>
5:42 pm - Wednesday March 21, 5477

የድሮው ጴ*ን*ጤ እና የአሁኑ የብልጽግና ጴ*ን*ጤ

የድሮው ጴ*ን*ጤ እና የአሁኑ የብልጽግና ጴ*ን*ጤ

(ቀሲስ ኤፍሬም እሸቴ)

 

፩. መነሻ፦

የዛሬ ስንት ዓመት ደብረ ብርሃን ላይ የሆነ የጴ*ን*ጤ ድርጅት ሕክምና በነጻ ልስጣችሁ ብሎ ሕዝቡን ጠራ። ሕክምና ፍለጋ የሄደውን ሕዝብ በጾም በሬ አርደው ካልበላህ አናክምህም አሉት። ሕዝቡ ለሕክምና ተጠርቶ መከልከሉ ሳያንስ በግድ ጾሙን እንዲሽር በንቀት መጠየቁ አበሳጭቶት የዘረጉትን ድንኳን አፈረሰው ተባለ። በዚህ የተነሣ የተበሳጨ አሁን ታዋቂ ታዋቂ የሚጫወት ገጣሚ ጴንጤ ልጅ “እናንተ ያልሰለጠናችሁ፣ ወንጌል የማይገባችሁ አሕዛብ ደንቆሮዎች” ብሎ በጽሑፌ ሥር ኮሜንት አደረገ።

ይህ ልጅ ገና ግጥም ለመለማመድ ዳዴ ሲል ጀምሮ አውቀዋለሁ። ታዋቂ እንዲሆን ብዙ ኦርቶዶክሶች ልጆች ሲደግፉት እንደነበር አውቃለሁ። ከኔም ጋራ በውስጥ ብዙ እናወራ ነበር። ጴ* ን* ጤ ይሁን አይሁን ትዝ ብሎኝም አያውቅም ነበር። ያቺ የእምነት ጉዳይ ስትመጣ ግን የማላውቀው ሰው ከውስጡ ከነቀንዱ ብቅ ሲል ገረመኝ።

የብልጽግና መንግሥት ባዘጋጀው የስብከት በዓል ላይ ተመርኩዞ በተነሣው ተቃውሞ ብዙ “ታዋቂ” ጴ*ን*ጤ*ዎች ከነቀንዳቸው ብቅ ሲሉ ያንን ገጣሚ ልጅ አስታወሱኝ። እምነታቸውን ለማስፋፋት ከሆነ ሀገርም፣ ባህልም፣ መከባበርም፣ አብሮ መኖርም ገደል ቢገባ ግድ አይሰጣቸውም። ግን ለምን? ለምሳሌ …

ጴጥሮስ መስፍን የኢሳት አሁን ደግሞ የEMS ጋዜጠኛ ነው። ሁሉንም ያከብራል ብለን እንጠብቀው ነበር። አነቃቂ ንግግር የሚናገረው ዮናስ ከበደ የመንግሥት ባለሥልጣንም ነበር። ፈላስፋ ነው ሲባል ሰምቻለሁ። ሚዛናዊ ይሆናል ብለን እንጠብቀው ነበር። ሁለቱም ዛሬ በክርስቲያኑ ላይ ሲሳለቁ ተመልክተናል።

፪. Empowering ጴ*ን*ጤ*ዎች

ጴንጤዎችን empower የማድረግ ዘመቻ ከ10 ዓመታት በላይ የዘለቀ ጉዳይ ነው። እናውቀዋለን። ኋላ አድጎ የመንግሥትን ሥልጣን ሙሉ በሙሉ ወረሰ። ልክ እንደ እንቦጭ አረም ተስፋፋ። በደቡብ ብቻ ሳይሆን በኦሮሚያና በሌሎችም ክልሎች ጴ*ን*ጤ*ነት የሁሉም ነገር መስፈርት ነው። ልክ በውጪው ዓለም እንዳሉ secret ሶሳይቲዎች ኢትዮጵያን በጥርሱ ውስጥ ማስገባት እና መንግሥት መሆን ችሏል።

ይህ empowered የሆነ የጴ*ን*ጤ ሰብሰብ በተቃዋሚነት ደረጃ ባሉ ፓርቲዎች፣ ሚዲያዎች፣ ማኅበራት ውስጥ በደንብ ተስፋፍቷል። ራሱን መደበቅና ማስመሰል እያቃተው ከነቀንዱ ብቅ የሚለው በዚህ ዓይነቱ አጋጣሚ ወቅት ነው።

ጴ*ን*ጤ*ዎች empower በሚደረጉበት ዘመን ከሥራና የትምህርት ዕድል ጀምሮ በሥልጣን እርከን ላይ እንዲፈነጩ ተደርገዋል። ይህንን ዕድል የሚፈልጉ ካሉም እምነታቸውን መቀየርና የዚህ secret society የሚመስል ድርጅት አባል ለመሆን ነፍሳቸውን እንዲሽጡ ይጠየቃሉ። በቤተ ክርስቲያን የምናውቃቸው ብዙ ወንድም እህቶች ነፍሳቸውን ገብረው ይህንኑ ቡድን ተቀላቅለዋል። በሥልጣን ላይ ያሉ አያሌ የትናንት ኦርቶዶክሶች ማተባቸውን የበጠሱ empowered ጴ*ን*ጤ*ዎች መሆናቸውን እናውቃለን።

፫. የብልጽግና ጴ*ን*ጤ*ነት ሁሉንም ጴ*ን*ጤ ይወክላል?

 

ብዙ ጴ*ን*ጤ ወዳጆች፣ ቤተሰቦች አሉን። በዚህ በአዲሱ secret society መሰል ጴ*ን*ጤ*ነት ውስጥ የሌሉ ብዙ በጎ ሕሊና ያላቸው ጴ*ን*ጤ*ዎች እናውቃለን። ስለዚህ የብልጽግና ጴ*ን*ጤ*ነት ሁሉንም ጴ*ን*ጤ ይወክላል ብለን አናምንም። ነገር ግን የብልጽግናን ጴ*ን*ጤ*ነትን መቃወም ሁሉንም ጴ*ን*ጤ መቃወም እየመሰላቸው ስለሚከፉ እነርሱን ላለማስቀየም ብዙ ጥረት ተደርጓል። ነገር ግን የሚቻል አልሆነም። ነገሩ መስመር አለፈ።

** የብልጽግና ጴ*ን*ጤ*ነት ባህል የለውም። የሰው ባህልም አያከብርም። ደፋርና ባለጌ ነው:: አንተ በምታከብረው እና የተቀደሰ ነው ብለህ በምታምነው ነገር ሲያላግጥ ለከት የለውም።

** ለምሳሌ በጥምቀት ሰሞን በታቦታተ ሕጉ ሲቀልዱ ነበር። በሕግ መጠየቅ አለመጠየቅ ሌላ ነገር ነው። መከባበር ሕግ ስላለ ብቻ የሚፈጠር ነገር አልነበረም። ግን የብልጽግና ጴ*ን*ጤ ደንታ የለውም።

** የቤተ ክርስቲያን ንዋየ ቅድስት (ከበሮ ፣ መቋሚያ፣ ጸናጽል ወዘተ) ልክ እንደ ስማቸው “የተቀደሱ ዕቃዎች” ናቸው። ነገር ግን በየመድረኩና በየአዳራሹ ሲቀልዱበት ቅር አይላቸውም። ምክንያቱም የብልጽግና ጴ*ን*ጤ ስለ ተቀደሱ ነገሮች ደንታው አይደለም።

** የብልጽግና ጴ*ን*ጤ በጴ*ን*ጤ*ነት ውስጥ የተደበቀ ሌላ ጴ*ን*ጤ፣ በኑ*ፋ*ቄ ውስጥ የተደበቀ ሌላ ኑ*ፋ*ቄ ነው። ድንጋይ ካብ ውስጥ እንደተደበቀ እባብ ሌላውን የፕሮቴስታንት ማኅበረሰብ ምሽግ አድርጎ ይነድፍሃል። ነደፈኝ ብለህ ስትናገር ሌላው ፕሬቴስታንት ይቀየማል ። መካከላቸው ያለውን እባብ ከመመልከት በመርዙ የተጎዳኸው ሰው ላይ ይነሱብሃል።

 

፬. ለብልጽግና ጴንጤ ጥፋት “የራስህን ወገን ተጠያቂ ማድረግ ብቻ” ያዋጣል?

 

በሰሞኑ የብልጽግና ጴንጤ መንግሥታዊ እብደት ብዙ ኦርቶዶክሳዊ ወገን “ይህንን ሁሉ ያመጣብን ቤተ ክህነት ነው፣ የራሳችን አባቶች ናቸው” በሚል ቁጣውን ወደራሱ አባቶችና ወደ ራሱ ተቋማት ሲያዞር ተመልክተናል። ለዚህ ሁሉ ውድቀታችን አጭር መልስ ለማግኘት መጣራችን ራሳችንን satisfy ያደርገን ካልሆነ በስተቀር መልሱ በአጭሩ አባቶችን በመውቀስ እና በመጥላት ብቻ እንደማይገኝ ደፍረን መናገር ይኖርብናል። ጳጳሳትን በመሳደብ፣ በመናቅና ጣት በመጠቆም የብልጽግና ጴ*ን*ጤ*ን ማስቆም ቢቻል እንዴት ደስ ባለን። ግን አይደለም።

ነገሩን ሰፋ አድርገን ለማየት ለምን አንፈልግም? ከቤተ መቅደሱ ጀምሮ አገልግሎታችንን እያረከስን ከእግዚአብሔር መራቃችን ለእግዚአብሔር የለሾች አሳልፎ እንደሰጠን ለምን እንዘነጋለን? አዎ “አክሊል ከራሳችን ወድቋል” (ሰቆቃወ ኤርምያስ 5፥16)። ምናምንቴዎች፤ እግዚአብሔርንም የማያውቁ ሰዎች ሰልጥነውብናል (መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 2፥12)። ለዚህ መፍትሔው ግን የራሳችንን ችግር፣ ተቻችለን፣ በራሳችን ለመፍታት መጨከን ነው። “ችግሩ የሌላ፣ መፍትሔው የእኛ” የሚል የግብዝነት መንገድ የትም አላደረሰንም።

አሁንም ቢሆን ሁሉም የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ከልሒቅ እስከ ደቂቅ ከመናናቅና ከመገፋፋት መንገድ ተመልሶ (ቢያንስ በዚህ ጊዜ እንኳን) ለራሱ ሲል ቁጭ ብሎ መፍትሔ ቢፈልግ ይሻለዋል። ሌላው መንገድ እንደማያዋጣ ተፈትኖ ታይቷል።

በዚህ ረገድ፣ ምዕመናንም ራሳቸውን ቢፈትሹ ጥሩ ነው። የእነርሱ ምንም ኃጢአት የሌለ ይመስል ሌላው ላይ ብቻ ጣት በመጠቆም ቤተ ክርስቲያን ላይ የመጣው መዓት አይመለስም።

፭. የብልጽግና ጴ*ን*ጤ*ነት ለእኩልነት ቦታ የለውም

የብልጽግና ጴ*ን*ጤ*ነት ለእኩልነት፣ ለመቻቻል፣ አብሮ በሰላም ስለመኖር ቦታ የለውም፤ ቁርጥህን እወቅ። አሁን ታንኩም፣ ባንኩም በእጁ ነው። ሀገሪቱ ከመቼውም ጊዜ በላይ በጎሳ፣ በቋንቋ እና በእምነት የተከፋፈለችበት ዘመን ስለሆነ “ተባብሮ ሊቃወመኝ የሚችል ኃይል የለም” ብሎ ገምቷል። ራሳቸው ኦርቶዶክስ የሆኑ ብዙ ወገኖቻችን የዚህ መንግሥታዊ እምነት ደጋፊዎች ናቸው። ይህንን ቡድን መቃወም የእነርሱን ብሔረሰብ መቃወም አድርገው ይመለከታሉ። ስለዚህ “ይህንን ቡድን ከመቃወም ቢያንስ ዝምታን መምረጥ ይበጃል” ብለው ያስባሉ።

Filed in: Amharic