እስክንድርን ለማውገዝ በፋኖ ስም የወጣ የመረጃ ቲቪ መግለጫ
“በአራቱ ግዛቶች ያሉ የአማራ ፋኖዎች የጋራ አደረጃጀት እየመሰረቱ መሆኑ ይታወቃል” እያሉ፣ “ከአማራ ፋኖ በጎጃም፣ ከአማራ ፋኖ በጎንደር፣ ከአማራ ፋኖ በሸዋና ከምስራቅ አማራ ፋኖ የተሰጠ የጋራ መግለጫ” ማለትን ምን ይሉታል? ገና ያልተመሰረተ የጋራ ድርጀት የጋራ መግለጫ እንዴት ያወጣል? መግለጫው በጋራ ወጥቶ ከሆነስ፣ መግለጫውን በጋራ አወጡት የተባሉት ፋኖወች አዛዦች ስማቸውን በመግለጫው ሥር ያልዘረዘሩት ማንን ፈርተው ነው? ባለቤቱ ሾላ በድፍን የሆነ መግለጫ ትክክለኛ ባለቤቱ ማን ነው?
________________________________________
ጭራቅ አሕመድ ስልጣን ላይ የሚቆይባት እያንዳንዷ ዕለት ያማራን ሕዝብ ግብአተ መሬት የምታቃርብ የተረገመች ዕለት ናት ። ጭራቅ አሕመድ ያማሮችን ማሕፀን ዘርከቷል ወይም ደግሞ እንዲዘረከት አድርጓል፣ ሽሉን ደግሞ በልቷል ወይም ደግሞ አስበልቷል፡፡ ጭራቅ አሕመድ ያማራ ሕፃናትን ጎጆ ውስጥ ዘግቶ በሰደድ እሳት አንጨርጭሯል ወይም ደግሞ እንዲንጨረጭሩ አድርጓል፡፡ ጭራቅ አሕመድ አማሮችን የፊጥኝ አስሮ ባደባባይ ረሽኗል ወይም ደግሞ አስረሽኗል፡፡ ጭራቅ አሕመድ አማሮችን ባደባባይ ዘቅዝቆ ሰቅሏል ወይም ደግሞ አሰቅሏል፡፡ ጭራቅ አሕመድ አማሮችን አጋድሞ አርዷል ወይም ደግሞ አሳርዷል፡፡ ጭራቅ አሕመድ ያማሮቸን ቆዳ በቁማችው ገፏል ወይም ደግሞ አስገፍፏል፡፡ ጭራቅ አሕመድ ያማሮቸን ሬሳ በሞተር ሳይክል ገትቷል ወይም ደግሞ አስገትቷል፡፡ ጭራቅ አሕመድ አማሮች በግሬደር ቀብሯል ወይም ደግሞ አስቀብሯል፡፡ ጭራቅ አሕመድ ካማራ አስከሬን በተቆረጡ እጆችና እግሮች ሆያ ሆየ ጨፍሯል ወይም ደግሞ አስጨፍሯል፡፡ ጭራቅ አሕመድ ላማራ ተቆርቋሪ አመራሮችን ያለ ርህራሄ ርፍርፏል ወይም ደግሞ አስረፍርፏል፡፡ ጭራቅ አሕመድ ያማራ ከተሞችን አቃጥሎ አውድሟል ወይም ደግሞ አስወድሟል፡፡ ጭራቅ አሕመድ ያማራ ባለሃብቶችን ሐብትና ንብረት ዘርፏል ወይም ደግሞ አስዘርፏል፣ አገራቸውን ጥለው እንዲሰደዱም አድርጓል፡፡ ጭራቅ አሕመድ አማሮችን አፈናቅሎ፣ ከተማ እንዳይገቡ ከልክሎ፣ በርሃ ላይ በትኖ በርሃብና በበሽታ ጨርሷል። ጭራቅ አሕመድ ያማሮችን ቤት አፍርሶ፣ ሜዳ ላይ ጥሎ ጅብ አስበልቷል። ባጠቃላይ ደግሞ ጭራቅ አሕመድ ያማራን ሕዝብ ባንድም በሌላም መንገድ በሚሊዮኖች ቀንሷል ወይም ደግሞ አስቀንሷል፡፡
ስለዚህም፣ ያማራ ፋኖ ሙሉ ትኩረቱን ማድረግ ያለበት ያማራ ሕልውና መቅሰፍት የሆነውን ጭራቅ አሕመድን በማናቸውም አስፈላጊ ዘዴ (by any means necessary) ባስቸኳይ በማስወገድ ላይ ነው። ጭራቅ አሕመድን በማስወገድ ያማራ ሕልውናን መታደግ ማለት ደግሞ ጦቢያን መታደግ ማለት ነው፣ ጦቢያ ያለ አማራ፣ አማራም ያለ ጦቢያ አይታሰቡምና። ያማራ ሕዝብ ጦቢያን ጦቢያ ለማድረግ ያንበሳውን ሚና የተጫወተ፣ ቁጥሩ ከኦሮሞና ከትግሬ ሕዝብ ድምር በሚሊዮኖች የሚበልጥ፣ የኢትዮጵያ ትልቁ ሕዝብ ነውና።
እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ፣ መነሻችን አማራ መድረሻችን ጦቢያ የሚለውን በመቃወም መነሻችንም መድረሻችንም አማራ የሚሉ፣ እስክንድር ነጋን ባንድም በሌላም መንገድ የማስወገድ ልዩ ተልዕኮ ያነገቡ ሰወች፣ የቀሩት ሁሉም ፋኖወች ትኩረታቸውን ከጭራቅ አሕመድ ላይ እንስተው በፋኖ እስክንድር ነጋ ላይ እንዲረባረቡ ነጋ ጠባ እየወተወቱ ይገኛሉ። የነዚህ መነሻችን አማራ መድረሻችንም አማራ የሚሉ እስክንድርን የማስወገድ ልዩ ተልዕኮ ያነገቡ ሰወች ዋና ሚዲያ ደግሞ መነሻው ገንዝብ መድረሻውም ገንዝብ የሆነው መረጃ ቲቪ (Mereja TV) ነው። የመረጃ ቲቪ ዋና አፈቀላጤ ደግሞ በፊት የወያኔ አቃጣፊ የነበረው አሁን ደግሞ የፋኖ አቃፊ ነኝ የሚለው አቶ ግርማ ካሳ ነው።
የመረጃ ቲቪ ባለቤት አንዱና ብቸኛ ችሎታው፣ የኢትዮጵያውያንን ትኩረት በሚስቡ አወዛጋቢ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩሩ ጦቢያነክ ሚዲያወችን ከፍቶ፣ የሚዲያ ዕድምተኞቹ በጦፈ ክርክር ልባቸውን ሲያወልቁ እሱ ቁጭ ብሎ ገንዘቡን መልቀም ነው። ግለሰቡ ገንዘብን በተመለከተ ቋሚ መመሪያው የትም ፍጨው ዱቄቱን አምጨው ነው። የግለሰቡ መነሻውም መድረሻውም ገንዝብ ነው የተባለውም በዚሁ ምክኒያት ነው፣ ለገንዘብ ሲል የማያደርገው የለምና። ከዚህ በተረፈ ግን ግለሰቡ አላዋቂነቱን በትቢተኝነት ለመሸፈን የሚጣጣር፣ ወላጅ አባቱን አባቱ ስለሆኑ ብቻ “ያመቱ ኢትዮጵያዊ” (Ethiopian of the year) ብሎ በመጽሔቱ ሲያስወጣ ትንሽ እፍረት የማይሰማው ከንቱ፣ የከንቱ ከንቱ ግለሰብ ነው።
ይህ መነሻውም መድረሻውም ገንዘብ የሆነ ግለሰብ “ኢትዮጵያን ሪቪው” (Ethiopian Review) የሚሰኝ መጽሔት በደርግ ዘመን ያትም የነበረው፣ የደርግ ዘመን የጦቢያ ችግር አሳስቦት የመፍትሔ አካል ለመሆን ሳይሆን፣ ደርግ ያፍናቸው የነበሩትን ፀርደርግ ጽሑፎች ማውጣት ከፍተኛ ገንዘብ የሚያስገኝ አትራፊ ሥራ ሁኖ ስላገኘው ብቻ ነበር። ለዚህ ደግሞ ሻቢያወች የሚልኩለትን የተገነጣጠለች ኢትዮጵያን ካርታ ከመጽሔቱ የጀርባ ገጽ ላይ (ከውጭ በኩል) በተደጋጋሚ ያወጣ እንደነበር መጥቀስ ብቻ በቂ ነው። እንደዚህ ያለው የገንዘብ ጥመኛ ነው፣ እስክንድር ነጋ የስልጣን ጥመኛ ነው እየተባለ በየዕለቱ እንዲወነጀል ሚዲያወቹን የሚያመቻቸው፣ በተለይም ደግሞ ለግርማ ካሳና ለዘመድኩን በቀለ።
ይህ መነሻውም መድረሻውም ገንዘብ የሆነ ግለሰብ መረጃ ፎረም (Mereja Forum) የሚሰኘውን ፎረም የከፈተው፣ የጦቢያውያን የተለያዩ ሐሳቦች እርስበርስ ተጋጭተው ነጥረው እንዲወጡ በማሰብ ሳይሆን፣ ጥላቻ የሚዘሩ ጽሑፎችን ማውጣት የፎረሙን ታዳሚ በማብዛት የገንዘብ ትርፉን ስለሚያበዛለት ብቻ ነው። ለዚህ ደግሞ በፎረሙ ላይ ያለምንም ገደብ እንደልብ እንዲዋኙና እንዲናኙ የሚያደርጋቸው ባማራ ጥላቻ የሰከሩ የትግሬና የኦሮም ጽንፈኞችን መሆኑን መጥቀስ ብቻ በቂ ነው። ይህ የወያኔንና የኦነግን ፀራማራ ትርክት በፎረሙ ላይ በስፋት የሚያሰራጭ ግለስብ ነው፣ እስክንድር ነጋ ያማራን ሕዝብ ለወያኔና ለኦነግ አሳልፎ ሰጠ እየተባለ ነጋ ጠባ እንዲወነጀል ሚዲያወቹን የሚያመቻቸው፣ በተለይም ደግሞ ለግርማ ካሳና ለዘመድኩን በቀለ።
ይህ መነሻውም መድረሻውም ገንዘብ የሆነ ግለሰብ መረጃ ቲቪን (Mereja TV) የከፈተው፣ ጭራቅ አሕመድ ድምጻቸውን ላፈነባቸው ኢትዮጵያውያን (በተለይም ደግሞ በጭራቅ አሕመድ ለሚጨፈጨፉት አማሮች) ድምጽ ለመሆን አስቦ ሳይሆን፣ ከነዚህ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ገንዘብ መሰብሰብ እንደሚችል ስላወቀ ብቻ ነው። በመሆኑም፣ ከነዚህ ኢትዮጵያውያን ከሚሰበስበው ገንዝብ የበለጠ ገንዘብ የሚሰጠው ካገኘ ሊክዳቸው ዝግጁ ሁኖ፣ አጥር ላይ ተንጠልጥሎ ይጠባበቅ የነበረ ነው። ለዚህ ደግሞ የኢትዮ360 ታዳሚወችን ድምጽ ለማፈን በተሰጠው ልዩ ተልዕኮ መሠረት፣ ኢትዮ360ን ከመረጃ ቲቪ በማስወጣት በምትኩ የብአዴኑን ኢትዮ251 ማስገባቱን መጥቀስ ብቻ በቂ ነው። እንደዚህ ያለው አትዮ360ን በብአዴኑ ኢትዮ251 የተካ ግለስብ ነው፣ እስክንድር ነጋ የብአዴንን ዓላማ ያራምዳል እየተባለ ዘወትር እንዲወነጀል ሚዲያወቹን የሚያመቻቸው፣ በተለይም ደግሞ ለግርማ ካሳና ለዘመድኩን በቀለ።
በመጨረሻም ይህ ኑሮውን በተለያዩ መንገዶች ከዳያስፖራ ገንዘብ በመሰብሰብ ላይ የመሰረተ ግለሰብ ነው፣ እንደሱ አሜሪቃን ቢመርጥ ተንደላቆ ለመኖር የሚችለውን እስክንድር ነጋን ከዳያስፖራ የተሰበሰበ ገንዘብ በላ ተብሎ በስርቆት እንዲወነጀል ሚዲያወቹን የሚያመቻቸው፣ በተለይም ደግሞ ለግርማ ካሳና ለዘመድኩን በቀለ።
በቅርብ ጊዜ (May 22, 2024) ዘሐበሻ (Zehabesha) ድርገጽ (website) ላይ የተለጠፈው መግለጫ ባማራ ሕዝብ ላይ ለደረሰውና እየደረሰ ላለው ሰቆቃ ሁሉ እስክንድር ነጋን ዋና ተጠያቂ የሚያደርግ መግለጫ ነው። የመግለጫው ርዕስ ደግሞ “ከአማራ ፋኖ በጎጃም፣ ከአማራ ፋኖ በጎንደር፣ ከአማራ ፋኖ በሸዋና ከምሥራቅ አማራ ፋኖ የተሰጠ የጋራ መግለጫ ” የሚል ነው። እስከምናቀው ድረስ ደግሞ የጎጃምን፣ የጎንደርን፣ የሸዋንና የምሥራቅ አማራ ፋኖወችን የሚያስተባብር አንድ የጋራ ቡድን ገና ስላልተፈጠረ፣ ያልተፈጠረ ቡድን መግለጫ ሊያወጣ አይችልም። መግለጫው በጋራ ወጥቶ ከሆነ ደግሞ ተአማኒነት ይኖረው ዘንድ መግለጫውን በጋራ አወጡት የተባሉት የጎጃም፣ የጎንደር፣ የሸዋና የምሥራቅ አማራ ፋኖወች አዛዦች በመግለጫው ሥር ስማቸውን ይዘረዘሩ ነበር። ስለዚህም መግለጫው ባለቤቱ በግልጽ ሳይቀመጥ በደፈናው የወጣ መግለጫ ነው።
ይህ ሁሉ የሚጠቁመው ደግሞ መግለጫውን ሊያወጣው የሚችለው እስክንድርን ከጨዋታ ውጭ በማድረግ አተርፋለሁ ብሎ የሚያስብ አንድ የፋኖ ክፍል ብቻውን ወይም ደግሞ እስክንድርን ከጨዋታ ውጭ የማድረግ ልዩ ተልዕኮ ካነገበ የዲያስፖራ ቡድን ጋር በመቀናበር እንደሆነ ነው። የመግለጫው ይዘት ደግሞ የመረጃ ቲቪወቹ ግርማ ካሳና ዘመድኩን በቀለ የእስክንድር ነጋ ስም ለማጥፋት በየጊዜው ከሚጽፉትና ከሚናገሩት ጋር ከሞላ ጎደል አንድ አይነት ነው። ስለዚህም መግለጫው መረጃ ቲቪ በፋኖ ስም ያወጣው መግለጫ ባይሆን እንጅ ቢሆን አያስገርምም። ስለዚህም ይህን መግለጫ በፋኖ ስም የወጣ የመረጃ ቲቪ መግለጫ ማለት ከእውነት የራቀ አይሆንም። የዚህ ጽሑፍ ዓላማ ደግሞ የዚህን በፋኖ ስም የወጣ የመረጃ ቲቪ መግለጫ ዋና ዋና ነጥቦች መቃኘት ነው።
በፋኖ ስም የወጣው፣ መነሻችን አማራ መድረሻችንም አማራ የሚለው የመረጃ ቲቪ መግለጫ “ሕዝባችን የሕልውና ጦርነት ውስጥ የገባው በቅድሚያ ሕልውናውን ለመታደግ ሲሆን በመቀጠልም የፀረ-አማራ ኃይሎች ጥምረት የሆነውን መንግሥት ለመገርሰስ ነው” ይላል። ይህ ታዲያ መነሻችን አማራ መድረሻችን ጦቢያ ከሚለው ከእስክንድር ነጋ መፈክር ጋር በዓላማ በምን ይለያል? ካልተለየ ደግሞ የእስክንድር መፈክር የተወገዘው እስክንድርን ለማውገዝ ሲባል ብቻ ነው ማለት አይቻልምን?
በፋኖ ስም የወጣው የመረጃ ቲቪ መግለጫ፣ መነሻችን አማራ መድረሻችን ጦቢያ የሚለውን የእስክንድር ነጋን መፈከር ሲተች “ እንደዚህ ዓይነት መፈክር ሌሎች ጦቢያውያንን ጥርጣሬ ውስጥ የሚጥል ነው ” ይላል። እስክንድርን ያላመነ ኢትዮጵያዊ ማንን ሊያምን ነው? ባሁኑ ጊዜ አብዛኛው አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ በሙሉ ልብ የሚያምነው፣ የእውነተኛነት ተምሳሌት የሆነ ሰው ከእስክንድር ነጋ በላይ ማን አለ? የሰው ምስክሩ ምግባሩ ነውና፣ እስክንድር ማለት እንደ ወርቅ በእሳት ተፈትኖ የወጣ፣ ከእምነቱና ካቋሙ ዝንፍ እንደማይል በተግባር ያረጋገጠ፣ በስልጣን፣ በጥቅም ወይም በሌላ በማናቸውም መደለያ ሊደለል የማይችል፣ የምዕራባውያን ጉዳይ አስፈጻሚ ይሆናል ተብሎ የማይጠረጠር፣ ሰው በጠፋበት ጊዜ ሰው ሁኖ የተገኘ የሁሉም አገርወዳድ ኢትዮጵያውያን የቁርጥ ቀን ልጅ አይደለምን?
በፋኖ ስም የወጣው የመረጃ ቲቪ መግለጫ፣ ፋኖ የተቆጣጠራቸውን የተለያዩ ከተሞች ለመልቀቅ የተገደደው በእስክንድር ነጋ ምክኒያት ነው ለማለት “በዚህ ግለሰብ ምክንያት የተፈጠረውን ክፍተት ለመድፈን ስንል ከተሞቻችንንና ወገናችንን ለጠላት ለመልቀቅ ተገደድን ” ይላል። እስክንድር ነጋ በፋኖ ትግል ላይ ያለው ተጽእኖ እስከዚህ ድረስ ከሆነ፣ እስክንድር ጦር የለውም ማለትን ምን አመጣው? እስክንድር ጦር የሌለው ከሆነ፣ ጦር በሌለው ግለሰብ ምክኒያት የያዛቸውን ከተሞች የሚለቅ ፋኖ ምን ዓይነት ፋኖ ነው?
በፋኖ ስም የወጣው የመረጃ ቲቪ መግለጫ፣ እስክንድርን ስልጣን ጥመኛ ባሕታዊ በማለት ሊሳለቅበት ፈልጎ “ሰውየው የተወውና የናቀው ሕይወት ካለው ለማይጠረቃ የመንገስ ፍላጎቱ እንጅ ለአማራ ሕዝብ ብሎ መስዋዕትነት እየከፈለ አለመሆኑን አሳይቶናል” ብሏል። ባሕታዊነትና ስልጣን ጥመኝነት ምን አገናኛቸው? ሕይወቱን ለናቀ ባሕታዊ ስልጣን ምን ይተክርለታል? እስክንድርን ባሕታዊ በማለት ሊሳለቅበት የሚሞክረው መግለጫ፣ አቶ ግርማ ካሳ (በእስክንድር ደጋፊነቱና በባንዲራ ወዳድነቱ በሚታወቀው) በአቶ ሺመልስ ለገሰ ላይ ለመሳለቅ ፈልጎ “የፖለቲካ ብስለት የሌለው፣ ምናልባት የጤና ችግር ያለበት ሥራፈት ሰው ነው ” በማለት ባንድ ወቅት ከጻፈው ጋር ተመሳሳይ ነው። ይህ ተመሳሳይነት ደግሞ መግለጫው በፋኖ ስም የወጣ የመረጃ ቲቪ መግለጫ ለመሆኑ ተጨማሪ ማስረጃ ነው።
ያማራ ሕዝብ የሕልውና ጠላቶች ወያኔና ኦነግ ከሆኑና፣ እስክንድር ነጋ በወያኔና በኦነግ ዘመን ወደርየለሽ መስዋዕትነት የከፈለው ወያኔንና ኦነግን በጽኑ በመታገል ከሆነ፣ እስክንድር ለስልጣኑ እንጅ ላማራ ሕዝብ ሲል መስዋዕትነት አልከፈለም ማለትን ምን ይሉታል? ያማራ ሕዝብ የሕልውና ጠላቶች የሆኑትን ወያኔንና ኦነግን ጥሎ ስልጣን ለመያዝ መታገል ኃጢያቱ ምን ላይ ነው? ፋኖ አራሽ፣ ተኳሽ፣ ቀዳሽ በሚለው ላይ ነጋሽ የሚለውን ቃል ዘወትር ሲጨምር የሚታየው ፋኖ እስክንድር ሳይሆን በመረጃ ቲቪ የሚደገፍ ሌላ ፋኖ አይደለም ወይ? ይህ በመረጃ ቲቪ የሚደገፍ ፋኖ፣ አራሽ፣ ተኳሽ፣ ቀዳሽ በሚለው ላይ ነጋሽ የሚለውን መጨመሩስ ምን ስተት አለው? መስዋዕትነት የሚከፈለው ስልጣን ይዞ ዓላማን ለማሳካት አይደለም ወይ? ያማራ ሕዝብ ለዚህ ሁሉ መከራና ፍዳ የተዳረገው ወያኔን ታግሎ ከጣለ በኋላ ስልጣኑን ራሱ እንዳይዝ ለኦነግ አሳልፎ በመስጠቱ አይደለም ወይ?
በፋኖ ስም የወጣው የመረጃ ቲቪ መግለጫ “አቶ እስክንድር ነጋ የአማራ ፋኖን በሰው ኃይልና በፋይናንስ ለማዳከም አዲሱን የገንዘብ መሰብሰቢያ ፕሮጀክቱን በ06/07/2016 ዓ/ም ይፋ አድርጓል” ይላል። “ሕይወቱን የናቀ” በማለት በእስክንድር ነጋ ላይ ለመሳለቅ በሞከረ መግለጫ ላይ “የገንዘብ ማሰባሰቢያ ፕሮጀት ከፈተ” ማለትን ምን ይሉታል? ሕይወቱን ለናቀ ሰው ገንዝብ ምን ይፈይድለታል?
በፋኖ ስም የወጣው የመረጃ ቲቪ መግለጫ አርበኛ እስክንድር ነጋን ሕይወቱን የናቀ በማለት ሊሳለቅበት ከሞከረ በኋላ “ከሕዝባችን ሕልውና በላይ ግለሰባዊ ሕልውናው የሚገዝፍበት፣ ከሕዝባችን ክብር በላይ ግለሰባዊ ክብሩ የሚበልጥበት፣ የሕዝባችንን ትግል ለግልና ለቡድን ጥቅሙ የሚያውል ” በማለት እስክንድርን ይከሰዋል። ሕይወቱን ለናቀ ሰው ክብርና ሞገስ ምን ያደርግለታል? ሕይወቱን ናቀ ማለትስ የግል ጥቅሙን ናቀ ማለት አይደለምን?
በፋኖ ስም የወጣው የመረጃ ቲቪ መግለጫ እስክንድር ነጋን ከብርሃኑ ነጋ ጋር በማጎዳኘት የብርሃኑ ነጋን ኃጢያቶች ሁሉ እስክንድር ላይ ለመከመር በማሰብ “እንደ ግንቦት ሰባት፣ ባልደራስና ሕዝባዊ ግንባር ዓይነት ድርጅቶች የሚፈጽሙትን ማታለል በቅጡ መረዳት ያስፈልጋል” ይላል። እውነታው ግን እስክንድር ነጋና ብርሃኑ ነጋ ያባታቸው ስም ሞክሸ ከመሆኑ በቀር ፍጹም ተቃራኒወች መሆናቸው ነው፣ ዱባና ቅል እየቅል እንዲሉ። ብርሃኑ ነጋ የጭራቅ አሕመድ አሽከር ሲሆን፣ እስክንድር ነጋ ግን የጭራቅ አሕመድ ፀር ነው።
ጭራቅ አሕመድ እስክንድርን የሚፈራውን ያህል ወያኔንም ሆነ ሌላ ማናቸውንም የታጠቀ ኃይል አይፈራም። እስክንድርን ከማንምና ከምንም በላይ የሚፈራው ደግሞ የእስክንድር ጦር ተቀስቅሶ በነቂስ የተነሳ ዕለት፣ አራት ኪሎን እንደ ጎርፍ አጥለቅልቆ ከነግብራበሮቹ እንደሚጠራርገው ስለሚያውቅ ነው። በወያኔም ሆነ በሌሎች ተቀናቃኞቹ ላይ ዝቶ የማያውቀው ጭራቅ አሕመድ እስክንድር ባልደራስን በመሠረተ ማግስት “ግልጽ ጦርነት እንገባለን” ብሎ የዛተውም ለእስክንድር ነጋ ጦር ካለው ፍራቻ ብዛት ነው።
በፋኖ ስም የወጣው የመረጃ ቲቪ መግለጫ አርበኛ እስክንድር ነጋን “በገዳማት ለመነኮሳት መጨፍጨፍ ምክንያት” የሆነ “የደም ነጋዴ” ይለዋል። ባማራ ሕዝብ ላይ የሚፈጸመውን ጭፍጨፋ ለማሳወቅ እተባበሩት መንግስታት ድረስ ሄዶ አቤቱታ ያቀረበው ማን ሁኖ ነው እስክንድር ነጋ ባማራ ሕዝብ ደም የሚነገድ የደም ነጋዴ የሚባለው? እስክንድር ነጋ ለተባበሩት መንግስታት አቤቱታ ሲያቀርብ የመረጃ ቲቪወቹ እነ ግርማ ካሳ የት ነበሩ?
እነዚህ ሁሉ የመግለጫው እርስ በርስ መጣረሶች በግልጽ የሚያሳዩት የመግለጫው ብቸኛ ዓላማ እስክንድር ነጋ ላይ የተገኘውን ጭቃ ሁሉ በመወርወር ቢያንስ አንዱ ተለጥፎበት ስሙን እንዲያጨቀይ መሆኑን ነው። በተጨማሪ ደግም የመግለጫው ርስ በርስ መጣረስ የሚያሳየው፣ መግለጫውን ያወጣው ቡድን አባሎች የእውቀት ደረጃ መናኛ መሆኑን ነው። በእውቅት ያልገፋ ደግሞ በቀላሉ ይታለላል፣ በትንሹ ይደለላል፣ ባሻንጉሊት ይሸነገላል፣ ሣር አይቶ ገደል ይገባል፣ ለቅርቡ ትንሽ ሲል የሩቁን ትልቅ ያጣል፣ መድረሻውን ትልቋን ጦብያ ከማድረግ ይለቅ ትንሿን ወያኔ ሠራሽ ያማራ ክልል ያደርጋል።
በእስክንድር ነጋ የሚመራ፣ መነሻየ አማራ መድረሻየ ጦቢያ ብሎ የተነሳ ያማራ ሕዝብ የሕልውና ትግል አማራ ያልሆኑ ጦቢያውያንን በዙርያው በማሰበሰብ የትግሉን ሜዳ አማራ ክልልን ብቻ ሳይሆን መላዋን ጦቢያን የሚያጠቃልል ሰፊ ሜዳ አድርጎ ፣ በመላዋ ጦቢያ ላይ በሰፊው የተሰራጩትን እልፍ አእላፍ አማሮች በስፋት አሳትፎ፣ የጭራቅ አሕመድን ኦነጋዊ መንግስት መግቢያ መውጫ በማሳጣት ውድቀቱን በከፍተኛ ፍጥነት እንደሚያቃርበው ሳይታለም የተፈታ ነው። ወያኔወችና ኦነጎች በምዕራባውያን አጋሮቻቸው እርዳታ በእስክንድር ነጋ ላይ ከፍተኛ የስም ማጥፋት ዘመቻ የከፈቱትም በዚሁ ምክኒያት ነው።
የምዕራባውያን ዋና ዓላማ ጎጠኝነት ስለሚጸየፍ ለምዕራባውያን ከፋፍለህ ግዛው የማይመቸውን ሰፊውን ያማራን ሕዝብ ቢቻል ሙሉ በሙሉ ማጥፋት፣ ባይቻል ደግሞ ቁጥሩን በጭፍጨፋ፣ በርሐብና በበሽታ በማመናመን፣ ብዛቱ ከኦሮሞና ከትግሬ ሕዝብ ብዛት እጅጉን ያነሰ፣ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ የሚጫወተው ሚና ኢምንት የሆነ አናሳ ብሔረሰብ (minority) ማድረግ ነው። እነዚህ ምዕራባውያን ጥቂት የትግሬ ሴቶች ተደፈሩ ከሚል በመረጃ ካልተረጋገጥ አሉባልታ (unconformed report) ተነስተው ኡኡታውን ሲያቀልጡት እንዳልነበሩ ሁሉ፣ ባማራ ሕዝብ ላይ በቪዲዮ የተደገፈ ከፍተኛ ጭፍጨፋ ሲፈጸም ሰምተው እንዳልሰሙ፣ አይተው እንዳላዩ የሆኑትም ያማራን ሕዝብ በጎጠኞች መጨፍጨፍ በቀጥታና በተዛዋሪ የሚደግፉ አልፎ ተርፎም የሚያስተባብሩና የሚያቀናበሩ በመሆናቸው ነው። ለዚህ ደግሞ ያሜሪቃ መንግስት አመራሮች በተለይም ደግሞ የጦቢያ ጉዳይ በቀጥታ የሚመለከታቸው ሚካኤል መዶሻ (Mike Hammer) እና አለቃው አንቶኒ ብሊንከን (Antony Blinken) በየጊዜው ከሚያወጧቸው ፀራማራ መግለጫወች ውስጥ እንዱን ብቻ መጠቀስ በቂ ነው።
“ያማራ ክልል ኃይሎቹን ከምዕራብ ትግራይ እንዲያስወጣና፣ ምዕራብ ትግራይን ለትግራይ ጊዜያዊ መንግሥት እንዲመልስ የኢትዮጵያን መንግሥት አጥብቀን እንጠይቃለን” (We urge the Government of Ethiopia to withdraw Amhara regional forces from the Tigray region and ensure that effective control of western Tigray is returned to the Transitional Government of Tigray, Press Statement, Anthony J. Blinken, May 15, 2021)
ስለዚህም፣ ወልቃይትና ራያን ለትግሬ ካልሰጣችሁ እያለ ከሚከራከረው ከሚካኤል መዶሻ (Mike Hammer) ጋር ነጩ ቤት (White House) ድረስ በክብር እየተጠራ የሚማከር ማናቸውም አማራን እወክላለሁ የሚል ቡድን ያማራን ጥቅም የሚቸበችብ እንጅ ላማራ ጥቅም የሚሸምት ሊሆን አይችልም።
በፋኖ ስም የወጣው የመረጃ ቲቪ መግለጫ፣ “የፖለቲካ አስተሳሰቡ ወርድና ቁመናው ሊመጥን ከማይችልበት የትግል ሜዳችን ራሱን ማግለል ይኖርበታል” በማለት ለእስክንድር ነጋ ቀጭን ትዕዛዝ ይሰጣል። የመግለጫው ቁልፍ ደግሞ ይህ ቀጭን ትዕዛዝ ነው። እስክንድርን ከትግሉ ሜዳ ማግለል የተፈለገው ደግሞ በመረጃ ቲቪ ሥር የተሰበሳቡት ግለሰቦች አማራን እንወክላለን ብለው ከወያኔና ከኦነግ ጋር ባሜሪቃ አደሪዳሪነት እንዲደራደሩ ነው። አሜሪቃኖች ድርድሩን የሚፈልጉት ደግሞ መነሻውን አማራ መድረሻውን ጦቢያ ያደረገው በእስክንድር ነጋ የሚመራ ትግል፣ ያሜሪቃ ጉዳይ አስፈጻሚ የሆኑትን ጎጠኞቹን ወያኔንና ኦነግን ከኢትዮጵያ ምድር ነቃቅሎ እንዳያጠፋባቸው ስለሰጉ ነው። በፋኖ ስም መግለጫ የሚያወጡ፣ መነሻችንም መድረሻችንም አማራ የሚሉ፣ በመረጃ ቲቪ ሥር የተሰባሰቡ ግለሰቦች ትልቅ የጥያቄ ምልክት ውስጥ መግባት ያለባቸውም በዚሁ ምክኒያት ነው።
ወያኔ እስክንድር ነጋን እያሰረ ያሰቃየው እንደነበረ ሁሉ፣ ኦነግም እስክንድር ነጋን እያሰረ አሰቃይቶታል። ጭራቅ አሕመድ በእስክንድር ነጋ ላይ ግልጽ ጦርነት አውጆ እንደነበር ሁሉ፣ በፋኖ ስም የወጣው የመረጃ ቲቪ መግለጫም በእስክንድር ነጋ ላይ ግልጽ ጦርነት አውጇል። በርግጥም እስክንድር ነጋ ወያኔን፣ ኦነግን፣ ምዕራባውያንን እና የመረጃ ቲቪ ቡድንን አራቱንም በጋራ እንዲቆሙ ያደረጋቸው የጋራ ጠላታቸው ሁኗል። ይህ ደግሞ በፋኖ ስም መግለጫ ያወጣውን የመረጃ ቲቪን ቡድን ማንነትና ምንነት ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፣ አጋሩን አይቶ ምግባሩን እንዲሉ።