችንና እህቶቻችን፤ በመርዝ እየጠቀለሉ አጉርሷቸዋል:: 

እንግዲህ ከታሪክ ለመማር፤ ፍላጎቱ ላላቸው ዕውነታው ይህ ሲሆን፤ የነጮቹን ስብከት እየተጋቱ ተጣመው ላደጉት ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ደግሞ፤ አማራ ጨቋኝ ገዢ፤ ሥልጣን ለብቻው ይዞ የቆየና: በነሱ አባባል የሰበረን፤ እየተባለ አዲሱን ትውልድ በማደንቆር፤ በዘረኝነትና በጥላቻ፤ በጎሣ አጥር ከልለው፤ ከሌሎች ወንድሞቹና እህቶቹ ጋር፤ አብሮ በመከባበር እንዳይኖር፤ ዓይኖቹን በጎሣ ቡሉኮ ጋርደው፤ የማደንዘዣ መርፌ እየወጉት ይገኛል::  

ይባስ ብለው እራሳቸው ተምረው ዓይኖቻቸውን እንደቡችላ የገለጡበትን የአማርኛን ፊደልና የአማርኛን ቋንቋ፤ አዲሱ ትውልድ እንዳይማርና እንዳይናገር፤ በመከልከል፤ የጀርመኑ ሚስዮናዊ በፈበረከው የላቲን ፊደል፤ ቁቤ ብቻ እንዲማሩና፤ ኦሮምኛ ብቻ እንዲናገሩ፤ ተፈርዶባቸዋል:: 

እንግዲህ የኦሮሞ ኤሊቶችና ካድሬዎች እድገት የሚሉት፤ ይኸን ትውልድ ገዳይና አገር የሚያነጥፍ፤ ስርዓተ ትምህርት ነድፈው በመተግበር ነው:: 

እህል በልቶ፤ ሳር ነጭቶ፤ ያላደገ ፍጡርና እንስሳ ባለመኖሩ ስለ እህል፤ ጠቃሚነት ከመዘርዘር፤ ሆድ ይፍጀው ብዬ አልፌያለሁ::

እናም !  ማራ ድንበር ባስከበረ፤ ማርኛ ባስተማረ፤ ህል ባሳደገ፤ ደበኛ አለመሆኑን፤ በደንብ ተረዱት!!

አማራን ፍቅር እንጂ፤ ጦር እንደማያሸንፈው፤(እንደማይገዛው) የዛሬዎቹ የአስተሳሰብ ድንክዬዎች ወይ አልተረዱም፤ ወይም እንዳይገባቸው: የአይምሯቸውን በርና መስኮት ጥርቅም አድርገው በመዝጋት፤ በጎሣ አጥር ታጥረው ያንኮራፋሉ:: 

 አማራ በአገሩ፤ በሃይማኖቱና በሚስቱ ከመጡበት ደሙ መራራ እንደሆነ መረዳት ከፈለጋችሁ ታሪኩን መለስ ብላችሁ አገላብጡ::  እነዚህ ሦስቱ ምሰሶዎች ደግሞ የኢትዮጵያዊነት መገለጫዎቹ ናቸው :: ካላወቃችሁ ጣሊያንን ጠይቁት፤ የደረሰበትን በደንብ ዘርዝሮ ይነግራችኋል :: 

መቼም እናንተ፤ ነጮች ሲሰብኳችሁ እንጂ፤ ጥቁሮች ወገኖቻችሁ ሲነግሯችሁ፤ ጆሯችሁ በሃሰት ትርክት የደነቆረ፤ ልባችሁ በጥላቻ የጠቆረ በመሆኑ፤ የመማር ፍላጎታችሁም ሆነ አቅማችሁ ውሱን ነው :: 

እናንተ፤ ከፍቅር፤ ከወንድማማችነት፤ ከአብሮነትና ከእኩልነት ተጣልታችሁ፤ ከዘረኝነት፤ ከጎሠንነት፤ከሌብነትና ከቅጥፈት ጋር ቁማር መጫወት ስለ ለመዳችሁ ከታሪክ መማር አይሆንላችሁም::

 ከታሪክ በመማር፤ የትናንቱን አጢኖ እውቀት በመቅሰም፤ የዛሬውን መደላድል በመዘርጋት፤ የነገውንና የወደፊቱን አቅጣጫ በመተለም፤ የአገር ዋልታዎችን በማስጠበቅ፤ የህዝብን ተስፋ በመሰነቅ፤ ህዝብን ለጋራ ጥቅሙና ክብሩ አጎናጉኖ፤ ለነፃነቱ አብሮ ዘብ እንዲቆም በማድረግ ፋንታ፤ እናንተ በስልጣን ላይ ለመቆየት ስለፈለጋችሁ ብቻ፤ ዓይኖቹን በጎሣ ቡሉኮ ጋርዳችሁ፤ እርስ በርሱ በማባላት ወደ መቃብር  ትጎትቱታላችሁ:: 

ሰሞኑን አንድ የሽመልስ አብዲሳ ተላላኪ ካድሬ፤ ወደ መቀሌ ሄዶ፤ በአሸንዳ በዓል ላይ፤ ለቀድሞ  የህወሃት አሳዳሪዎቹ ያደረገውን፤ አማራን አብረን  ሆነን እንዘንጥል ጥሪ፤ ሰምተናል:: የአማራ ሕዝብ ከአሁን በኋላ፤ የማንም ደንቆሮ አፍ ማሟሻ እንደማይሆን፤ ይችን የቀድሞ ጀግኖቻችን፤ የፋኖዎች ስንኝ ጋብዣችኋለሁ ::

« የማን ቤት ፈርሶ – የማን ሊበጅ፤

ያ’ውሬ መፈንጫ – ይሆናል እንጅ »

እንግዲህ፤ ልብ ያለው ልብ ይበል!!   

የኦሮሞ ህዝብ ከሚታወቅባቸው ሸጋ ባህሎቹ መሃከል አንዱ፤ ጉዲፈቻን  ብንጠቅስ እንኳ፤ የኦሮሞ ህዝብ ከራሱ ልጆች አልፎ፤ የሌሎች ወገኖቹን ልጆች ወስዶ፤ እንደራሱ ልጆች ወተት እያጠጣ አሳድጎ የሚድር፤ ሩህሩህና ደግ ህዝብ እንጂ፤ እንደናንተ የገዛ ወገኑን የሚያፈናቅልና የሚያርድ፤ ጨካኝና አረመኔ አለመሆኑን፤ አብዛኞቻችን እናውቃለን::

ማሳረጊያ፤

ለኦሮሞና ለትግራይ፤ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን፤ እንዲሁም ለመላው ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን፤ 

ለእኛ ለኢትዮጵያውያን፤ የጦርና የረሃብ አዙሪት ፈጣሪዎች፤  ዘወትር በተንኮል የተካኑ፤ የፖለቲካ እንጎቻ፤ ከመጋገር በስተቀር፤ ሠርተው የሚበሉበት፤ ሌላ ምንም ዓይነት ሞያ የሌላቸው፤ የአይምሮና የአካል ሰንካላዎች ስብስብ መሆናቸውን ተገንዝበን፤ በአንድላይ በቃ ልንላቸው ይገባል ::

ልጇን ይጦረኛል ብላ ስታስተምር የነበረች የትግራይ እናት፤ እነዚህ የአይምሮ ሰንካላ ፖለቲከኛች፤ በለኮሱት ጦርነት፤ ዛሬ በተቃራኒው፤ እናት አካለስንኩል ልጇን በጋሪ ትገፋለች:: አንድ ልጁን አፈር እየገፋ ያስተምር የነበረ፤ የአማራ አርሶ አደር አባት፤ እነዚህ የአይምሮ ሰንካላ ፖለቲከኛች በጫሩት ጦርነት፤ ልጁን በጦርነት ተነጥቆ፤ ዛሬ ቤቱ ጭር ብሏል ::

እነዚህ የአይምሮ ሰንካላ ፖለቲከኛች በለኮሱት ጦርነት፤ በብዙ ሚልዮን የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ዛሬ በገዛ አገራቸው ስደተኞች ሆነው ይንከራተታሉ::

እነዚህ የነጠፈ አይምሮ ያላቸው፤ ሰንካላ ፖለቲከኛች፤ ባነደዱት የጦርነት እሳት እየተለበለቡ፤ በብዙ ሚልዮን የሚቆጠሩ ወገኖቻችን፤ ዛሬ በረሃብ እንደ ቅጠል ይረግፋሉ:: እነሱ ግን ዛሬም በስልጣን ላይ ሙጥኝ ብሎ ለመቆየት፤ የጦርነት አታሟቸውን ይጎስማሉ :: 

እነዚህ የፖለቲካ ዝሙተኞች በለኮሱት ጦርነት፤ በአማራ፤ በወላይታ፤ በሲዳማ፤ በሱማሌ፤ በጉራጌ፤ በጉጂ፤ በከንባታና ሃድያ፤ በጋሞ፤ በኮንሶ ….ወዘተ. የአገራችን ህዝብ እንደቅጠል ረግፏል:: አገራችን በልጆቿ ደም አከላቷን ታጥባለች፤ የአገራችን ኢትዮጵያ ምድር በደም ጨቅይቷል፤ የአገራችን ወንዞች የልጆቻችንን ደም ቀላቅለው ይፈሳሉ፤ በውሃ ሳይሆን በልጆቻችን ደም ተዘርቶ የሚበቅል ዕህል ለመብላት፤ የምንሰለፍበት ቀኑ ተቃርቧል !!

ይህ እንዳይሆን፤ እርስ በእርሳችን የሚያባሉንን፤ የነጠፈ አይምሮ ባለቤት የሆኑ፤ ሰንካላ ፖለቲከኞችን፤ ሁላችንም ተባብረን፤ በአንድላይ በቃ ልንላቸው ይገባል !!!  

የምንታገለው ለጥገና ለውጥ ሳይሆን፤  ለስር ነቀል፤ የሥርዓት ለውጥ በመሆኑ፤ ሁላችንም  ለመብታችን አብረን  ዘብ እንቁም ::

አምባ ገነኖች ድንፋታ እንጂ፤ በህዝብ  ፊት የመቆም  ሃይልና ብርታት የላቸውምና አንፍራ ::

ህዝብ ያሸንፋል !!  

እኛ ኢትዮጵያውያን ከተለያዩ ጎሣዎች የተወለድን ብንሆንም፤ የአንዳችን ጎሣ፤ ከሌላው ጎሣ ጋር የሚጋመድበት ብዙ ዕሴቶችና ባህሎች አሉን:: ልዩነታችን አብረን የምንደምቅበት ጥበባችን ሲሆን፤ ኢትዮጵያዊነት ደግም የምንላበሰው የጋራ ካባችን ነው:: 

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!

ነፃነት፤ እኩልነትና ወንድማማችነት ይለምልም !!

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ህዝቧን ይባርክ !! 

 

Filed in: Amharic