>

ለአማራ ወልቃይት የማትዋጥ የማትተፋ የጉሮሮ ውስጥ አጥንት ናት!!! ለእነ አሰብ ኬኛ!!!

ለአማራ ወልቃይት የማትዋጥ የማትተፋ የጉሮሮ ውስጥ አጥንት ናት!!!

ለእነ አሰብ ኬኛ!!!

ፂዮን ዘማርያም (ኢት-ኢኮኖሚ /ET- ECONOMY)

ኮነሬል አብይ አህመድ ወልቃይት የህልውና ጥያቄ ሲሆን የባህር በር የህልውና ጥያቄ ነው ብሎ አጀንዳ መቀየር ምሁራዊ ኢ-ታማኝነት ነው!!! አዲስ አበባ ኬኛ ያለ፣  ድሬዳዋ ኬኛ ያለ፣ አሰብ ኬኛ አይልም ማለት ዘበት ነውና!!!

ኮነሬል አብይ አህመድ ለኢትዮጵያ የባህር በር የህልውና ጥያቄ ነው፡፡ ለኤርትራ የኢትጵያ አየር መንገድን ሠላሳ በመቶ ወይም የታላቁን ህዳሴ ግድብ የተወሰነ ድርሻ ስጥተን የአሰብ ወደብን መያዝ አለብን፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ብዛት ከ120 ሚሊዮን እጥፍ ይሆናል፡፡ ኢትዮጵያ ያለወደብ መኖር አትችልም፡፡

በሠላም ወይም በጦርነት ወደብ ማግኘት አለብን፡፡ የዶክተር ዮናስ ብሩ በኮነሬሉ ሃሳብ አምነውና ተረተዋል፡፡ በአጠቃላይ በኮነሬሉ መነሻ ሃሳብን በመደገፍ የራሳቸውን መነሻ ሃሳብ በማቅረብ ድጋፋቸውን ገልጸዋል፡፡ ኮነሬል አብይ አህመድ ‹‹ወልቃይት ኤርትራ ያለማል›› ጠ/ሚ/ በርዕዬት ሚዲያ በቀረበው መሠረት ወልቃይትን ለኤርትራ ሰጥቶ አሰብን ለመቀበል የኮነሬሉ የመጀመርያ ሃሳብ መሆኑን ለማወቅ ይቻላል፡፡ ታዲያ ሃሳቡ የኮነሬሉ ወይስ የዶክተሩ ወይስ ግጥምጥሞሸ

የዶክተር ዮናስ ብሩ ምሁራዊ ኢ-ታማኝነት (Intellectual dishonesty) ቁልጭ ብሎ የወጣበት የውይይት መድረክ  በኢትዮ ቮይስ ኔት ወርክ (Ethio Voice Network) የጦፈ ክርክር/ በአበበ ገላውና ዶክተር ዮናስ ብሩ ወልቃይትን ለኤርትራ ሰጥቶ አሰብን ከትግራይ ጋር ለማዋሃድ ባቀረበው አወዛጋቢ ሃሳብ ላይ የተደረገ ሙግት አደመጥን፡፡ በኮነሬል አብይ አህመድ የማዘናጋት አጀንዳና አቅጣጫ ማስቀየሻ ዶክተሩ አብሮ  በመፍሰስ ያለውን ተጨባጭ የኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ በምንም መንገድ የማዘናጋት ኃይል እንደሌለው አጀንዳ መቅረጽና የማስቀየስ ኢምንት የኃይል ስበት የሌለው  መሆኑን በመገንዘብ እችን ጹሑፍ አበረከትን፡፡  

 የዶክተር ዮናስ ብሩ ሙሉ ጽሑፉን ለማንበብ ቀጥሎ ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ።

The Question of Port 9 Nov 2023 Final 12

Filed in: Amharic