>
5:42 pm - Friday March 21, 0977

መስቀለኛው  መንገድ ላይ

መስቀለኛው  መንገድ ላይ

 

ከኦሜጋ ጸሎት

 

የፓን አፍሪካ መሥራቿ እና የአፍሪቃ ሕብረት መቀመጫዋ ሀገር ሥጋዋ ረግፎ አጽሟ ከቀረ መቆየቱን የምናሰተውለው ጉዳይ ነው።  መንግሥት በኩል በፖለቲካ አቅም ማነስ እና በነገረ መለኮት ቅርቃር ውስጥ የወደቀች ሀገር ሆናለች፡፡

የአክሊሉ ሀብተወልድ ሀገር፣ የጎሹ ወልዴ ሀገር፣… ብቃት ሳይኾን የነገድ ኮታን መሠረት አድርጋ “ዲፕሎማት” የምትመለምል ኢትዮጵያ የዛሬ 4 አመት ታላቁ ግድቧ “Blow up” እንዲኾን በአደባባይ አብሪ ጥይት ለተኮሰ  መሪ  ዶናልድ ትራምፕ የሰጠችው ምላሸ የወርደ  እንደነበረ  ። እድልና በአጋጣሚው ግን ግድቡ እደተባለው አልፈነዳም።ምክንያቱ ደግሞ የዶናልድ ትራምፕ በዳግም ምርጫ መሽነፉ ነው። 

እናቶች መቀነታቸውን ፈተው ከእጅ ወደ አፍ ከሆነ ኑሮ ላይ ከልጆች ጉሮሮ ነጥቀው እያዋጡ የተሰራው የህዳሴ ግድብን ቤቱን ‘Arrogance and Ignorant’  ዶናልድ ትራምፕ ግብጽ በሚሳኤል እንድታጋየው ጥቆማ የሰጠው መንግስት ተመልሶ ስልጣን ይዟል። ኢትዮጵያም ችግር ላይ ወድቃለች።ከአራት አመት በፊት ኢትዮጵያን በጥቂቱ ያውቅ ነበር።ይኽውም ለአልሲሲ ፍቅር ሲል ነበር አሁን ከ4 አመት ብኋላ ግን የበለጠ  ያውቃል።ከግል ባህሪ በመነሳት ንዴትም ፥በቀልም አለበት። የትራምፕ ፖለቲካ transactional ነው። የዛሬ 4 አመት ግብጽ ያልተሳካለትን በጉልበት ኢትዮጵያን አስፈገድዶ  የህግ binding Agreement እንድትገባ የማድረግ አቅሙ 97% ነው።

  • እንደ አብይ አይነት ለኢትዮጵያ ጥላቻ ያለው መሪ
  • እንደ አብይ ላለ ለአሜሪካ እዘምታለሁ ለሚል መሪ
  • እንደ አብይ ላለ የስልጣን ጥመኛ
  • እንደ አብይ ላለ የፖለቲካ ብስለት ለሌለው
  • እንደ አብይ ላለ ሁሉን አውቃለሁ የሚል (self consumed) መሪ ሊወጣው የሚችል ችግር አይደለም የመጣው።

ዶናልድ ትራምፕ ለአፍሪካ መሪዎች ያለውን ንቀት አሳይቷል። ዋይት ሀውስ  በገባ ወር ባልሞላ ግዜ ውስጥ ሙልጭ አርጎ ተሳድቧል። የተናገረው እውነትነት ቢኖረውም  ቅሉ  በዲፕሎማሲው ቋንቋ ለአፍሪካ ደንታ እንደሌለው ኣሳይቷል። አፍሪካዎች (Shithole country) ናቸው ለዶናልድ ትራምፕ።

 በቅርቡ ጂቡቲ ኢትዮጵያን በድሮውን ደበድበች የሚል ዜና ተሰራጭሯቷል።ድብደባውን ግን የፈጸመችው አሜሪካ መሆኗን ዶናልድ ትራፕ በ3 ኛ ቀን በቴሌቭዥን ብቅ ብሎ አፍርካ ቀንድ አንድ አሸባሪ በድሮውን ገለናል አለ።ሆን ተብሎ የተደረገ የማሸማቀቂያ መንገድ ነው። አብይ አህመድ እውነትን ከመቀበል ድብብቆሽ መጫወት ነው የመረጠው። ዜናው በጅቡቲ እንዲመሀኝ ነው የተፈለገው። ምክንያቱ ደግሞ:- 

ከዶናልድ ትራፕ አስተዳደር ጋር ጥሩ ግንኙነት ያለው ለማስመስል ነው

ዶናልድ ትራሞፕ የታሪክም፣ የዲፕሎማሲም ጾመኛ መኾኑን በአደባባይ ሲያሰጣ የቆየ መሪ ነው::

ኢትዮጵያ አሁን አጋር የላትም።አፍሪካ አገሮች እንኳ ከጎኗ የሚቆሙ አይሆንም።ለዚህ ምክንያት ደግሞ የተሳሳተ የአብይ የውጭ ግንኙነት ፓሊሲ ነው።ከዓባይ ተፋሰስ ሀገራት መካከል የላይኞቹን 11 ሀገራት በላቀ ዲፕሎማሲያዊ ጥበብ ወደ ኢንቴቤ ሰምምነት ማምጣት የቻለች ሀገር፣ በNile Basin Initiative ማዕቀፍ የወንዙን አጠቃቀም ወደ ጉልህ ምዕራፍ ያደረሰች ሀገር፣ ከባድመ በኋላ የዜጎቿን ሥነልቦና ወደ አንድ ዘመቻ ለማምጣት አጋጣሚውን የፈጠረች ሀገር፣ በአንድ ጥጋበኛ  በአጋጣሚ እና በእድል መሪ የሆነ ሰው ላይ ያበሳጫል፤ ያስቆዝማል።

ኢትዮጵያ በማይመጥናት ጨቅላዎች እጅ መውደቋንም ፍንትው አድርጎ ያሳያል። ለሥልጣን ሲባል በሴራ ፍተላ ሀገር በመጋዝ በሚገዘገዝባት ሀገር ይኽ መኾኑ ተጠባቂ ቢኾንም ማናደዱ አይቀርም።

ዶናልድ ትራፕ ለአብይ ትእዛዝ እንዲሰጥ ዋይት ሀውስ ከገባ ወዲህ የግብጽ ደህንት ሚስትር ሁለት ጊዜ የወጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ  ሁለት ጊዜ ከዶናልድ ትራምፕ እና አስተዳደሩ ጋር ተገናኝተዋል።

ከአልሲሲ ጋርም ሁለት ጊዜ በስልክ ተገናኝተዋል። ከተነሱት አጀንዳዎች መካከል የህዳሴ ግድብ መሆኑን ግብጾች በኩራት እየተናገሩ ነው።

የሚቀጥለው ወር ደግሞ IMF እና WORLD ባንክ የኢትዮጵያን የብድር አከፋፈል ስርአት ፓሪስ ላይ የሚገመግሙበት ነው። ዶንልድ ትራም “ኢትዮጵያ ካልፈረመች ገንዘቡ እንዳይሰጥ ያዛሉ ተብሎ ይጠበቃል!”

 “አገር መሽጥ የለመደው አብይም ከመስማማት እንደማይመልስ ነው!

 

Filed in: Amharic