>
5:18 pm - Sunday June 15, 6684

የአዲስ አበባ ህዝብ ዝምታ፤ ፍርሃት ወይስ ------?

የአዲስ አበባ ህዝብ ዝምታ፤ ፍርሃት ወይስ ——?


መገደልም ሆነ መግደል አልፈልግም፤ ከሁለት አንዱን እንድመርጥ ከተገደድኩ ግን ያለጥርጥር  ከምገደል፤ አገላለሁ።”  (ስሙን የዘነጋሁት አይሁዳዊ ፈላስፋ)  የዘመኑ ገዥዎቻችን  ”እንገላችኋላን ! እናጠፋችኋለንብለው ተነስተዋ፤ በተግባርም  አሳይተውናል፤ እያሳዮንም  ነው። ታዲያ መልስ  ምን መሆን አለበት?

በተለይም የአዲስ አበባን ሁኔታ ሳስብ፤ በአሥራ ስምንተኛው ክፍለ ዘመን የነበረው፤ የነባር አሜሪካን ወይም የቀይ ኢንዲያና ‘’የሞድክ’’  ነገድ ባላባት፣  ስለ ወራሪ አውሮፓዊያን የተናገረውን ያስታውሰኛል፤

አውሮፓዊን ወደ አገራችን  ሲመጡ ብዙ ቃል ገብተውልናል፤ ከገቡት ቃል ሁሉ ግን በተለይም አንዱን ፈጽመውታል።መሬታችሁን እንወስደዋለንብለው ነበር፤ አዎቃል እንደገቡት መሬታችን ወሰዱት።ነበር ያሉት።  

ኦነጋዊብልጽግናም  የአዲስ አበባንዲሞግራፊእንቀይረዋለን ወይም ከጥቅም ውጭ እናደርጋታለን ብለው ቃል በገቡት መሰረትቃላቸውንአየፈጸሙ ይገኛሉ።ግን   የኢትዮትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የኦሮሚያና የሸገር ዋና ከተማ ህዝብ እንዲት ይኽን ሊፈቅድ ቻለ?

አዲስ አበቤ ከሌላው አካባቢ በተሻለ ደረጃ የመደራጀት፣ የመናበብ አቅምና መብቱን የማስከበር ችሎታ  አለው።  የገዥዎቻችን ሰምቶ አዳሪዎችም ሆነ አቀንቃኝካድሪዎችየማያታልሉት፤ ከወያኔ ዘመን ጅምሮ  የጎሳን ፓለቲካ አደገኛነት የተረዳና አንቅሮ የተፋ ነው።  ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊነቱም ብዙ መሰዋአትነት የከፈለ ህዝብ ነው።ይሁን እንጂ  የፍርሃት ይሁን  በኑሮ ውድነት መደንዘዝ ወይም በአንድነትና በኢትዮጵያዊነት ስም  በሚነግዱ የፓለቲካ  ሆድአደሮች በመከዳቱና  ከጎሳ ገዥዎቻችን ጋር በማበራቸው የህዳር አህያ”  ለመሆን በቅቷል።  ግን እስከመቼ?

የአዲስ አበባ  ህዝብ  የተቀጣጠለውን ትግል  ከአሁኑ  በመቀላቀል የራሱንም ሆነ የኢትዮጵያዊንን ህልውና  ብሎም ገዥዎቻችን  በያቅጣጨው የሚያደርሱት የዘር ፍጅት  ከቁጥጥር ውጭ  ሳይሆን  ከሌሎች ወገኖቹ ጋር በመሆን መታደግ ይችላል።

በብልጽግና ገዥዎቻችን ዘነድ የአዲስ አበባ ህዝብየአዲስ አበባ ህዝብ አይደለም መጤ ነው። ኗሪ ነው። ዜግነት የለውም። ማንኛውም የመኖር ሆነ የመስራት መብቱ የሚወሰነው በተረኞቹ የኦነጋዊብልጽግና ገዥዎቻችን በጎ ፈቃድ ብቻ ነው። መጤ  መብት የለውም፤ መጤ ማለት ውጣ ሲባል የሚወጣ፣ ግባ ሲባል የሚገባ፤ የገነበው ቤት በላዩ ላይ የሚፈርስበት፣ በላቡ የሰበሰበው ኃብትና ንብረት የሚወረስበትና የሚዘረፍበት ፤ልጆቹ የገዥዎችን ቋንቋ ካልተማሩ (ቋንቋ መማር በግዳጅ  ወይም የሌለውን ቋንቋ ለማጥፋት እሰክ ካለሆነ ድረስ ጥቅም እንጅ ጉዳት የለውም።) በቀር  ከትምህርት ቤት የሚባረሩበት፤  በአጠቃላይ  ከሰው በታች ከሞቱት በላይየአፓርታይድአገዛዝ  ውስጥ  ከወደቀ ዓመታትን አስቆጥሯል።

ግን እንዴት? —-የአዲስ አበባ ህዝብ ለዘመናት ተሳስሮና ተጋምዶ የኖረ፤  በኢትዮጵያ የፓለቲካ ትግል ውስጥ  ከአዲስ አበባ ዮኒቨርስቲ  ጀምሮ የአምበሳውን ድርሻ  የሚይዝ፣ በአንደነት በመታገል  ለሌሎች ከተሞችና አካባቢዎች  አርያ የነበረው ህዝብ፤ እንዴት ዛሬ  ኢትዮጵያዊነቱ ተገፎ፣ ማንነቱ ተዋርዶና ተንቆ፤  ልጆቹን በጅብ ሳይቀር እያስበላ ለመኖር ፈቀደ?

እንዴት ሃይማኖቱንና አገራዊ የድል ቀኑን ማክበር እንኳን ተከለከል? እንዴት ሰንደቅ ኣላማውን እንኳን በመሰለው መልክ መጠቀም የሚያስገድለው ሆነ? እንዴት ከአገራችን ህዝብ ሁሉ ለዘመናዊነት፡ ለስልጣኔና መብቱን ለማስከበር ቅርብና ችሎታው ያለው በሚልዮን የሚቆጠር ህዝብ ከሌላ አካባቢ በመጡ ገዥዎች እንደ እቃ እየቆጠሩና እያንቋሸሹ በኑሮ ውድነት አይጠበሱ ሲገዙት አሜን ብሎ ተቀበለ?
በዚች ሰዓት እንኳን በተለያዩ የአገራችን ከተሞችና መንደሮች ከአገዛዙ ጋር እየተናናነቁ ያሉ የወገኖቹን ትግል እየሰማና እያየ ዝም ብሎ መረገጥንና መጨቆንን መረጠ?

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኖራለች!!
ፊልጶስ

Filed in: Amharic