መሣይና መሣዮቹ – ክፍል ሁለት
መሣይና መሣዮቹ ፤ እስክንድርን ሲፈልጉ ወዳጅ መስለው ይቀርቡታል። ሲፈልጉ ደግሞ ይገዘግዙታል። ቢቻላቸው ግን ከኦነግም – ከሕወሓትም በላይ ለእርድ የሚያቀርቡት እነዚህ ተኩላዎች ናቸው።
እንደፈለጉ ነው። ውሸት ይፈበርካሉ። ይቀደዳሉ። መልሰው ይቅርታ ሳይጠይቁ ያጃጅላሉ። ልክ ግንቦት ሰባት ውስጥ ሆነው ድርጅታቸው ጋር አብረው እየሰሩ እንዳልሰሩ የሚደሰኩሩት ዓይነት ነው። በይፋ ”ግንቦት ሰባትን ለቅቄያለሁ” ያለችው እስከማውቀው ድረስ ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ ብቻ ነበረች። ልክ ”የግንቦት ሰባት አባል ሆኛለሁ” እንዳለችው ሁሉ። ሌሎቻቸው ግን ለቀናልም፣ ወጥተናልም ሳይሉ ያሳክራሉ፣ ይቀላምዳሉ። መንጋውን ያሳክሩታል። አብይ ፆም ሆኖብኝ ነው እንጂ ”ያቅለሽልሻሉ” ልል ነበር። ለ አብነት ሁለቱን ምሥሎች ብቻ ተመልከቱ። በውሸታቸውም በድርጊታቸውም ይናበባሉ። የተለያየው የዩቱብ ቻናሎቻቸው ብቻ ነው።
በነገራችን ላይ መሣይ መኮንን ከአንከር ሚዲያው በተጨማሪ ”ኢትዮ ፋክት” በሚለው ”ዩቱብ ቻናሉ” ”ፋክት” ብሎ ውሸት በሚያሰራጭበት ”ዩቱብ” ላይ የለቀቀው ዜና ነበር። አሁን ብትሄዱ ይህን አታገኙትም። አጥፍቶታል። አድማጭን፣ ተመልካችን ብቻ ሳይሆን፤ የሰው ሕይወትም ላይ የሚጫወቱት በዚህ መልኩ ነው። ታዲያ እርሱ ብቻ አይደለም።የትግል አጋሮቹም ናቸው። እነ ደረጀ ወዘተ…. ። ለ አብነት ያስቀመጥኩትን የውሸት ስርጭቶቻቸውን ተመልከቱ። ግርማ ካሣ የተባለ ቀድሞ ለሕወሓት አሁን ደግሞ ለኦሕዴድ/ኦነግ የሚሰራው ሰውዬም በጽሑፍ ያግዛቸዋል። እነርሱ ደግሞ በድምጽ ያቅራራሉ።
መሣይና መሣዮቹ የተከሰቱት ተለውጠው አይደለም። አቀራረባቸውና ትወናቸው ተለወጠ እንጂ፣ ያው የበፊቱ ናቸው።አሁን የተለየ የሚያደርጋቸው ለየብቻ ”ዩቱብ ቻናል” መክፈታቸው ነው። ኢሣት ተበታትኖ ወይም ተለያይቶ ማለት ናቸው። በፊት በአንድ ቻናል በብዙ አፍ (ምላሥ) ይቀርቡና (ያቀርቡልን) ነበር። የሚያገኙትን ገንዘብ በዚያው ልክ በጋራ ነበር የሚቀራመቱት። አሁን ግን ገቢያቸው ለየራሳቸው ነው። መሣይና – መሣዮች በአገዛዙም በዩቱብ አለቆችም እገዛ ይደረግላቸዋል። አይዘጉም። አይወርዱም። አይታገዱም። ምክንያቱን መጨረሻ ላይ ለመግለጽ እሞክራለሁ። ”ጌታዋን የተማመነች በግ ላቷን የፈለገችበት ቦታ ነው የምታደርገው”። ዓላማቸው፣ ትግበራቸው እና የመዳረሻ ግባቸው አንድ ዓይነት ነው። ልክ የቀድሞው ኢሕአዴግ ስሙን ለውጦ ብልጽግና እንደሆነው ማለት ነው።
ያን ጊዜ”አዳነች አቤቤ ዳግማዊት ጣይቱ ነች” ያለው ፋሲል የኔዓለም ብቻ አይደለም። ደረጀ ሃብተወልድም፣ መሣይ መኮንንም፣ ሲሳይ አጌናም አበበ ገላውም ናቸው።የገለጹበት መንገድ አባባላቸው ይለያይ እንጂ። ያን ጊዜ ”…አብይ እኮ አይደለም አላሰራም ያሉት በዙሪያው የተሰባሰቡት ናቸው” ያሉት ነዓምን ዘለቀ፣ ኤፍሬም ማዴቦ ብቻ አይደሉም። ከላይ በስም የጠቀስኳቸውም ናቸው። ያን ጊዜ አንዳርጋቸው ጽጌ ”ለአብይ አህመድ ROAD MAP የሰጠሁት እኔ ነኝ” ሲል የተቀባበሉትና ያራገቡት እነዚሁ ነበሩ። በእርግጥ አብይ አህመድም የኢትዮጵያ ሕዝብ ”ሾርት ሚሞሪያም” ነው ባለው መሰረት ነው ጉዞአችንን ያደረግነው። ስለዚህም ትላንት ሲያላግጡብን፣ ሲያደሙን እና ሲወሻክቱ የነበሩ ሰዎች ዛሬም ቢወሽክቱ አይገርምም። አይደንቅምም። ምክንያቱም ”ሾርት ሚሞሪያሞች” ነንና።
ግን የዛኑ ያህል በዓይነ – ቁራኛ የምንከታተላቸው፣ የሚያደርጉትን የምንመለከታቸው ብዙዎች መሆናችንን አያስተውሉም። በመንጋቸው ተከልለው መርዛቸውን መትፋት ብቻ ሳይሆን የአብይን ኢትዮጵያን የማዳከምና የመከፋፈል፤ የማባላትና የማጨራረስ ስልታቸውን ከግንቦት ሰባት እስከ ኢዜማ፣ ከ ኢዜማ እስከ ብልጽግና ፤ እንዲሁም በተቃዋሚ ስም አሁንም ሚናቸውን በፈጣንና ፣ በፈጣጣ እየተወጡ ነው።
ቀድሞ በገነቡት ስም ብዙ ተከታይ አላቸውና፣ የሚነዳላቸው መንጋ አለና ። ይህን ለመለወጥ ብዙ ትግል ማስፈለጉ የግድ ነው። እየጻፍኩ ያለሁት እነሱን ለመለወጥ አይደለም። መልካሙን ምዕመን ለማንቃትና አስተውሎት ለመቸር እንጂ ።
አንድ ለእናቱ እስክንድርን በአዲስ አበባ ጉዳይና በተረኝነት ጉዳይ ከጅምሩ በግልም፣ በቡድንም በድርጅትም ሆኖ እላይ – እታች ሲል ” ዕብድ ነው፣ የሚሰራውን አያውቅም፣ ትኩረት ፍለጋ ነው” ወዘተ… እያሉ ሲያላዝኑ የነበሩት እነዚሁ ሰዎች ነበሩ። መሣይና መሣዮቹ።
ከመሣይ አንከር ሚዲያ በሮኬት ፍጥነት ጣና ቲቪ ላይ በቅርቡ የተከሰተው፤ በገዱና በአንዳርጋቸው ጽጌ ወይም (በዲያስፖራው አማራ ዓለም አቀፍ ትብብር) የሕዝብ ግንኙነትን ስልጣን የተሰጠው መስፍን አማን የዚሁ ተቀጥያ ነው።
በኢንሣ እና በሲ አይ ኤ የተመለመሉና የተመደቡ ብዙ ዩቱበሮች፤ የቴሌግራም ጣቢያዎች፤ የሶሻል ሚዲያ አርበኞች የ አማራውን የሕልውና ትግል ለማኮላሸትና ዓላማውን በማሳት የብአዴን ተንበርካኪ ለማድረግ የወረሩት ከኤድስም ፤ ከክፉኝም በከፋና በባሰ ሁኔታ መሆኑን ልብ ማለት ያስፈልጋል። ስለሆነም እነዚህን መሰል ‘ወዳጅ’ መስለው የተቀላቀሉ ግለሰቦችን አጥርቶ መታገል የግድ አስፈላጊና አጠያያቂም መሆን አይገባውም።
መስፍን አማን የተመለመለው በቀድሞው የነፃ ፕሬስ ጋዜጠኛና ብዙዎች በማያውቁት የኢትዮጵያ መረጃና ደህንነት ባለስልጣን (ኢንሣ) ውስጥ በሚሰራውና እየሰራ በሚገኝው፤ ክንፉ አሰፋ በኩል ነው። ክንፉ አሰፋ በኔዘርላንድ አምስተርዳም ነዋሪ የነበረ አሁን ግን በአብይ አህመድ ጋባዥነት ወደ ሃገር ቤት ጠቅልሎ የገባ ነው። ሸራተን ሆቴል ብትገቡ ባለሃብቱ አላሙዲን የሚቀመጡበት መቀመጫ ላይ እሱ ነው ተቀምጦበት የምታገኙት።
እንዲያውም በለውጡ ጊዜ አብይ ዲያስፖራዎችን ሰብስቦ ያስጨበጨባቸው ጊዜ መስፍን አማንም እጁ እስኪላጥ እንዲያጨበጭብ ያስደረገው ይሄው ክንፉ አሰፋ ነው።
መስፍን አማን በዚሁ ጭብጨባውና ውዳሴው ጥሩ ማርክ ተሰጥቶት ነው የተመለሰው። ባለፈው ቁጥር አንድ መሣይና – መሣዮቹ መጣጥፌ ለኮፍኮፍ አድርጌ ነገር ግን ጫን አድርጌ ያልጻፍኩት ጽሑፍም ነበረኝ። እንዲያውም ይሄው መስፍን አማን ”አማራ ዓለም አቀፍ ትብብር ” የህዝብ ግንኙነት ስልጣን ከመውሰዱ በፊት በአውሮፓ የእነ እስክንድር ነጋ ተጠሪም ለመሆን ሞክሮ ነበር። ”ሟች የገዳይን ሐሳብ ቢያውቅ ኖሮ አይሞትም ነበር” አሉ። ብቻ ብዙ ነው። ይሄንና የመሳሰለውን ”መሣይና መሣዮችን” ይዤ በሚቀጥለው እከሰታለሁ። እያዘገምን ።
ግርማ እንድሪያስ ሙላት
girma077@gmail.com
ethreference@gmail.com