‹‹ነቀርሳ›› ምን መደረግ አለበት?
ከይኄይስ እውነቱ
አብዛኛው ሰው እንደሚያውቀው ነቀርሳ ዓይነቱ የተለያየምይሁን ገዳይ ደዌ ነው፡፡ ሳይንስና ቴክኖሎጂ እጅግ የዘመነበትጊዜ ላይ ብንገኝም በዓለማዊው ጥበብ የዚህ ደዌ መንስዔበርግጠኝነት አልታወቀም÷ ፈጽሞ ፈውስ የሚሰጥመድኃኒትም እስካሁን አልተገኘለትም፡፡ መድኃኒት ተብሎየሚሰጠውም ገድሎ የሚያነሣ ነው፡፡ የስቃይ ጥግ የሚታይበት፡፡ ‹መድኃኒቶቹ› በነቀርሳ የተመረዘውን ሕዋስ (ሴል›) ለይቶ በማጥቃት ለማጥፋት ሲባል ሕይወት የሆኑትን ነጭ የደምሴሎች፣ ቀይ የደም ሴሎችና በደማችን ውስጥ የሚገኘውንናደምን ለማርጋት የሚጠቅመውን ‹ፕላተሌት› የተባለ የሴልቅንጣት የሚዋጉና ሊያጠፉም የሚችሉ ናቸው፡፡ ከዚያም ያለፈእንደ ሕመምተኛው ልዩ ሁናቴ በሠራ አካላታችን ውስብስብ የሆኑ እስከ ሞት የሚያደርስ ዘላቂ ችግሮችን ሊያስከትል የሚችል ደዌ ነው፡፡ እንደ ደረጃው ክብደት መፍትሔ ያገኙቢኖሩም፣ ብዙውን ጊዜ ሲያገረሽም ይስተዋላል፡፡ ፈውስ አገኙየተባሉት ጥቂቶቹም ዕድሜ ልካቸውን በሚደረግ ክትትልናጥንቃቄ መኖር እንዳለባቸው ባለ መድኃኒቶቹ አበክረው ያሳስባሉ፡፡
ከፍ ብዬ ስለ ነቀርሳ ደዌ ከዐዋቂዎቹ የተረዳሁትንመጠነኛ መግለጫ ለጽሑፌ መግቢያ ያደረግሁት ነገረ ሕክምና የጽሑፌ ርእስ ሆኖ አይደለም፡፡ የዐምሐራን ሕዝብ ህልውና ብሎም የአገራችንን ኢትዮጵያ ግዛታዊና ሉዐላዊ አንድነት÷ ክብርና ኩራት ከዘረኛ ፋሺስቶች በመታደግ ዓላማ የትጥቅትግል የገቡ ወገኖቻችንን (የዐምሐራ ፋኖ) ትግሉ ከተጀመረበት ማግስት ጀምሮ እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ የተሰማኝን ምክርሳካፍል ብቆይም ሰሚ ዦሮ ባለማግኘቱ ሳልታክት ደጋግሜ ብናገር ክፋት የለውም በሚል ለትግሉ በተለይ÷ ባጠቃላይ ለኢትዮጵያ ‹‹ነቀርሳ›› የሆነውን የጥፋት ኃይል ማስወገዱ ላይ ስምምነት አለ ወይ የሚል ጥያቄ በማንሣት መፍትሔው እላይ እንደተጠቀሰው (በላቲኑ አገላለጽ ከአስፈላጊው ማስተካከያ ጋርmutatis mutandis/with the necessary changes having been made) የማያዳግም መሆን እንዳለበት ለመጠቆም ነው፡፡ በነገራችንላይ በዚህ አስተያየት የቀረበው ንጽጽር ወይም ማመሳሰል (analogy) ብአዴንን በቅጡ የሚገልጸው ሆኖ አይደለም፡፡ የዚህ ነውረኛ ቡድን ርኵሰት አቻ ተወዳዳሪ አይገኝለትምና፡፡
የዐምሐራን ሕዝብም ሆነ አገራችንን የተጣባው ‹ነቀርሳ› ሌላ ሳይሆን ፀሐይ የሞቀው አገር ያወቀው ብአዴን የተባለው ዘላለማዊ አሽከርነት÷ ሆዳምነት÷ ታሕተ ሰብእነት÷ የዓለሙ ማፈሪያነት መገለጫ ባሕርይው የሆነው የምናምንቴዎች ስብስብ ቡድን ነው፡፡ የዐምሐራ ፋኖ በርካታ ችግሮች ሊኖሩት ይችላል፡፡ ባንድም ሆነ በሌላ መልኩ ሁሉም ተጠቃልለው መነሻቸውም ሆነ መድረሻቸው ይህ ርጉም ‹ፍጡር› ብአዴንነው፡፡ በዚህ የምድር ዝቃጭ ‹ነቀርሳነት› ላይ የዐምሐራን ሕዝብ ፍትሐዊ የህልውና ትግል እንደግፋለን÷ ኢትዮጵያን በተግባር እንወዳለን በሚሉ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ዘንድ ስምምነት ካለ መፍትሔው ላፍታ ሳያወላውሉ ማጥፋት ብቻነው፡፡ ይህንን ገዳይ ‹ደዌ› ተሸክሜ እያስታመምሁ እቀጥላለሁ የሚል የትኛውም የፋኖ አደረጃጀትም ሆነ የዐምሐራ ሕዝብካለ፣ እሱ/እሷ ያለምንም ጥርጥር በቅድሚያ የምዐሐራ ሕዝብከፍ ሲልም የኢትዮጵያ ጠላት ነው፡፡ ምርጫው ሦስት ወይም ከዚያ በላይ አይደለም፡፡ ‹‹እሳት ወማይ አቅረብኩ ለከ÷ ደይ እዴከኀበ ዘፈቀድከ›› (እሳትና ውኃ በፊትህ አቅርቤአለሁ፤ እጅህን ወደፈለግኸው/ወደ መረጥኸው ስደድ፡፡) ይሄ ለዐምሐራ ፋኖየቀረበ ጥሪ ነው፡፡ ለሕዝብና ለአገር የቆምህ ኃይል መሆንህ እየተፈተነ ነው፡፡
ከፈተናዎቹ ቀዳሚውና ዋነኛው ከእንግዲህወዲህ ዘመድ ወገን ሳትል በዚህ ‹ነቀርሳ› ላይ የምትወስደው ርምጃ ነው፡፡ አጠገብህ ያለውም ሆነ አንድ ሐሙስ የቀረውየ4ኪሎው ቡድን አንተን አያሳታምምህም፡፡ ጀግንነቱ ሳያንስህእንዴት አንድነት በማጣትና በወሬ ትፈታለህ? እንዴት ቢሆንነው ከሁለት ዓመት በኋላ ብአዴን የሚባል ነቀርሳ እንደድርጅትም ሆነ ግለሰብ በዐምሐራ ምድር እንዲኖር የተፈቀደለት? አልፎ ተርፎም ሕዝቡን ግብር በማስገበርም ሆነ በሌሎች አጥፊ ድርጊቶች የጐሣ ፋሺስቶቹ አገዛዝ ገረድ ደንገጥር ሊያደርግ የቻለው? ሕዝቡን ምንኛ ቢንቁት ነው ርጉም ዐቢይም ሆነ ጀሌዎቹ ምድረ ዐምሐራን ለመርገጥ የበቁት? ጊዜ በሰጠኸው ቊጥር ርጉም ዐቢይና ወሮበላ ቡድኑ ከጻዕረ ሞቱ እንዲያንሠራራ እያደረግኸው እንደሆነ ላንተ መንገር አያሻኝም፡፡ በዚህ የምታምን ከሆነ በቅድሚያ በውስጥህ በአመራር ደረጃም ሆነ በተራ ጀሌነት ያለውን‹ነቀርሳ› አጥራ፡፡ በአራቱ ክፍላተ ሀገራት ብቻ ሳይሆን በመላውኢትዮጵያ ይህ ‹ነቀርሳ› መወገድ መጥፋት ይኖርበታል፡፡
በመግቢያዬ ላይ ነቀርሳን ለማጥፋት የሚወሰድ መድኃኒት የጉዳቱ መጠን ይለያይ እንጂ በሌላ አካላችን ላይ ጉዳት ማድረሱ አይቀሬ ነው፡፡ ጥረታችን መሆን ያለበት ጉዳቱን በተቻለ መጠን መቀነስ ብቻ ነው፡፡ ባንዳን አስታምሞ የተሳካ ትግል በታሪክ አልተመዘገበም፡፡ ወያኔ ብአዴንን ሲፈጥረው ሕሊና አልባ አድርጎ ነው፡፡ ባንዳ እምነቱ ሆዱ ነው፡፡ አሁን ላለውም ሆነ ለቀጣዩ ትውልድ ባንዳነት ከዐምሐራ ሕዝብ መንፈሳዊም ሆነ ባህላዊ ዕሤቶች ጋር ተቃራኒ መሆኑን ለሚያስተምር በሚያስችል መልኩ ‹ነቀርሳውን› በማያዳግም መልኩ ማጥፋትይኖርብናል፡፡
በሌላ በኩል ዐምሐራ÷ ትናንት ወያኔ ትግሬ በፈጠረው‹ክልል› የሚወሰን ሕዝብ አይደለም ሊሆንም አይችልም፡፡ ይህን እባጭ ብአዴን ቆርጠህ ሳትጥል ለዐምሐራም ሆነ ለመላው ኢትዮጵያ ድኅነት የለም፡፡ ወሬ፣ ፉከራና መግለጫ ይብቃ፡፡ እንደ አጀማመርህ መልካም ፍሬህን በተግባር አሳይ፡፡ በሰቆቃ ያለውንሕዝብህንና እየፈራረሰች ያለች አገርህንን የምታስቀድም ከሆነእግዚአብሔር ይርዳህ፡፡ የዚህም መገለጫው አንድነት ኅብረት ፈጥረህ እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናገሪ ሆነህ ጅምሩን ማጠናቀቅ ነው፡፡
ከዚህ ውጭ ከነቀርሳው ሳትገላገል÷ የደዌያት ምንጭ ከሆኑት ወያኔና ኦሕዴድ/ኦነግ ጋር አንሶላበመጋፈፍ ለጊዜያዊ ሥልጣንና ለሀብት ዘረፋ የምትራኮት ከሆነወላዲተ አምላክ ጥፋትህን ታሳየኝ፡፡ ነቀርሳን (ከሚያስከትለውጉዳት ጋር) ከማስወገድ ውጭ ሌላ ምርጫ የለም፡፡ ገዳይ ነውና፡፡