አትነሳሞይ አትነሳሞይ፤ የትግል መዝሙር
የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ጥያቄ የኔም ጥያቄ ነው!
በድሉ ሙሉ-አለም
አትነሳሞይ አትነሳሞይ፣ ሃኪም ተርቦ አገር አለወይ፣
አትነሳሞይ አትነሳሞይ፣ ሃኪም ሲታሰር መምህር የለምወይ፣
አትነሳሞይ አትነሳሞይ፣ ወገኔ የሚል ጦር የለንሞይ፣
አትነሳሞይ አትነሳሞይ፣ አብሮን የሚቆም ፖሊስ አጣንወይ፣
አትነሳሞይ አትነሳሞይ፣ ርሃብ ሰቆቃው አይበቃህሞይ፣
አትነሳሞይ አትነሳሞይ፣ ተረግጦ መኖር ተስማምቶሃልወይ፣
አትነሳሞይ አትነሳሞይ፣ ስራ አጥነት አይመርህምወይ፣
አትነሳሞይ አትነሳሞይ፣ ኑሮ ዉድነት አልነካህሞይ፣
አትነሳሞይ አትነሳሞይ፣ ተዋርዶ መኖር ግብርህ ሆኗል ወይ፣
አትነሳሞይ አትነሳሞይ፣ ፍትህ ማጣቱን ወደኸዋልወይ፣
አትነሳሞይ አትነሳሞይ፣ የአንድነት ትርጉም አይገባህሞይ፣
አትነሳሞይ አትነሳሞይ፣ ፍትህ ነጻነት አይጠማህሞይ፣
አትነሳሞይ አትነሳሞይ፣ ወንድም ሲታሳር ትተኛለሆይ፣
አትነሳሞይ አትነሳሞይ፣ የእህትህ በደል ያንተ አይደለምወይ፣
አትነሳሞይ አትነሳሞይ፣ አገር ስትጠፋ ታዛቢ ሆንክ ወይ፣
አትነሳሞይ አትነሳሞይ፣ ነግ-በኔ ማለት ጭራሽ ቀረወይ፣
አትነሳሞይ አትነሳሞይ፣ የአባት አደራ አይወቅስህሞይ፣
አትነሳሞይ አትነሳሞይ፣ የናትህ አገር በአንተ ትጥፋወይ፣
አትነሳሞይ አትነሳሞይ፣ መፈናቀሉ ይገባሃልዎይ፣
አትነሳሞይ አትነሳሞይ፣ ዘራፊ መንግስት ይገባናልወይ፣
አትነሳሞይ አትነሳሞይ፣ ከፈፍሎ ገዢ አይበቃንምወይ፣
አትነሳሞይ አትነሳሞይ፣ አገር ስትሸጥ ደላላ ሆንክወይ፣
አትነሳሞይ አትነሳሞይ፣ እንደሰው መኖር አትመኝምወይ፣
አትነሳሞይ አትነሳሞይ፣ የሚፈሰው ደም ላንተ አይደለሞይ፣
አትነሳሞይ አትነሳሞይ፣ የግፍ አገዛዝ አይበቃህምወይ፣