>

በምርጫው ምክንያት አዲስ አበቤን ለምትወቀሱ ትንሽ ማሳሰቢያ! (ዳግማዊ ጉዱ ካሣ)

በምርጫው ምክንያት አዲስ አበቤን ለምትወቀሱ ትንሽ ማሳሰቢያ

ዳግማዊ ጉዱ ካሣ


በኢትዮሪፈረንስ ድረገጽ ላይ የሚከተለውን አነበብኩ፤ አንዳንድ የዋሃን እንዳለ ሊቀበሉት ስለሚችሉ መጠነኛ ማብራሪያ መስጠትን ወደድኩ፡፡ አዲስ አበቤ ያ ሁሉ ብርድና ዝናብ እንዲሁም ፀሐይ እየተፈራረቀበት ብዙ ሰዓታትን ተገትሮ ድምጹን የሰጠው ለጭራቁና ለዐረመኔው ሰውበላ የአቢይ ኢሕአዲግ ሣይሆን ከኢዜማና ከብልጽግና ውጭ ላሉ ፓርቲዎች መሆኑን ለመረዳት ብዙ መፈላሰፍን ወይም የመንዝ ደብተራና የፈረቀሳን አበጋር መጠየቅን አይሻም፡፡ አዲስ አበባን የሞላት ገጠርን ከከተማ የሚያገናዝብ፣ የበፊትን ኑሮ ከአሁኑ የሚያነጻጽር ልባምና አስተዋይ እንጂ በሚወረወርለት መናኛ ድርጎ የሚታለል ወይ የሚሸወድ የብልጽግና ካድሬና ተላላኪ አይደለም፡፡ ይህን እውነት የምናውቅ የይርጋለም ጽሑፍ እንዲስተካከል ብንጠይቅ ትክክል ነን፡፡ አዲስ አበቤ እጅግ ብልኅ ነው፡፡ 

“አዲስ አበቤ ልዩ ጥቅምንና የዘር ፖለቲካን  መርጧል…!!!” (ይርጋለም ታደሰ)

አዲስ አበቤ በምንም መንገድ ብልጽግናን በአብዛኛ ድምጽ ሊመርጥ እንደማይችል የነፍሴን ልመሰክር እወዳለሁ፤ ስለዚህ ይርጋ ታደሰ ይህን ልብ እንድትልልኝ እፈልጋለሁ – አንድ ወገን ወይም አንድ ሰው ካለአበሳው ሲወቀስ ማየትም ሆነ መስማት ያስከፋል፡፡ ብልጽግና የሚባለው የጥፋት ወኪል በሠራው ፊንታና ደባ የሕዝብ ድምፅ ተሰርቆ እንጂ ብልጽግናም ሆነ ኢዜማ በአዲስ አበባ ቀርቶ በየትም የኢትዮጵያ ክፍል ሊያስመርጣቸው የሚችል አንዳችም መልካም ነገር የላቸውም፡፡ ጨፍጫፊንና የጨፍጫፊን ተባባሪ ማን ሊመርጥ ይችላል!! በአሻር የአንድ ኩንታልን ጤፍ ዋጋ 7 ሽህ ብር እያስገባ ያለ ፓርቲ፣ ሰውን በተለይም አማራን መግደል እንደመዝናኛ የሚቆጥር ናዚስት አምባገነን እንዴት ሊመረጥ ይችላል!! ዐይን ባወጣ ሁኔታ አጭበርብረው እንዳሸነፉ አድርገው አሁን ቢያውጁ ውጤቱን ወደፊት ያዩታል፡፡ በጎንደር አካባቢ የምንሰማውን ግን አንድዬ ይፍታው፡፡ የጎንደር ሕዝብ አማራን ገዳዩን ብልጽግናን በርግጥም መርጦ ከሆነ ደይን አለበት – መከራና ፍዳ፡፡ ይሄ ዓይነቱ በአንዳንድ ሥፍራዎች የሚታየው የአማራ መከፋፈል ስቃዩን ያራዝምበታል እንጂ በምንም መንገድ የመፍትሔው አካል ሊሆን አይችልም፡፡ የሚያርድህን መምረጥ የጤነኝነት ምልክት ባለመሆኑ ብልጽግናን የመረጡ ሁሉ አስቸኳይ ህክምና ያስፈልጋቸዋል፤ በጥቅምና በዓላማ የተያያዙ ከሆኑ ግን ምንም ማድረግ አይቻልም፡፡ ለምን ክርስቶስንም የሸጠ ጉድ በሃይማኖታዊ ታሪክ ተመዝገቧልና፡፡ ክህደትና ከሃዲነት ዛሬ አልተጀመረም፤ ያለ ነው፡፡ የሆነ ሆኖ ይሁዳ አምላኩን ሸጦ ባገኘው ገንዘብ እንዳልተጠቀመ ሁሉ የአሁኖቹ ይሁዲዎችም በሽያጩ ገንዘብ ያሰቡትን ያህል ሊጠቀሙ አይችሉም፤ ንጋቱ ሁላችንም ከምንገምተው በላይ በእጀጉ ተቃርቧልና፡፡

ስለዚህ አዲስ አበቤ ድምጹ ባልሰጠበት ሁኔታ መታማት የለበትም፡፡ ድምጹ ተቀምቷል፡፡ የተቀማውን ድምጽ ለማስመለስ ግን እንደ97ቱ የተጭበረበረ ምርጫ አደባባይ ወጥቶ በጨካኞች መታረድን አልመረጠም፡፡ ቀኑን ጠብቆ ግን ልክ እንደወያኔ እነዚህንም ሂሳባቸውን ይሰጣቸዋል፡፡ አንቸኩል፡፡ አለቀ፤ ደቀቀ፡፡ ብልጡ አቢይ ብቻ አይደለም፡፡ አዲስ አበቤም ብልጥ ሆኗል፡፡ በዚህ “ምርጫ” ድል የተጎናጸፈው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንጂ በተጨፈኑ ላሞኛችሁ ኮረጆ እየሰረቀና እየለወጠ እንዳሸነፈ የተቆጠረው ብልጽግና አይደለም፡፡ በተሰረቀ ድምጽ የሚገኝ አሸናፊነት ደግሞ የጊዜ ጉዳይ እንጂ ደስታውም ሆነ ፈንጠዝያው እንደጠየዛ መርገፉ አይቀርም፡፡ ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ ነው፡፡ አለባብሶ የሚያርስም በአረም መመለሱ አይቀርም፡፡ እውነተኛ ደስታ የሚገኘው በሃቅ እንጂ በማጭበርበር በሚገኝ ጊዜያዊ ድል አለመሆኑን በግምባር የሚመጣው ኢትዮጵዊ ጊዜ በተግባር ያሳየናል፡፡ ለማንኛውም ከተደገሰልን የመከራ ዶፍ እኛም ሀገራችንም እንተርፍ ዘንድ አጥብቀን እንጸልይ፡፡ ሌላውን ተውት፤ ወያኔና ደርግም ተረት ተረት ሆነዋል እንኳንስ ሮጦ ያልጠገበ ወጣቱ አፄ ቦካሣ ወግራኝ አህመድ፡፡

Filed in: Amharic