የታላቁ እስክንድር ነጋ የትግል ጉዞ እና የጠላት ሴራ
ሰናይት አያሌው
ስለታላቁ በእኔ አቅም መግለፅ ባይቻለኝም ነገር ግን ታሪክ በደንብ ይሰንደዋል!
ታላቁ ሁሉም ከሚመኛት ከሃገር አሜሪካ ወደ እናት ሀገሩ በመግባት ጊዜ ሳያጠፋ ወደ ሸዋ ጫካ ገባ። አርበኛው ሸዋ ጫካ በመግባት ከአርበኛ መከታው ማሞ ጋር በመሆን ፋኖን ማደራጀትና ማሰባሰብ ጀመረ ፣ሸዋ ላይ ፋኖን መሰረት አስያዘ፣አርበኛ እስክንድር ነጋ ሸዋ ላይ አላቆመም፣ጎጃም በመግባት በቡሬ ወለጋ መስመር እስከ ደብረኤልያስ ቀጠና በመግባት ፋኖን አደራጀ፣ በነገራችን ላይ አርበኛው ከአሜሪካ ወደ ሀገር ቤት በመግባት የጫካን ህይወት ሲቀላቀል ከአዲስ አበባ የጋዜጠኚነት ሙያቸውን በመተው ጫካ የገቡት አርበኛና ጋዜጠኛ ጌጥዬ ያለው፣አርበኛና ጋዜጠኛ ወግደረስ ጤናው እና ከባህርዳር ከተማ በመውጣት ደግሞ ጌራወርቅ ወርቁ ናቸው።
አርበኛ እስክንድር ለጠላት ቁልፍ ቦታወች ናቸው ብሎ ያሰባቸውን ሸዋና ጎጃም ላይ መሰረቱን አስቀመጠ!
አርበኛው መሰረቱን ጎጃምና ሸዋ ላይ ብቻ ሳይሆን በሃገር አሜሪካም አስቀምጧል፣የአሜሪካ ፋኖወች በተለይም የትግሉ የጀርባ አጥንት የሆነውን ፋይናስ በማሰባሰብ የከተማ ቻርታሮችን በመዘርጋት ከፍተኛ ስራ እንዲሰራ አድርጓል።
የአሜሪካ ፋኖዎች ገንዘባቸውን፣ጊዜያቸውንና ሀሳባቸውን ለትግሉ በማአዋል አፋድ የተሰኘውን የአማራ ድርጅት እንዲመሰረት ተገዳዳሪ የሌለው አስተዋፆኦ አበርክተዋል።
አርበኛ እስክንድር ነጋ በቡሬ ወለጋ እየተቀሳቀሰ ባለበት ወቅት አስደጋጭ ክስተት ተፈጠረ፣ታላቁ ቡሬ ከተማ ላይ በብአዴን ሰዎች ተይዞ በጎጃም መስመር ወደ አዲስ አበባ ተወስዶ ለፊድራል ተላልፎ ሊሰጥነው የሚል የሁላችንንም ጆሮ ጭው የሚያደርግ ዜና ሰማን፣በጣም ተደናገጥን መረጃውን ያደረሰኚ አብረውት ከነበሩት መካከል ጋዜጠኛ ወግደረስ ጤናው ነበር፣ከታላቁ ጋር አብረውት የነበሩት ሁለት ልጆች ሽባባው እና ደግሰው የተባሉ ሲያዙ ጋዜጠኛ ወግደረስ በአጋጣሚ ነጠል ያለ ቦታ ስለነበር ከብአዴን ሰዎች አምልጦ መረጃውን ለሚድያወች አሳወቀ፣እኔም በቻልኩት ሁሉ ድምፅ ይሆኑታል ላላኳቸው ሚድያወት ለማሳወቅ ሞከርኩ፣ በመጨረሻም አርበኛው ወደ አዲስ አበባ ታጅቦ እየተወሰደ እያለ ደጀን ላይ ወጣቶች መንገድ ዘግተው አስቆሙት፣የብአዴን ሰዎችም በደረሰባቸው ከፍተኛ ተቃውሞ ምክንያት ደጀን ፓሊስጣቢያ ታስሮ እንዲያድር ተደረጉ።
ጠዋት ታላቁና አብረውት የተያዙ ሁለቱ ልጆች ታስረው ካአደሩበት ፓሊስ ጣቢያ በጠዋት ተደወለልኚ ፣ስልኩን ሳነሳ ከደጀን ፓሊስጣቢያነው የሚል ነበር ስልኩን አነሳሁት፣አቤት ማን ልበል አልኩ፣የእስክንድር ነጋ ቤተሰብነሽ አለኚ፣ፈጠን ብዬ አዎ ነኚ፣አዲስ አበባ ተወሰደ እንዴ ስል በድንጋጤ ጠየቅኩት፣ አይ አይደለም ሰው ይፈልግሻል ካለኚ በኃላ ስልኩን ለፈለገኚ ሰው ሰጠው ሃሎ ስል ንግግሬን ጀመርኩ፣ሰኒ ሸባባው ነኚ፣ደህናነን ወደ ባህርዳር የሚመልሱን ይመስለኛል፣ፓሊሶች ሳይቀር ከወጣቱ ጋር በመሆነ በተቃውሞ መንገድ ዘግተዋል አለኚ።
ደና መሆናችንን ላሳውቅሽ ብዬነው፣እንደውልልሻለን አለኝና ስልኩን ዘጋ።
ሽባባው ከታላቁ ጋር ከተያዙ አንደኛው ነበር፣እኔም ሸባባውን በስልክ ካገናኘኚ ፓሊስ ጋር በየደቂቃወች ልዩነት መደወል ተያያዝኩት፣ በመጨረሻም ብአዴን ደጀን ላይ በገጠመው ምድር አንቀጥቅጥ ተቃውሞ ምክንያት ታላቁ እስክንድር ነጋን አብረውት ከነበሩ ልጆች ጋር ወደ ባህርዳር ከተማ መለሰው፣ባህዳር ከተማ ቀበሌ 14 9ኛ ፓሊስ ጣቢያ እየተወሰደ መሆኑን የሰማ የባህዳር ወጣት በኒቂስ ወቶ መሐል አስፓልቶችን በመዝጋት ፓሊስ ጣቢያው ላይ ከበባ በማድረግ ወጣቱ እስክንድር ነጋን ልቀቁ የሚል አስፈሪ ድምፅ ይሰማ ነበር!
በመጨረሻም ይህን የህዝብ ማዕበል የተመለከተው ብአዴን ብዙ ከመከረ በኃላ እስክንድር ነጋ ቤትና ቋሚ ንብረት ያለው ባለው ሰው በዋስ ይፈታ ተባለ።
ይህንን በሰማሁ ጊዜ የግል መኖሪያ ቤት እና ቋሚ ንብረት ያለው አንድ ሰው መፈለግ ነበረብኚ፣ይህን ከባአዴን ሰወች የተላለፈውን ትዕዛዝ ለማስፈፀም ስሞክር አሁን ለደህንነታቸው ስማቸውን ማልጠራቸው ሰዎች ”እኔ እሆናለሁ፣እኔ እሆናለሁ” አሉኚ፣ይሁን እንጀ አርቆ አሳቢው ታላቁ እስክንድር ነጋ አስጠራኚ እና ”ሰኒ ቤትና ቋሚ ንብረት ያለው ነው ዋስ ሊሆን የሚችል የሚለውን ትዕዛዝ በፍፅም አንቀበልም” ካለ በኃላ ”ሰኒ ዛሬ ዋስ ቢሆኑኚ ነገ ወጥመድ ውስጥ ያስገቧቸዋል አለኚ፣ከተል አድርጎም ሰኒ በአንች የመታወቂያ ዋስ ብቻ ሞክሪ ይህንን ነው ማድረግ ያለብን” አለኚ ልበ ሙሉው አርበኛ እስክድር ነጋ እኔም እሽ አልኩት፣በመጨረሻም ታላቁ በእኔ የመታውቂያ ዋስ ተያዢነት አብረውት ከታሰሩት ሸባባውና ደግሰው ጋር ከስር ተለቀቀ።
የባህርዳር ወጣት ታላቁ ታላቁ ያረፈበትን ቤት ከቦ ሲጠብቅ አደረ።
አርበኛው ከአረፈበት ቤት በመውጣት በማግስቱ ጊዜ ሳያጠፋ የትግል ጓዶቹን በስልክም ና በሐካል ጭምር ማግኘት ጀመረ፣ምንም ሳያመነታ ትግሉን አጠናክሮ ቀጠለ፣ወደ ጫካም ተመለሰ።
አርበኛ እስክንድር ነጋ ቦታ የሆነ ሰው ታላልፎ ለፌድራል ተሰጥቶ ለስር ሊዳረግ መሆኑን እያወቀ እና ወደ ነበረበት ወደ ሃገር አሜርካ መመለስ እየቻለ ተመልሶ ወደ ትግል ይገባል ?ወይስ ወደ አሜርካ ይመለሳል ?መልሱን ለእናተ ትቻለሁ።
አርበኛ እስክንድር ነጋ ከዚያ ሁሉ ውጣ ወረድ በኃላ ነው እንግዲህ አርበኛና ጋዜጠኛ ጌጥዬ ያለውን በመያዝ ጦርን አሰማርቶ በደብረ ኤልያስ ጫካ ካልተነካው ግዙፍ የአብይ አህመድ ጦር ጋር የገጠመው ጀግናው፣ፀረ ብአዴንና ፀረ ብልፅግና የሆኑ ጀግና የአማራ የቁርጥ ቀን ልጆችን በማሰለፍ በጠላት ላይ የመጀመሪያውን ጥይት በመተኮስ ተፋልሞል!!
እናም ታላቁ እስክንድር ነጋ ሸዋ ላይ ያስጀመረውን የአማራ ትግል ምስራቅ ጎጃም በደብረ ኤልያስ ጫካ ጨርሶታል፣ማንም ለመድፈር ያልሞከረውን ደፍሮ የሁሉንም የፍራት ኮፈን ገፎ ስራቱን እራቁቱን ያስቀረው።
ከዛ በኃላ ታላቁ እስክንድር ነጋ ፊት ለፊት ከገጠመው የብአዴን ብልፅግና በላይ በፋኖ ስም በተደራጅ ፣ብአዴን ከጠፋ እስትፋሳቸው ሚያቆም ከመሰላቸው የስራቱ ተጋላቢወች ከባድ ፈተና ገጥሞታል!
ከፋተኛ የሆነ የስም ማጥፋት ዘመቻ፣የስብና ገደላ እና ከታጋዩ የአማራ ፋኖ ጋር የመለያየት የሐሰት ስም ማጥፋት ዘመቻው በብአዴን ፋኖዎችና በሚድያ ሰወች ተካሄዶበታል፣ይህ የስም ማጥፋት ዘመቻ የተካሄደበት እዚሁ ራሱ በመሰረተው ድርጅት ሰርገው በገቡ ድንኳን ሰባሪወች ጭምር ነው!!
አሁንም ታላቁ እስክንድር ነጋ ከፋኖ ሰራዊት ጋር እንዳይገናኝ ተደርጎ፣ ”መምራት አይችልም እና ጦሩ ሊያየው አይፈልግም” የሚል ደንበኛ የስብዕና ገደላ እየተደረገበት ይገኛል!
እንደነገርኳችሁ ነው ፣እናተ የስራቱ አስቀጣይ ሰርጎ ገቦች ስሙ፣ተወደደም ተጠላም ፣አርበኛ ታላቁ እስክንድር ነጋ በአማራ ትግል ውስጥ ማንም የማይገዳደረው ደማቅ ታሪኩን የፃፈው ሁሉም የሚመኛትን ሃገር አሜሪካንን ጥሎ ምቾትን፣ ድሎትን ሞትንም ጭምር ንቆ ጫካ ሲገባ ነው አለቀ።
ዝም የምንለው ለአማራ ህዝብ ትግል፣ ከህዝባችን ስንል ነው፣ብዙ የምንናገረው ነበረን!