>

የዳንኤል ክብረት ቅኔ

የዳንኤል ክብረት ቅኔ

 

ጭራቅ አሕመድ ማለት ሥጋ ለብሶ የሚሄድ ውሸት ነው ብሎ ለጦቢያ ሕዝብ መናገር ለቀባሪው ማርዳት ነው።  ይህን ሥጋ ለብሶ የሚሄድ ውሸት የሚያማክረው ደግሞ አቶ ዳንኤል ክብረት ነው።  አቶ ዳንኤል ክብረት ደግሞ ጭራቅ አሕመድን እየሱሴ ብሎ ሞቱንም ሽረቱንም ከጭራቅ አሕመድ ሞትና ሽረት ጋር እንዳይፈታ አድርጎ በጥብቅ አቆራኝቷል።  ጭራቅ አሕመድ ደግሞ እየሞተ ስለሆነ፣ ዳንኤል ክብረትም እየሞተ ነው።  ስለዚህም ዳንኤል ክብረት እስትንፋሱ እስክትወጣ ደረስ መዋሸቱን መቀጠል ብቻ ሳይሆን፣ የውሸቱን ዓይን አውጭነት እየጨመረ ይሄዳል።  ባጭሩ ለመናገር አቶ ዳንኤል ክብረት በውሸት ዝናብ መበስበስ ብቻ ሳይሆን ስለሾቀ፣ የውሸት ፍራቻው ሙሉ በሙሉ ጠፍቶለታል።  ሲዋሽ የሚቆጠቁጠው ሕሊናው ሙቶ ስለተቀበረ፣ ለመዋሸት ገደብ የለውም።   

ዳንኤል ክብረት ገደብ የሌለው ውሸታም ነው ማለት ግን ውነት አይናገርም ማለት አይደለም።  አቶ ዳንኤል ክብረት በመጠኑም ቢሆን ቅኔ ተምሯል።  ያስተማረችው ደግሞ ጭራቅ አሕመድን እየሱሱ ካደረገ በኋላ ሊያጠፋት ቆርጦ የተነሳባት ተዋሕዶ ናት።  ቅኔ ደግሞ ሰም በመጥቀስ ወርቅ መናገር ነው።  ስለዚህም አቶ ዳንኤል ክብረት “ፋኖ ባሌስትራውን ሰብሯል፣ የቀረው ምላስ ብቻ ነው” ሲል በወርቅ የተናገረው ስለ ፋኖ ሳይሆን ስለጭራቅ አሕመድ ነው።  የጭራቅ አሕመድ ጨፍጫፊ ሠራዊት ስለፈራረሰ፣ እሱ (ማለትም ዳንኤል ክብረት) እና ጭራቅ አሕመድ ጣረሞት ላይ እንደሆኑና ግብአተ መሬታቸው በቅርቡ እንደሚፈጸም መርዶውን ለመናገር የፈለገው ለጭራቅ አሕመድ ነው።  ችግሩ ግን የበሻሻው ደንቆሮ ቅኔ አለማወቁ ነው።       

    መስፍን አረጋ                 

mesfin.arega@gmail.com

Filed in: Amharic