>

ሙስጠፌና አብዲልሀፊዝ Hardtalk ክፍል አራት (ሙክታሮቪች)

ሙስጠፌና አብዲልሀፊዝ Hardtalk

 

ክፍል አራት
(ሙክታሮቪች)
ጋዜጠኛ:
ክቡር ፕሬዝዳንት ሁለት ሰው በአሁኑ ወቅት በእስር ላይ ያሉ አሉ። አንዱ ሪፐርተር አንዱ ደግሞ የቀድሞ አድቫይዘርዎት መሆናቸው ይታወቃል። ለምን ታሰሩ?
ሙስጠፋ:
በአሁኑ ወቅት በእስር ላይ አይደሉም። ቀድሞ ታስሮ የነበረው ገፍዲድ ነው። ከደር ቀድሞም አልታሰረም፣ አሁንም አልታሰረም።
በነገራችን ላይ የተሳሳተ መረጃ ደርሶሃል። ገፍዲድ የኦብነግ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል እንጂ ጋዜጠኛ አይደለም። ከደር ኦላድም የእኔ አድቫይዘር የነበረ ሰው ነው። በነፃነት እየተንቀሳቀሱ ነው በአሁኑ ወቅት። ደውለህ ልታገኛቸው ትችላለህ።
ጋዜጠኛ;
ቀድሞስ ለምን ገፍዲድ በማስረጃ ምን ተገኝቶበት ነው የታሰረው?
ሙስጠፋ:
እንደቅድሙ በህግ የተያዘ ጉዳይ ነው። ሆኖም ደጋግመህ እንዳትጠይቀኝ ወደ ዝርዝር ጉዳዮች ሳይገባ ጠቅላል አድርጌ ልንገር።
ገፍዲድ ፖለቲከኛ ነው። የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃ አውጪ ግንባር ማዕከላዊ ኮሚቴ ነው እንደነገርኩህ። ለረጅም ጊዜ በሀገሪቱ በወንጀል ሊያስከስሰው የሚችልን ተግባር በማህበራዊ ሚዲያ ሲቀሰቅስ ነበረ። እንግዲህ ከፓርቲው ጋር ስምምነት ነበረን በሰላማዊ ፖለቲካ ለመጓዝ። እሱ ግን በእኔ ላይ ግድያ እርምጃ እንዲካሄድ ሲቀሰቅስ። ሀይማኖታቸው ከሶማሌ ህዝብ ሀይማኖት የተለየውን እንዲገደሉ ሲቀሰቅስ በኦዲቪዡአል ማስረጃ አለን። ወንድሜ በጩቤ እንደተወጋ ታስታውሳለህ። ይህን አሳዛኝ ጉዳይ በተመለከተ አደገኛ አስተያየቶችን ሲናገር ነበረ። ጎሳን ከጎሳ የሚያጋጭ ቅስቀሳ ውስጥ ሲገባ እንግዲህ ከዚህ በላይ አንታገስም ብለን አስረነው፣ በዋስ ተፈቷል።
ባለፈው ከባድ አደጋ በክልላችን የደረሰ አደጋ የሶማሌን ህዝብ ምስል አበላሽቶብን ነበረ። ይህ እንደ ደገም ስላለፈቀድን ይዘነው፣ በዋስ ተፈቶ አሁን ነፃ ነው?
ጋዜጠኛ፣
ፍትሃዊ ፍርድ እንደሚያገኝ ቃል ይገባሉ
ሙስጠፋ:
ሰውዬው ከእስርቤት ውጪ ነው አልኩህ እኮ። ፍርዱ ቅድም እንዳልኩህ በህጉ ያለው መብት ሁሉ ተጠብቆለት ይዳኛል።
ጋዜጠኛ:
መልካም ወደ ሌላ ጥያቄ ልለፍ። እርስዎ አሁን የሚገኙበት ጂግጂጋ ከባድ የውሃ ችግር አለ። የመጠጥ ውሃ ችግር አለ። ቅድም ብዙ ስኬት እንዳስመዘገባችሁ ነግረውናል። ታዲያ የጂጂጋ ከተማ ውሃ ችግር ከየት የመጣ ነው። ከዚህ ቀደም ያልነበረ እና የማይነገር ችግር አሁን እንዴት መጣ? ለምንስ አልተቀረፈም?
ሙስጠፋ:
የጂጂጋ የውሃ ችግር ቀድሞ ከኔ በፊትም የነበረ ነው። አሁን ድንገት የመጣ አድርገህ ማቅረብ የለብህም። ከዚህ ቀደም በአብዲሌ ቆይታ ጊዜ አምስት ቢሊየን የህል ገንዘብ የተበላበት ችግር ነው። ሌቦች እተፈራረቁ የሚበሉበት ጉዳይ ነው።
እኛ ስንመጣ ይህን ችግር ለመቅረፍ እየተንቀሳቀስን ነው። አሁን የውሃ ሽፋኑ እየተሻሻለ መልካም በሚባል ደረጃ ነው ያለው።
ልዩነቱ የቀድሞ መንግስት ያልተሰራን በፕሮፓጋንዳ ያሳያል። እኛ በውሸት ፖለቲካ መነገድ አንፈልግም። የቀድሞ ስርዓት ስለችግር መተንፈስ አትችልም። እኛ ግን የሰውን ቅሬታ የማቅረብ መብት ሰጥተናል። ለዚህ ነው ችግሩ የተጋነነ የመሰለህ።
ሌላው
ባሳካነው ሰላም ምክንያት በርካታ ኢትዮጵያውያን ክልሉን ምርጫ አድርገው ለኑሮም፣ ለንግድም እና ለተለያየ አላማ እየመጡ ነው። ይህ ደግሞ በውሃ አቅርቦት ላይ ጨና መምጣቱ የሚጠበቅ ነው። በፌስቡክ የሚለቀቁ፣ እውነታውን የማያንፀባርቁ ፎቶዎችን ሳይሆን ከፈለክ እኔ ከክልሉ ውሃ አገልግሎት ባለስልጣን ጋር አገናኝቼህ ዝርዝር መረጃ እንዲሰጥህ ለማድረግ እችላለሁ።
ጋዜጠኛ:
ቅድም ብዙ ስኬቶችን እንዳስመዘገቡ ተናግረዋል። ሆኖም እኛ የተለያዩ ሰዎችን ጠይቀን መረጃ ሰብስበን በርካታ ችግሮች እንዳሉ ለማወቅ ችለናል።
መንገድ የለም። የመሰረተ ልማት ችግሮች አሉ። የፈራረሱ መንገዶች በየቦታው አሉ። በኢኮኖሚም በኩል ችግር አለ። እንዳልኮት ውሃ ችግር አለ።
ሙስጠፋ:
ስላሳካነው ጉዳይ ዶክመንት ስለደረግነው ላቀርብልህ እና በፕሮግራምህ አሳይተህ ህዝቡ መመልከት ይችላል።
ጋዜጠኛው:
አሃ በእናንተ የተዘጋጀውን ነው እኛ የምናስተላልፈው? እውነታ የሌለው ነገር አዘጋጅታችሁ ቢሆንስ?
ሙስጠፋ:
ከፈለክ መጥተህ በአካል ማየት ከፈለክም እንደዚያው። በዋይፋይ ከቻልንም እንዳሁኑ ቃለመጠየቅ አይነት በማዘጋጀት ማስጎብኘት እንችላለን።
ጋዜጠኛው:
የፈራረሱ መንገዶች፣ የውሃ ችግሩ እኮ ፈጦ ያለ ነው ክቡር ፕሬዝዳንት
ሙስጠፋ (ፈገግ አለ፣ በቅሬታ አይነት)
አብዲሀፊዝ እባክህ እንዲህ አይጠየቅም። ለተመልካቾቻችን ክብር ስንል እንዲህ አይጠየቅም
ጋዜጠኛ:
ለምን አይጠየቅም
ሙስጠፋ:
የሚጠየቀው ባላችሁ ሀብት ምን አቅዳችሁ ምን አሳካችሁ ነው። ለምሳሌ ጥናት አድርገን የዚህ ክልልን በአንድ አመት የተሻለ ልማት ልናመጣ የምንችለው በምን ያህል ገንዘብ ነው ብለን ብሩ ወደ አስር ቢሊየን ዶላር ያህል ይሆናል። እኛ በወቅቱ በእጃችን የነበረው አምስት ቢሊየን ዶላር ነው።
በዚህ በያዝነው ብር ምን ቅድሚያ በመስጠት ሰራን፣ ብሩ የት ገባ? ባቀዳችሁት መሰረት ምን አሳካችሁ? ብለህ መጠየቅ ጥሩ ነው።
አንተ በምትጠይቅበት መንገድ ግን ጥያቄ አይጠየቅም።
ጋዜጠኛ:
እንዴ ክቡር ፕሬዝዳን ጥያቄ የመጠየቁ አማራጭ መንገድ እኮ የኔ ምርጫ ነው። እንደፈለኩት ብጠይቅ ምን ችግር አለው?
ሙስጠፋ:
እሱማ መብትህ ነው መጠየቅ፣ ሰው ይታዘበኛል የማትል ከሆነ።
ለምሳሌ እኔ ልጠይቅህ?
ጋዜጠኛ:
አሺ
ሙስጠፋ:
ሞቃዲሾ እንደ ኒውዮርክ ለምን ፎቅ በፎቅ አልሆነች ብዬ ብጠይቅህስ?
(ጋዜጠኛው አልመለሰም)
አየህ አንድ ነገር ስረ መሰረቱን የሚገነዘብ ጥያቄ ነው መጠየቅ ያለብህ። facts on the ground and reality የሚባል ነገር አለ። ይህን መሳት የለብህም። በዚህ መንገድ መጠየቅ የምንችለውን እና የማንችለውን፣ የተሳካ እና ያልተሳካውን ለመለየት እና ለመሞገት ይቻላል።
ለምን የፈረካከሰ መንገድ ይኖራል ብሎ ጥያቄ ለኔ ጥያቄ አይደለም።
ደሃ ሀገር ነው ያለነው። በርካታ ያልተሟሉ ነገሮች አሉ። ፍላጎት አለ።
እንኳን እዚህ አንተ ያለህበት የለንደን ነዋሪን ስለመሰረተ ልማት ብትጠይቀው በርካታ ችግር ሊነግርህ ይችላል።
ጋዜጠኛው ፈዞ ቀረ።
ሙስጤ ፈገግ አለ።
ጋዜጠኛው ወደ ሌላ ጥያቄ ለመሻገር ጎሮሮውን ጠረገ።
Filed in: Amharic