>
5:13 pm - Tuesday April 19, 4935

በከማሺ ዞን  የሴዳል ወረዳ ከሃያ አምስት ሺህ በላይ ነዋሪዎች  በታጣቂዎች ቁጥጥር ስር ውለዋል...!!! (የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን)

በከማሺ ዞን  የሴዳል ወረዳ ከሃያ አምስት ሺህ በላይ ነዋሪዎች  በታጣቂዎች ቁጥጥር ስር ውለዋል…!!!

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ)


*…የወረዳው አስተዳደር እና ፖሊስ አካባቢውን ጥለው ወደ ተለያዩ ስፍራዎች ሸሽተዋል!
 በቤኒንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ ከማሺ ዞን የሚገኘውና ከሃያ አምስት ሺህ በላይ ነዋሪዎች የሚገኙበት የሴዳል ወረዳ ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል ደረጃ፣ ከሚያዝያ 11 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ በታጣቂዎች ቁጥጥር ስር መዋሉን የደረሱት መረጃዎች ያመላክታሉ። በርካታ ነዋሪዎች፣ የወረዳው አስተዳደር እና ፖሊስ አካባቢውን ጥለው ወደ ተለያዩ ስፍራዎች መሸሻቸውን ኮሚሽኑ ተረድቷል። ታጣቂ ቡድኑ የመንግስት እና የግለሰብ ንብረቶችን ማቃጠሉን፤ ነዋሪችን፣ የወረዳውን እና የዞን አመራሮችን እንዲሁም የመንግስት ሰራተኞችን መግደሉን እና ማገቱም ተገልጿል። ኢሰመኮ ያነጋገራቸው የአካባቢው ነዋሪዎች በአቅራቢያው ያለው የፀጥታ ኃይል ከአቅሙ በላይ እንደሆነና ተጨማሪየተላከው ኃይልም ወደ አካባቢው እንዳልደረሰ ይገልጻሉ።ይህ ክስተት በክልሉ የቆየው የጸጥታ ችግር እየተባባሰና መልኩን እየቀየረ መምጣቱን የሚያሳይ በመሆኑ ከፍተኛ ስጋት የሚያሳድር ነው። ኢሰመኮ ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለሲሆን፣ ከሚመለከታቸው የፌዴራል እና የክልል መንግስት አካላት ጋር በመነጋገር ላይ ነው። ኮሚሽኑ መንግስት በአፋጣኝ የአካባቢው እና የክልሉን የፀጥታ ኃይል እንዲያጠናክርና እና ተጨማሪ የሰዎች ሞት እና የከፋ ሰብዓዊ መብቶች ጥሰት እንዳይከሰት እንዲከላከል ጥሪውን ያቀርባል::
Filed in: Amharic