ፋኖወች የተሰውባቸውን ቦታወች በስማቸው የመሰየም አማራዊ ግዴታ!
መስፍን አረጋ
በጭራቅ አሕመድ የሚመራው የኦነግ አውሬ ሠራዊት አማራን ቆርጣጥሞ ሊጨርሰው አፉ ውስጥ ካስገባው በኋላ፣ ፋኖወች በድንገት ተነስተው የጭራቁ ጥርሶች የሆኑትን ብአዴኖችን በመነቃቀል ያማራን ሕዝብ ተቆረጣጥሞ ከማለቅ እያዳኑት ይገኛሉ። በዚህ አካሄዳቸው ከቀጠሉ ደግሞ የጭራቁን ጥርሶቸ መነቃቀል ብቻ ሳይሆን ራሱን ጭራቁን በመመንገል ያማራን ሕልውና ቀጣይነት ባጭር ጊዜ ውስጥ እንደሚያረጋግጡ ሳይታለም የተፈታ ነው።
ይህ ሁሉ የተገኘው ግን በከፍተኛ መስዋእትነት ነው፣ ነጻነት ነጻ አይደለምና፡፡ ስለዚህም ያማራ ሕዝብ እሱን ለማዳን ሲሉ ራሳቸውን የሰውትን የቁርጥ ቀን ልጆቹን ለዘላለም ሊያከብራቸውና ሊዘክራቸው ይገባል፣ ጀኞቹን የማያከብር ሕዝብ ጀግና ሊፈጥር አይችልምና።
ፋኖወች ለዛላለም ሊከበሩና ሊዘከሩ ከሚችሉባቸው መንገዶቹ ውስጥ አንዱና ዋናው ደግሞ የተሰውባቸውን ቦታወች በስማቸው መሰየም ነው። ቦታወችን በፋኖ ጀግኖች ለመሰይም ደግሞ ምንም ችግር የለም፣ መሰየም በሌለባቸው ስሞች የተሰየሙ አያሌ ቦታወች አሉና።
በግራኝ ወረራ ዘመን ያማራ ሕዝብ ታላላቅ የጦር መሪወቹን አጥቶ አለቅጥ በመዳከሙ ለሉባ ተስፋፊ ሠራዊት ከፍተኛ እድል ተከፈተለት። ይህ አረመኔ ሠራዊት የግራኝ አሕመድን ጭራ እየተከተለ፣ ከግራኝ ጭፍጨፋ የተረፉትን አማሮቸ ያለርህራሄ እየጨፈጨፈ፣ ባብዛኛው ያማራ መሬት ላይ ዘለነበትና (ዘላን ሆነበትና) የቦታወቹን ስም እየቀየረ ቢሸፍቱ፣ ዱከም፣ ጉለሌ፣ ሰላሌ፣ ወረኢሉ፣ ወረባቦ እያለ ሰየማቸው። ያማራ ሕዝብ ደግሞ በራሱ የሚተማመን ኩሩ ሕዝብ በመሆኑ ተስፋፊውን ከገፋው በኋላ የቦታወቹ በተሰፋፊው ስያሜወች መሰየም ምንም ችግር የለውም በሚል እሳቤ ወደ ቀድሞ ስማቸው ሳይመልሳችው ቀረ።
የዘመናችን የኦነግ አረመኔ ሠራዊት ግን፣ ቦታወቹ በኦሮምኛ በመሰየማቸው ብቻ የኦሮሞ ናቸው አለና፣ አማራን በመጤነት ፈረጀ። በዚህ ፍረጃው መሠረት ደግሞ አማራን እንድ ከብት ማረድና ከአርድ የተረፈውን ደግሞ እያፈናቀለ ማባረር ጀመረ።
ስለዚህም ለአማራ ሕዝብ በኦንጋውያን መጨፍጨፍ በተወሰነ ደረጃ ተጠያቂው ራሱ ያማራ ሕዝብ ነው። ያማራ ሕዝብ ተሰፋፊው የፈጠራቸውን ዳኀራዊ (ኋለኛ) ስሞች ሙሉ በሙሉ አስወግዶ ቀደምት ስሞችን ቢጠቀም ኖሮ፣ ኦነጋውያን በመጤነት እንዲፈርጁት ዕድል ባለከፈተላቸው ነበር።
ነገር ግን፣ ለመጭው እንጅ ላለፈው ክረምት ቤት አይሠራም። አንዴ መሳሳት የዋህነት ሲሆን፣ ሁለቴ መሳሳት ግን ጅልነት ነው። ስለዚህም ያማራ ሕዝብ ዳግም ተሳስቶ ለዳግም ጭፍጨፋ እንዳይዳረግ ከፈለገ፣ ወሎ፣ ወለጋ፣ ጉለሌ፣ ሰላሌ፣ ወረኢሉ፣ ወረባቦ የመሳሰሉትን የተስፋፊ ቃሉች አንዳቸውም ሳይቀሩ ሁሉንም ካማራ ሕዝብ መዝገበ ቃላት ሙሉ በሙሉ ሊፍቃቸው ይገባል ። ፋኖወች ታላቅ ገድል እየፈጸሙ የተሰውባቸውን የውጊያ አውደማወች (ተራሮች፣ ሸለቆወች፣ ሜዳወች) ደግሞ በሰማዕታቱ ስም ሊሰይማቸው ይገባል።
መስፍን አረጋ
mesfin.arega@gmail.com