>

የሰሜን ሸዋ ኮማንድ ፖስት ዓላማ፡ሰሜን ሸዋን ሰሜን ኦሮምያ ማድረግ! (መስፍን አረጋ) 

የሰሜን ሸዋ ኮማንድ ፖስት ዓላማ፡ሰሜን ሸዋን ሰሜን ኦሮምያ ማድረግ!

መስፍን አረጋ) 

ይህ ጦማር ሰባት ነጥቦችን ያካተተ ጦማር ነው፡፡

አንደኛ ነጥብ፡፡  ዐብይ አሕመድ ለሰሜን ሸዋ የደገሰለትን ኦነጋዊ ድግስ፣ በቀጠናው ውስጥ ባስቀመጣቸው ሁለት ኦነጋዊ እንደራሴወች አማካኝነት የፓርላማን ሕግ በጣሰ መልኩ በጥያቄ መልክ እንዲነበብ አደረገ፡፡  ጥያቄውም የአማራ ልዩ ኃይል አካባቢውን ለቆ እንዲወጣና በምትኩ መከላከ እንዲገባ ነው፡፡  የመከላከያ እንዲገባ የተፈለገበት ምክኒያት ደግሞ፣ በስሙ የሀገር መከላከያ ቢሆንም በግብሩ ግን የኦሮሞ፣ ለኦሮሞ በኦሮሞ የሆነ የኦነግ መከላከያ በመሆኑ ነው፡፡  ባጭሩ ለመናገር ኦነግ ሸኔ የጫካ ኦነግ ሲሆን፣ መከላከያ ደግሞ የከተማ ኦነግ ነው፡፡  ሁለቱም የኦነግ ወታደራዊ ክንፎች ናቸው፡፡  የኦነግ ፖለቲካዊ ክንፍ ደግሞ በራሱ በዐብይ አሕመድ የሚመራው በስሙ የተደገፈው መልከ ጥፉው ብልጽግና ነው፡፡    

ሁለተኛ ነጥብ፡፡ ዐብይ አሕመድ የጫካውን ኦነግ (ማለትም ኦነግ ሸኔን) እና የከተማውን ኦነግ (ማለትም መከላከያን) በማስተባበርና በማቀናበር በሰሜን ሸዋ አማሮች ላይ ከፍተኛ ሽብር ከፈተ፡፡ ቀጠናው ከሞላ ጎደል ሙሉ በሙሉ ከአማሮች ነጻ እስኪሆን ከጠበቀ በኋላ፣ በቀጠናው ላይ የከተማው ኦነግ (ማለትም መከላከያ) አዛዥና ናዛዥ የሆነበትን ኮማንድ ፖስት አቋቋመ፡፡  በዚህም ሁለቱ አነጋዊ እንደራሴወች በፓርላማ ላይ እንዲጠይቁ ያደረጋቸውን ጥያቄ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ መልስ እንዲያገኝ አደረገ፡፡ 

ሦስተኛ ነጥብ፡፡  ቀጠናው በኮማንድ ፓስት ስም በከተማው ኦነግ (ማለትም በመከላከያ) ሙሉ ቁጥጥር ውስጥ ሲሆን፣ የጫካው ኦነግ (ማለትም ኦነግ ሸኔ) ወደቀጠናው እየገባ ሁከት እንዳይፈጥር ቀጭን ትእዛዝ ስለሚሰጠው ወደ ቀጠናው ዝር አይልም፡፡  ወደ ቀጠናው ለመመለስ የሚሞክሩ ዐማሮች (በተለይም ደግሞ ወጣቶች) ደግሞ አሸባሪወች እየተባሉ በተገኙበት በኮማንድ ፓስቱ ይደመሰሳሉ፡፡  ዐብይ አህመድ ደግሞ ቀጠናውን በኮማንድ ፓስት በማስተዳደር ሰላም አሰፈንኩ እያለ ይታበያል፡፡  የመንግስት ሚዲያወችና ኢሳትን የመሳሰሉ ተደማሪ ሚዲያወች ደግሞ ታላቁ ሰላም አስከባሪ እያሉ ለዐብይ አሕመድ ውዳሴያቸውን ቀን ከሌት ያዘንቡለታል፡፡  ኮማንድ ፖስቱ ደግሞ ሰላም ስላሰፈነ እድሜው ይራዘም ተብሎ በፓርላማ ይጠየቃል፡፡  የይስሙላው ፓርላማ ደግሞ ጥያቄውን ወዲያውኑ ያጸድቃል፡፡     

ዐራተኛ ነጥብ፡፡  የኮማንድ ፓስቱ እድሜ ሥራውን እስኪያጠናቅቅ ድረስ ይራዘማል፡፡  ይህ ሥራው ደግሞ (ልክ መተከል ላይ እንደተደረገው) በተነቀሉት አማሮች ምትክ ኦሮሞወችን እየተከለ፣ የሕዝብ አሰፋፈርን በመቀየር ሰሜን ሸዋን ሰሜን ኦሮምያ ማድረግ ነው፡፡  የሰሜን ሸዋ ኮማንድ ፖስት ዓላማ ይሄውና ይሄው ብቻ ነው፡፡

አምስተኛ ነጥብ፡፡  ያማራ ልዩ ኃይል እስካፍንጫው የታጠቀውን የወያኔን ጦር በነፍስ ወከፍ መሳርያ ብቻ ድባቅ በመምታት፣ ያብይ አሕመድን አገዛዝ ከውድቀት ያዳነ ትልቅ ኃይል ነው፡፡  በመሆኑም ይህ ትልቅ ኃይል ተገቢው ስንቅና ትጥቅ ከቀረበለትና ከጀርባው ካልተወጋ፣  ሰሜን ሸዋን ቀርቶ ሙሉ ሸዋን ከኦነግ ሠራዊት ሙሉ በሙሉ ለማጽዳት ሳምንት አይፈጅበትም፡፡  ስለዚህም፣ የዐብይ አሕመድን ኦነጋዊ እቅድ ለመተግበር ካልሆነ በስተቀር፣ በብርሃኑ ጁላ የሚመራው ጦር ሰሜን ሸዋን በኮማንድ ፓስት ስም የሚያስተዳድርበት ምንም ምክኒያት የለውም፡፡ 

ስድስተኛ  ነጥብ፡፡  ይህ ደግሞ የአማራ ክልል አስተዳዳሪ ነው ለሚባለው ለአቶ አገኘሁ ተሻገር ነው፡፡  ጀግንነቱን ያስመሰከረው ያማራ ልዩ ኃይል እያለ፣ በብርሃኑ ጁላ የሚመራውን የኦሮሙማ ጦር ዐብይ አሕመድ በኮማንድ ፓስት ስም ሰሜን ሸዋ ላይ የሚያሰማራበት ምንም ምክኒያት ስለሌለው፣ በገዛ ፈቃድህ አሰማራ እንጅ እኔ አልፈቅድልህም በለው፡፡  አለበለዚያ ያጼ ዳዊትን ምድር፣ አጼ አምደ ጽዮን ገድሉን በደሙ የጻፈበትን ቅዱስ ቦታ፣ አጼ ልብነድንግል አማራን በቱርክ ከሚታገዝ ጨፍጫፊ ለመታደግ የተንከራተተባቸውን ተራሮችና ሸንተረሮች፣ የኦነግ መፈንጫ ታስደርግና ታሪክ ይቅር የማይልህን ትልቅ ጥፋት ታጠፋለህ፡፡  ዐብይ አሕመድ የሚፎክረው ባንተ (ማለትም በብአዴን) ላይ ቁሞ ስለሆነ፣ አንድ ቀን ጀግነህ አሻፈረኝ ብትለው (ለማ መገርሳ በጌታቸው አሰፋ ፊት አደረገው እንደሚባለው)፣ ዐብይ አህመድም በቁሙ ሲሸና ታየዋለህ፣ ጨካኝ ሲባል ፈሪ ነውና፡፡        

ሰባተኛ ነጥብ፡፡  ወያኔ የለኮሰውን አማራን የሚለበልበውን እሳት የሚያቀጣጥለው፣ ባማራ ታዝሎ ቤተመንግስት የገባው ራሱ ዐብይ አህመድ ስለሆነ፣ ዐብይ ካልተወገደ እሳቱ አይበርድም፡፡        

 

መስፍን አረጋ mesfin.arega@gmail.com  

Filed in: Amharic