>

በፎቶ ቦለቲካ አንታለልም!

በፎቶ ቦለቲካ አንታለልም!

በመዝገቡ ዱባለ

ዛሬ የብአዴን አልጋ ወራሽ መንጋ ‘ዶ/ር እንዳለማውን እና ጋዜጠኛ ወግደረስን’ በታሰሩበት ሲስቁ የሚታይበትን ፎቶ እያዘዋወረ ይገኛል።

ታሳሪ ከአሳሪው ጋር ሲስቅ ታየ ማለት፣ የታሳሪው እስር ልክ ነው ወይም ታሳሪው በተመቻቸ ቦታ ላይ ነው ያለው ማለት አይደለም።

ዘመነ ካሴ የዛሬ አመት እስር ላይ እያለ ሊጠይቁት ከመጡት  ጋር፣ ከታሳሪዎች ጋር እንዲሁ ከወይህኒ ቤቱ ዋርዲያዎች ጋር ሲስቅ ይታይ ነበር። ያ ማለት ግን እስሩ ትክክል ነበር ወይም እስሩ ተመችቶት ነበር ማለት አይደለም።

አሁን በአዋሽ አርባ፣ በቂሊንጦ፣ በቃሊቲ እና በሌሎች ማጎሪያዎች በእስር ላይ የሚገኙ አማራዎች ድንገት ብንሄድ እየሳቁ ልናገኝ እንችላለን። ያ’ግን በአማራነታቸው እና በጠያቂነታቸው ምክንያት የሚደርስባቸውን መከራ አይሸፍንብንም።

ዛሬም እነ ወግደረስ የተቀመጡበት ወንበር የታሰሩበትን ቦታ፣ ጥርሳቸው ላይ የታየው ሳቅ የደረሰባቸውን ስቃይ፣ የተንውሱት በደል ያጡትን ነፃነት አይሸፍንብንም። አንታለልም።እነወግደረስን ሊያስር የሚችለው አንድም ብልፅግና፣ አንድም ብአዴን፣ አንድም የብአዴን አልጋ ወራሽ ብቻ ነው። ዛሬውኑ ፍቷቸው።

Filed in: Amharic